2015-11-27 15:53:00

አባ ሎምባርዲ፦ ቅዱስ አባታችን በሐሴት ወደ አፍሪቃ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ኬንያ እ.ኤ.አ. ህዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በተነሱብት ወቅት በተሳፈሩበት አይሮፕላን ከተለያዩ ጋዜጠኞች ጋር በመገናኘት አጭር ንግግር ከማስደመጣቸው ቀደም በማድረግ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ቅዱስ አባታችን በሚሳተፉበት አይሮፕላን ለተገኙት ጋዜጠኞች አጭር መልእክት ለማስደመጥ ፈቃደኛ ሆነው በመገኘታቸው አመስግነው፣ ቅዱስ አባታችን ጧት ከአገረ ቫቲካን ቅዱስ ማርታ ሕንፃ ወደ አየር ማረፊያ ከመጓዛቸው ቀደም በማድረግ በቤተሰብ ውስጥ የተለያየ ዓመጽ የተደረሰባቸው፣ ላመንዝራነት ሕይወት ተዳርገው በአዲስ ባርነት ተግባሮች በስቃይ ውስጥ የነበሩት በአንድ መንፈሳዊ ማኅበር መጠለያ አግኝተው መንፈሳዊና ሰብአዊ ሕንጸት በማግኘት ላይ ካሉት በጠቅላላ 25 ሴቶች ጋር ተገናኝተዋል፣ በመቀጠልም የጎዳና ተዳዳሪዎችን በመዘዋወር ሰላምታን አቅርበዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሚሳፈሩበት አይሮፕላን ውስጥ የቫቲካን ረዲዮና የቫቲካን የቴሌቪዥን ጣቢያ ልኡካን ጋዜጠኞች የሚገኙባቸው በጠቃላላ 74 ጋዜጠኞች እንደሚገኙም አባ ሎምባርዲ ለቅዱስ አባታችን ከገለጡ በኋላ ቅዱስ አባታችን፦ አባ ሎምባርዲን አመስግነው ለሁሉም ልኡካን ጋዜጠኞች ሰላምታን አቅርበው አብሮአቸው ለመጓዝ በመገኘት በዚህ ጉዞ ሊሸኙዋቸው ፈቃደኞች ሆነው በገኘታቸው አመስግነው ከኬንያ ሕዝብ ጋር ለመገናኘት በሐሴት ወደ ኬንያ እንዲሁም በተመሳሳይ መልኩ ወደ ኡጋንዳ በመጨረሻም ወደ ማእከላዊት ረፓብሊክ አፍሪቃ እንደሚሄዱ ገልጠው በዚህ መርሃ ግብር እናንተ ጋዜጠኞች በምታከናውኑት አገልግሎት እግዚአብሔር ይደግፋችሁ፣ ብለው 74ቱን ጋዜጠኞች አንድ በአንድ ሰላም ካሉ በኋላ መልካም ጉዞ መመኘታቸው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ሊዛ ዜንጋሪኒ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።     








All the contents on this site are copyrighted ©.