Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ሐዋርያዊ ጉዞዎችና ጉብኝቶች

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በኬንያ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በኬንያ - AFP

25/11/2015 16:12

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሦስት የአፍሪቃ አገሮች የሚያካሂዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት እ.ኤ.አ. ህዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ኬንያ ርእሰ ከተማ ናይሮቢ በመግባት የጀመሩ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ናይሮቢ እንደገቡም ከአገሪቱ ባለ ሥልጣናትና በአገሪቱ ከሚገኙት የተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት ጋር ተገናኘተው ባስደመጡት ንግግር

ክቡር ርእሰ ብሔር

የተከበራቸሁ የመንግሥትና የብሔር አባላት

የተወደዳችሁ ወንድሞች ብፁዓን ጳጳሳት

ክቡራንና ክቡራት

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪቃ ባሚያካሂዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት ለተደረገላቸው የሞቀ አቀባበልና መስተንግዶ ማመስገን ይገባኛል በማለት፣ ክቡር ርእሰ ብሔር በኬንያ ሕዝብ ስም ባስደመጡት ንግግር ስላሉት መልካም ቃል አመሰግናለሁ ብለው በሕዝቡ መካከል ለመገኘት አቢይ ጉጉት አለኝ ብለዋል።

ኬንያ ወጣትና ንቁ አገር ነች፣ በኅብረአዊነት ኃብታም የሆነ በክልሉ አቢይ ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ የሚሰጥ ማኅበርሰብ ያላት መሆንዋ የሚያረጋግጥ ነው። የኬንያው ዴሞክራሲያዊ ገጠመኝ በተለያዩ የአፍሪቃ አገሮች በተለያየ መልኩ የሚገለጥም ነው።  ኅብረአዊ ህብረተሰብ ለማቆም የሚያግዝ  እርስ በእርስ በመከባበር በውይይትና በመተባበር ላይ የጸና አንድ የተወሃደ ቅንና ሁሉንም የሚያቅፍ ኅብረተሰብ ለመገንባት የምትጥር አገር ነች።

አገራችሁ በወጣት የኅብረተሰብ ክፍል ሃብታም ነች፣ በቆይታየ ወቅትም ተስፋና መጻኢ የመጠባበቅ ያላቸው ጉጉት ለማበረታታት  ከሁሉም ጋር ለመገናኘትና ለመወያየት ፍላጎቱ አለኝ፣ ወጣት የአንዲት አገር እጹብ ድንቅ ሃብት ነው፣ ወጣቱን መከላከል፣ ለድጋፉም መዋዕለ ንዋይ ማቅረብ ጥበብ የተገባው መጻኢና ለእዚያ የሕዝብ ልብና ተዘክሮ ለሆነው አዛውንት የአገር ዜጋ አቢይ ክብር ያለው መንፈሳዊ እሴቶች ለበለጠው ዓለም ግንባታ ዋስትና ነው።

ቅዱስነታቸው ባስደመጡት ንግግር የኬንያ ተፈጥሮአዊ ሃብትና የተዋበው መልክዓ ምድራዊ ሃብቷን ጭምር ጠቅሰው የአገሪቱ ሕዝብ ይኽ ሃብት እግዚአብሔር የጸገወው መሆኑ በመታመን ሃብቱን በመንከባከብ አቅቦ ለመኖር የሚያደርገው ጥረት ተደናቂ የሚያደርገው ተግባር ነው። የአካባቢና የተፈጥሮ ቀውስ  በሰው ልጅና በተፈጥሮ መካከል ያለው ግኑኝነት አቢይ ጥንቃቄ እንደሚያሻው ምልከት ነው። የተፈጥሮው ውበት በሙላት ለመጻኢ ትውልድ የማስተላለፍና የተቀበልነው ጸጋ በቅንነት የማስተዳደር ኃላፊነት አለብን። ይኽ ደግሞ በአፍሪቃ መንፈስ በጥልቅነት የጸና እሴት ነው። በዚህ በአሁኑ ወቅት ያንን የማኅበራዊ ቤት የሆነውን መሬት ከመከላከል ይልቅ የሚበዘብዘው ዓለም መንግስታት ኃላፊነት የተካነው የኤኮኖሚ ልማት አርእያ የሆነውን እንዲያነቃቁ አስተንፍሶ ነው።

