2015-11-30 16:01:00

ቅዱስ አባታችን ለኡጋንዳ ወጣቶች


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንችስኮ ካምፓላ በሚገኘው ኮሎሎ የአየር ማረፊያ ነበር ባለው አደባባይ ከኡጋንዳ ወጣቶች ጋር ተገናኝተው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።

ቅዱስ አባታችን ከአዲት ገና ከመወለድዋ የኤይድስ በሽታ ታማሚ የሆነች ወጣትና አንድ በአገሪቱ በሚገኘው የጌታ ታጣቂ ኃይል በማለት ገዛ እራሱ በሰየመው የአማጽያን ኃይል ተጠልፎ ሕጻን ወታደር በመሆን ያገለገለው ከዚያ ባርነት ነጻ የወጣው ወጣት ከሰጡት የምስክርነት ቃል በኋላ  በለገሱት ምዕዳን፦ በአይድስ በሽታ የተጠቁት ወጣቶች ፍቅር ሊለገስላቸውና ሊደገፉም የተገባ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኃላፊነት ነው።

ኢየሱስ ግድግዳዎችን ወደ አድማስ ይለውጣል

የሁለቱ ወጣቶች ገጠመኝ ጠቅሰው፣ ያንን አሉታዊ ገጠመኝ ኢየሱስ ወደ አዲስ አድማስ ለውጦታል፣ በኢየሱስ ኃይል ሕይወታችን እንደሚለወጥ የሁለቱ ወጣቶች ሕይወት ምስክርነት ተአምራዊ አብነት ነው።

እናንተ የኡጋንዳ ወጣቶች የጥላቻው መንፈስ ወደ ፍቅር ለወጡት

በኢየሱስ ማመን ስጋት ሊሆን ይችላል፣ ሆኖም የሚያድነውም በእርሱ ላይ ያለን እምነት ነው። ሕይወታችን ልክ እንደ አንድ ዘር ነው፣ ለመኖር መሞት ያስፈልጋል፣ አንዳንዴም ሥጋዊ ሞት ሊያጋጥም ይችላል፣ ሆኖም ሞትን የሰማዕትነት ሞት ማድረግ ያለው የላቀው እሴት የኡጋንዳ ሰማዕታት ይመስክሩታል፣ አሉታዊ ገጠመኝ ወደ አወንታዊ ገጠመኝ ለመቀየር ስችል ባለ ድል እሆናለሁኝ፣ ይህ ደግሞ በኢየሱስ ጸጋ የሚቻል ነው ብለዋል።

ጦርነትን ወደ ሰላም። የሰማእታት አገር ልጆች መሆናችሁ ማስተዋል ይኖርባችኋል፣ ስለዚህ ይኽ ያላችሁ የአፈሪቃ ክቡር ሕይወት ነው። ኢየሱስ ያንን ለያይ ግንብ ወደ አድማስ ለውጦታል።

ችግሮችን መወጣት አሉታዊው ወደ አወንታዊ እንዲለወጥ መጸለይ

ከመጸለይ አትቦዝኑ፣ የልባችሁን በር ክፈቱ፣ ኢየሱስ ይገባ ዘንድ ፍቀዱለት፣ እርሱ በምናደርገው የሕወት ትግል ሁሉ ይደግፈናል ኃይልም ይሆንልናል፣ እርሱ በሕይወታችን ውስጥ ሲገባ ሁሉን ለመቋቋም ይቻለናል፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነን፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁላችን እናት አለችን እርሷም ቅድስት ድንግል ማሪያም ነች፣ እርሷን ተማጠኑ።

ስለዚህ ችግሮችን መወጣት፣ አሉታዊው ወደ አወንታዊ መለወጥና መጸለይ የተሰኙትን ሦስት ነጥቦች እትርሱ። ሊያድነኝ ሕይወት ሊሰጥኝ ወደ መጣው ኢየሱስ መጸለይ፣ እርሱ ብቻ ነው ጌታ፣ በቤተ ክርስቲያንም ወላጅ አልባ አይደለንምና እናታችን ወደ ሆነችን ቅድስት ማርያም እንጸልይ በማለት የለገሱት ምዕዳን እንዳጠቃለሉ ጂስቲ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.