Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ሐዋርያዊ ጉዞዎችና ጉብኝቶች

በሰማዕታት ደም ለጸናው በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን የሚኖር የጋራ ግኑኝነት ክብር

በሰማዕታት ደም ለጸናው በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን የሚኖር ጋራ ግኑኝነት ክብር - OSS_ROM

02/12/2015 15:35

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚህ ዝክረ 50ዓመት የኡጋንዳ ሰማዕታት የቅድስና አዋጅ በሚከበርበት በአሁኑ ወቅት በኡጋንዳ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት በኡጋንዳ የሰማዕታት ቅዱስ ሥፍራ እ.ኤ.አ. ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 9 ሰዓት ተኩል በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ምእመናን የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ዓበይት የመንግሥት አካላት በተገኙበት መሥዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ ገልጠዋል።

 

የካቶሊካዊትና አንግሊካውያን ሰማዕታት ቅዱስ ሥፍራ

ቅዱስ አባታችን በናሙጎንጎ የሚገኘው የአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሰማዕታት ቅዱስ ስፍራ ጎብኝተው እዛው ከአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ጋር ተገናኝተው የህሊና ጸሎት አሳርገው እንዳበቁ፣ በዚያ ቅዱስ ካርሎ ልዋንጋና 21 ወጣት ክርስቲያን ጓደኞቹ እውነተኛውና ብቸኛው ንጉሥሳቸው ክርስቶስ መሆኑ በመምስከራቸው እ.ኤ.አ. ሰነ 3 ቀን 1886 ዓ.ም. በክልሉ በነበረው ንጉሥ ለሞት በተዳረጉበት የደም ሰማዕትነት በከፈሉበት ቅዱስ ሥፍራ ተገኝተው መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው፣ የሰማእታቱ ምስክርነት ክርስቶስን ወደ ሁሉም የዓለም ማእዝን ለማድረስ አብነት ነው የሚል ቅዉም ሃሳብ ማእከል ያደረገ ስብከት መለገሳቸው ኦንዳርዛ ገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ባስደመጡት ስብከት የእነዚያ ወጣት ሰማዕታት ምስክርነት የምናከብረው በዝክረ በዓልና በቤተ መዘክር ለማስቀመጥ እንደ ሚወረስ የእምነት ሃብት ስናቅብ ሳይሆን እነርሱ ለክርስቶስ የከፈሉት መሥዋዕትነት በዚህ በምንኖርበት ዘመን ወደ ቤታችን ለጎረቤቶቻችን በምንሰራበት ሥፍራ በምንኖርበት ማኅበረሰብ እስከ አጽናፍ ዓለም ምስክርነታቸውን ስንመስከር ብቻ ነው።

የኡጋንዳ ሰማዕታት ለክርስትና ሕይወት አደገኛ በሆነበት ዘመን ክርስቶስ ያወጁ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ካርሎ ልዋንጋና ጓደኞችን ጠቅሰው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ለማፈን የማይቻል መሆኑ በማብራራት፣ በእምነት ከታነጹ በኋላ ያንን የተቀበሉት እምነት በዚያ አደገኛ በሆነበት ዘመን መስክረውታል። ምስክርነታቸውም ዛሬም ክርስቶስን የሚያውጅ የመስቀል ኃይል የሚያበስር ነው ብለው፣ የሰማዕታቱ ሕይወት ብቻ ሳይሆን ለእነርሱ በአደራ የተሰጡት የወጣቶች ሕይወት ጭምር ነበር ላደጋ የተጋለጠው፣ ለሌሎች ክርስቶስ ለመመስከር ሕይወታቸው ለመሰዋት አልፈሩም፣ እምነታቸው ምስክርነት ሆነ፣ ዛሬ ሰማዕታት ብለን እናከብራቸዋለን፣ አብነታቸው አሁንም ለብዙ ሰዎችና ለዓለም አስተንፍሶ ነው።

ክርስቶስ ልኡካነ ወንጌል እንድንሆን ይጠራናል፣ ለጓደኞቻችን ለጠላቶቻችን ሁሉ፣ ለዚህ ተልእኮ ክፍት መሆን ከቤተሰብ ከፍቅርና የምህረት ትምህርት ቤት የሚጀምር አዛውንቶችን ለመንከባከብ ድኻው መበለት ወላጅ አልባ ሁሉ ለመንከባከብ የሚያንጽ ነው።

ለሥልጣንና ለዓለማዊ ድሎት ሳይሆን ለጌታ ታማኝ በመሆን ዘላቂነት ያለው ሐሴት እንለግስ

የሰማዕታት ምስክርነት ለሥልጣን ወይን ለዓለም ድሎት ሳይሆን ለእግዚአብሔር ታማኝነትና ቅነነት፣ የሕይወት ምሉእነት ስለ ሌሎች አሳቢና ገር ለመሆን የሚያበቃ ዘላቂ ሐሴትና ሰላም የሚሰጥ ነው።

መጻኢን ብቻ በማተኰር ስለ ወቅታዊው ዓለም ችላ በል የሚል ምስክርነት ሳይሆን ለዚህ ዓለም ህያው ግብ የሚያቀርብ የተናቁትንና ለድኾች ቅርብ ለመሆን የሚያበቃ ስለ የጋራ ጥቅም ከሌሎች ጋር ለመተባበር የሚደግፍ በጋራ ቅንና ፍትህ የተካነው ማንም የማያገል የሰው ልጅ ክብር ለማነቃቃት ሕይወት የእግዚአብሔር ጸጋ ለመከላከል የሁላችን ቤት የሆነው ተፈጥሮና የተፈጥሮ አስደናቂነ ለመንከባከብ የሚያንጽ ነው በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያስደመጡት ስብከት ማጠቃለላቸው ኦንዳርዛ አስታወቁ።   

02/12/2015 15:35