2015-11-25 16:17:00

ዓውደ ተማሪዎች


ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት ዓውደ አሕዛብ በሚል መጠሪያ ያነቃቃው በአማንያንን ኢአማንንያን መካከል በተለያየ ሥነ ምርምርና ሥነ እውቀት ዘርፍ እምነትና ምርምር ርእስ ዙሪያ በማወያየት እምነት ምርምርን ምርምር ደግሞ እምነትን የሚያገል ሳይሆን ተሟይ መሆናቸው የሚያወያየው ዓውደ ጥናት መርሃ ግብር ሥር ይኸው እ.ኤ.አ. ህዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም. የ20ኛው ዘመን በተሰየመው ቤተ መዘክር የላቲን ቋንቋ መማር ያለው አስፈላጊነት የሚያበክር አመክንዮ ርእስ ዙሪያ የመከረ የተማሪዎች ዓውደ ጉባኤ መካሄዱ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አንቶነላ ፓለርሞ አስታወቁ።

የተማሪዎች ዓውደ ስያሜ ሥር በተካሄደው ዓውደ ጥናት የተሳተፉት ተማሪዎች የላቲን ቋንቋ መማር ለተማሪው የሚበጅ አእምሮን የሚያሰፋ አነጋገርን ሁሉ አመክንዮያዊ የሚያደርግ አስተዋይ በአምክንዮ በተካነው የንግግር ችሎታ የሚያሳድግ መሆኑ ማስተጋባታቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፓለርሞ አክለው የላቲን ቋንቋ እምሮን የሚያሰፋ መሆኑም እንደተሰመረበት ገልጠዋል።

የባህል ጉዳይ ተንከባክቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ በተካሄደ ዓውደ ጥናት ከተማሪዎች ጋር በመወያየትም የላቲን ቋንቋ አስፈላጊነት በሁሉም የታመነበት ሲሆን፣ ብፁዕነታቸው “የላቲን ቋንቋ መማር ገዛ እራስ ለመሆንና በተስተውሎ ገዛ እራስን ለማወቅ መቻል ማለት ነው ሲሉ አንቶኒዮ ግራምሺ ያሉትን ሃሳብ ጠቅሰው የላቲን ቋንቋ ለአእምሮ ልምምድና የምትናገረው ቋንቋ ጥልቅና አመክኒዮያዊ የሚያደርግ ነው፣ የአንድ አገር ሥነ ጽሑፍ የታሪክ ቅርስ ብርታት ቋንቋ ነው፣ የላቲን ቋንቋ ማወቅ ታላላቅ ደራሲያን የቲዮሎጊያ የተለያዩ የሥነ ምርምር ዘርፍ ሊቃውንት፣ ፈላስፋዎች ትተዉት ያለፈው የምርምር ጥናታቸውና ጽሑፋቸው ድርስቶቻቸውን በጥልቀት ለማወቅ የሚደግፍ ነው፣ ታሪክ መምህር ነው የሚባለውም አለ ምክንያት አይደለም፣ ስለዚህ ይኽ ደግሞ የመሆንና የኅልውና ምክንያት ለይቶ ለመረዳት ይደገፋል እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ፓለርሞ አስታወቁ።

በተካሄደው ዓውደ ጥናት የተሳተፉት የፍልስፍና ሊቅ ጁሊዮ ጂረሎ በበኵላቸውም የላቲን ቋንቋ ሌላው የማሳመን ብቃት የሚያጎለብት ብቻ ሳይሆን የነጻነት ቋንቋም ነው፣ የላቲን ቋንቋ የሥነ ምርምር አብዮት የከወነ ነው። በዚሁ ጉዳይ ሥር ጋሊለዮን፣ ኔውቶን በላቲን ቋንቋ የሚያስብ፣ ቶማስ ሆበስም፣ ዳንተና ሸክስፒር ጭምር በላቲን ቋንቋ ያስቡ እንደነበር ታሪክ ጠቀስ የሥነ ጥናት ውጤቶች በማስደገፍ ማብራራታቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፓለርሞ በማያያዝ በተካሄደው ዓውደ ጥናት ንግግር ያስደመጡት የሥነ ላቲን ቋንቋና ባህል ሊቅ ፕሮፈሰር ኢቫኖ ዲዮኒጂ ጭምር የቋንቋ ምኅዳር ያለው አስፈላጊነት በስፋት ማብራራታቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.