Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ሐዋርያዊ ጉዞዎችና ጉብኝቶች

ቅዱስ አባታችን በኡጋንዳ፦ ድኾችን አትርሱ፣ ክርስቶስ በሚሰቃዩት ውስጥ ነው

ቅዱስ አባታችን በኡጋንዳ፦ ድኾችን አትርሱ፣ ክርስቶስ በሚሰቃዩት ውስጥ ነው - REUTERS

30/11/2015 15:54

እ.ኤ.አ. ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኬንያ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ዑደት አጠናቀው ወደ ኡጋንዳ በመነሳት በኡጋንዳ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከቀትር በኋላ 11 ሰዓት ከ 15 ደቂቃ ኤንተበ በሚገኘው ዓለም አቀፍ ያየር ማረፊያ እንደደረሱ በአገሪቱ ርእሰ ብሔር ዮዎሪ ሞሰቪኒና ክብርት ባለ ቤታቸው በአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳትና በብዙ ሺሕ የሚገመት የአገሪቱ ሕዝብ በመዝሙርና በባህላዊ ሸብሸቦ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ የቅድስት መንበርና የኡጋንዳ ሕዝባዊ መዝሙሮች ተደምጠዋል።

በመቀጠልም ቅዱስነታቸው ወደ ቤተ መንግሥት በመሄድ ከአገሪቱ ርእሰ ብሔር ጋር የግል ግኑኝነት አካሂደው እንዳበቁም በርእሰ ብሔሩ ተሸኝተው ከመንግሥት አበይት አካላትና በኡጋንዳ ከሚገኙት ከተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት ጋር መገናኘታቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ አያይዘው ቅዱስ አባታችን በዚህ የኡጋንዳ ሰማዕታት ቅድስና አዋጅ ዝክረ 50ኛው ዓመት ጋር በተያያዘው ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በቤተ መንግሥት ባሰሙት ንግግር፦ የደም ሰማዕትነት የከፈሉት የካቶሊካዊትና የአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሰማዕታት የአገር ጀግኖች በከፈሉት መሥዋዕትነት አማካኝነትም የእምነት ግብረ ገብ የተካነ ሕይወትና ለጋራ ጥቅም ትጋት የሰጡት ምስክርነት ዛሬ በአገሪቱ የባህል የኤኮኖሚ የፖለቲካ ሕይወት ህላዌው ቀጣይነት አለው፣ ምንም’ኳ የተለያየ ሃይማኖታዊ እምነት ያለን ቢሆንም ቅሉ ሁላችን ይላሉ ቅዱስነታቸው፣ እውነትን ለመሻት ፍትሕ ለመገንባት ዕርቅና መከባበር ለማረጋገጥ እንደ የአንዲት ቤተሰብ አባላት እርስ በእርስ ለመደጋፈና ለመተሳሰብ ተጠርተናል እንዳሉ አስታውቀዋል።

እነዚህ አበይት እሴቶች ለእነዚያ ግልጽነት የተካነው መስተዳድር የተሟላ ሰብአዊ እድገት የሁሉም በማሕበራዊ ሕይወት ሱታፌ የሚል መመዘኛ መሠረት ለሁሉም በዚያ ፈጣሪ በጸጋው ለሰጠው የአገር ሃብት የተስተካከለ ተጠቃሚነት ዋስትና ለማረጋገጥ ኃላፊነት ላላቸው አካላት እግብር ላይ እንዳያውሉ ይጠየቅባቸዋል፣ ዓለም አፍሪቃ የተስፋ ክፍለ ዓለም አድርጎ ነው የሚመለከታት፣ ኡጋንዳ በእውነቱ እግዚአብሔር በሕዝቧ በጽኑ ቤተሰቦቸዋ በወጣቶችዋና በአዛውንቷ ባጠቃላይ የአገሪቱ ዜጎች አማካኝነት ባርካታል፣ በመሆኑም ይኸንን እግዚአብሔር ያደላት ሃብት በሚገባ በመንከባከብና በማቀብ ለማስተዳደር የተጠራችሁ ናችሁ እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ በማያያዝ፦ ለወጣቱ ትውልድ ተገቢ ሕንጸት ተገቢ የደሞዝ ክፍያ ያለው ሥራ የማግኘት መብት ማስከበር በተለይ ደግሞ በማሕበራዊ ሕይወት ንቁና የተሟላ ሱታፌ እንዲኖረው ማድረግ ያስፈልጋል።

አዛውንት የአገር ዜጎች ቡራኬ ናቸው፣ የሕዝብ ተዘክሮ ያላቸው ጥበብና ገጠመኝ ብሶል ነውና ያለው ክቡር እንዲጠበቅ በማሳሰብ ኡጋንዳ ስደተኞችና ተፈናቃዮች በማስተናገዱ ተግባር የምትሰጠው አገልግሎት አመስግነው፣ የምንኖርበተ ዓለም በዚህ ተጠቅሞ መጣል በሚል መንፈሳውያን እሴቶችን በሚያዳክም የሰውን ልጅ ልብ የሚያደነድን ድኾችን የሚዘነጋ የወጣት ትውልድ ተስፋ የሚነጥቅ ባህል እጅግ እየተበከለ ባለው ዓለም ትብብር መደጋገፍ እንዲረጋገጥ አደራ እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አመለከቱ።

30/11/2015 15:54