ቅዱስ አባታችን በመቀጠልም ይሴባሕ በሚል ርእስ ሥር በደረሱት ዓዋዲ መልእክት ቁጥር 118 ያለውን ሃሳብ ጠቅሰው ተፈጥሮ መንከባከብና አንድ ቅንና እኩልነት ላይ የጸና ማኅበራዊ ሥርዓት መገንባት ተያይዘው እንደሚሄዱና፣ ከተፈጥሮ ጋር ላለን ግኑኝነት ኅዳሴ ካለ አንድ የታደሰ ሰባአዊነት መከወን አይቻልም።

ጎሳዊ ሃይማኖታዊ ብሎም ኤኮኖሚያዊ መከፋፈል ኅብረተሰባችን የሚኖሩት ገጠመኝ ነው፣ ስለዚህ ሁሉም ሰው መልካም ፈቃድ ያለው ሁሉ ለእርቅና ለሰላም ለምህረትና ለልብ ፈውስ እንዲተጋ ተጠርተዋል። የአንድ ጽኑ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ጽናት ማኅብራዊ ውህደትና የተሟላ ህብረተሰብ መከባበርና መደጋገፍ እንዲታይበትም ለጋራ ጥቅም ትጋት ተቀዳሚ ግብ መሆን አለበት። ድኽነትና ጭንቀት በውስጡ የሚደብቀው ግጭት ዓመጽ ውጥረት አሸባሪነት በፍርሃት ባለ መተማመን በቀቢጸ ተስፋነት ይባባሳል ያሉት ቅዱስ አባታችን አክለው፣ ከእነዚህ የሰላምና መጻኢ ላይ ለሚያተኮር መንፈስ ጠላት የሆኑት ተግባሮች አለ ምንም ፍርሃት በእነዚያ ለአንድ አገር አስተንፍሶ በሆኑትና በሚመሰከረው በአበይት መንፈሳውያን ፖሊቲካውያን እሴቶች ላይ በመታመን የሚታገሉ ወንዶችና ሴቶች እንዳሉም ገልጠዋል።

ክብራትና ክቡራን እነዚህ አበይት እሴቶች የማነቃቃቱና የማጽናቱ ኃላፊነት ለየት ባለ መልኩ ለእናንተ የአገር የፖለቲካ የባህል የኤኮኖሚ ሕይወት ለመምራት ለተጠራችሁ የተሰጠ ነው። ይኽ በእውነቱ አቢይ ኃላፊነት ነው። ጥሪያችሁ ያንን የኬንያ ሕዝብ ማገልገል ነው። ወንጌል ያ ብዙ የተሰጠው ብዙ እንደሚፈለግበትም ያረጋግጥልናል (ሉቃ. ምዕ. 12, 48)። በዚህ መንፈስ በሙላትና በግልጽነት ለጋራ ጥቅምና በህሉም የማኅበራዊ ደረጃ መተባበር እንዲኖር ታገለግሉ ዘንድ አበረታታችኋለሁ … አደራ ድሆች ለሚያፈልጋቸው ሁሉ አንድ ቅን አሳቢ መንፈስ ለወጣት ትውልድ ምኞት ላንድ ቅንና የተፈጥሮ ሃብት ለተስተካከለ ክፍፍል የሚል አግልግሎት እንዲኖራችሁ እማጸናለሁ … የካቶሊክ ማኅበረሰብም በሕንጸት በግብረ ሠናይና የሚሰጠው አገልግሎት አረጋግጥላችኋለሁ።

እዚህ ኬንያ እንደደርሱም የአገሪት ወጣት ትውልድ መጻኢ ትውልድ እንዲኖር የፍርያማነት ትእምርት የሆነው ዛፍ የመትከል ልማድ እንዳለው የተነገራቸውን አስታውሰው በእውነቱ እጹብ የተስፋ ምልክት ነው፣ ይኽ ተግባር እግዚአብሔር በሚሰጠው የእድገት ጸጋ እማኔ እንዲኖራችሁ ቅን ጽኑ ሰላም የተካነው ኅብረተሰብ በአገራችሁና በመላ ታልቁ የአፍሪቃ ክፍለ ዓለም ለምታደርጉት ጥረት ድጋፌ እንደማይለያችሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።

ላደረጋችሁልኝ የሞቀው ልባዊ አቀባበል ደግሜ አመሰግናለሁ፣ በእናንት ላይ በቤተሰቦቻችሁ በጠቅላላ በመላ የኬንያ ሕዝብ ላይ የጌታ ቡራኬ እማጠናለሁ።

ሙንጉ አባሪኪ ከንያ

እግዚአብሔር ኬንያን ይባርክ።

25/11/2015 16:12