2015-11-23 18:08:00

በተለያዩ ችግሮች ቆስላ በምትገኘው ዓለማችን የምሕረት ተግባር ያስፈልጋታል! ር.ሊ.ጳ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡ ምእመናንና ነጋድያን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕለቱ ቃለ ወንጌል በመመርኰዝ “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሥ ነው! ይህ ንግሥነት ግን የዚህ ዓለም አስተሳሰብ የሚቀበለው ሳይሆን ሰማያዊ ንግሥነት ነው ይህም ሁሉ ነገር አበቃለት በሚባልበት ጊዜ የሚገለጥ ከሃሌ ኵሉነት ነው፣ ጌታ ኢየሱስ ንግሥነቱን የተገለጠው የሽንፍት ምልክት በሆነው በመስቀል ነው፣” ሲሉ የክርስቶስ ንጉሥ በዓልን በሚመለከት ካስተማሩ በኋላ በዚሁ ሳምንት ሊያደርጉት በመጠባበቅ ላይ የምንገኘው የአፍሪቃ ሓውጾተ ኖልዎ አመልክተውም “የፍቅር ተጨባጭ ምልክት” ሲሉ ገልጠውታል፣

በዚሁ የኢየሱስ ንጉሥ በዓል በሚከበርበት እሁድ ቅዱስነታቸው አዲስ የሰላምና የዕርቅ አንገብጋቢ ጥሪ በማቅረብ ነው የዘከሩት፣ ይህንን ደግሞ በእመቤታችን ድንግል ማርያም በመማጠንና ሁሉ ባለበጎ ፈቃድ ሰዎች ለጥላቻና ለዓመጽ እምቢ እንዲሉ ጥሪ በማቅረብ ነው፣

“እንዲህ ባሉ ዓለምን በሚያቅዩ ሁኔታዎችና በሰው ልጆች ሥጋ ባጋጠሙ ቁስሎች ፊት እመቤታችን ድንግል ማርያም ኢየሱስ ክርሶትስን ለመምሰል በምናደርገው ትግል እንድትረዳን ዘን እንለምናት መንግሥቱ በመካከላችን እንዲሆን በምናደርገው የርኅራኄ የመረዳዳትና የምሕረት ተግባር እንድትረዳን ዘንድ እንለምናት” ብለውም ጸሎት አሳርገዋል፣

ላሉና ለሞቱት በእውነት የሚፈርድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዐርብ በውሸታም መኳንንቶች ፊት ቀርቦ በተከሰሰበት ወቅት ጲላጦስ ግራ ገብቶት አንተ ንጉሥ ነህን ብሎ በጠየቀው ወቅት ንጉሥ መሆኑን እንደመሰከረ ነገር ግን ይህ ንግሥነት እኛ በምናስበውና በምንረዳው መንገድ ሳይሆን በመንፈሳዊ መልክ ስለሆነ ንግሥነቱን የመከላከል መንገድ እንደሚለያይ የገለጹ ቅዱስነታቸው፤ የዚሁ ዓለም ንግሥነት የፍርሃት መሳርያ ስለሚጠቀም ሙስናና የኅሊና መዋዠቅ ሲከተል የወንጌሉ ንግሥነት ግን በትሕትና እና በነጻ ስጦታ እንደሚመሠረት ይህም አለምንም ድምጽ እንደሚያደረግ ሆኖም ግን የእውነት ኃይል በዚህ እንደሚግለጥ ገልጠዋል፣ በተቀራናዊ መንገድ የዚህ ዓለም መንግሥታት በውድድር በጭቆና እና በእብሪተኝነት እንደሚረጋገጡ የክርስቶስ መንግሥት ግን የፍትሕ የፍቅርና የሰላም መንግሥት ስለሆነ ይህንን ዝንባሌ እንደማይቀበል አመልክተዋል፣

የኢየሱስ ክርስቶስ ንግሥነት በመስቀል እንደተገለጠ ያስተማሩ ቅዱስነታቸው መስቀልን በእውነት የሚመለከት ሁሉ የጌታ ነጻ ፍቅርን ለመርዳት አይዳግተውም ብለዋል፣ ነገር ግን ይላሉ ቅዱስነታቸው! ነገር ግን ይህ የመሸነፍ የውድቀት ምልክት የሆነው ነገረ መስቀል ኃጢአት እንዳሸነፈ የሰው ልጆች መጥፎ ፍላጎት እንደገፋ ቢያመልከትም ሁሌ ድላችን በመስቀል ነው ሲሉ የመስቀል ጉዳይ ሽንፈትና ችግር ቢያመለክትም የክርስትያን ድል በመስቀል ብቻ ነው፣ ይህም በትሕትና ለማለት ነው ብለዋል፣

አያይዘውም ለክርስትያን ችሎታና ኃይል ምን መሆኑን ለመግለጥ ደግሞ “ሁሉ ነገር በጌታ ኢየሱስ መስቀል እንደሚተረጐምና እንደሚነበብ መዘንጋት የለብንም” ሲሉ የጌታ ኢየሱስ ፍቅር በመስቀል እንደሚገለጠና በዚህም ጽናትና እምነት እንደሚያስፈልግ ከሁሉም ነገር በላይ ደግሞ ትህትና እንደሚያስፈግም ገልጠዋል፣ ክርስቶስ ንጉሥ ነው ነገር ግን በፍቅር የሚያገለግል ንጉሥ እንጂ የሚገዛና የሚጨቁን ንጉሥ አለመሆኑን መረዳት እንደሚያስፈልግም ገልጠዋል፣

የደህንነት ጉዳይ ሁሌ የጋራ ጉዳይ አድርገን በመመልከት ጌታ ኢየሱስ ዓለምን ለመዳን ሕይወቱን ሰጠ ለማለት እንችላለን! እውነቱም እንደዛ ነው! ነገር ግን እያንዳንዳችን ጌታ ኢየሱስ ሕይወቱን ስለኔ ሰጠ ብለን ማመን አለብን፣ በዛሬው ዕለት አሁኑኑ በዚሁ አደባባይ የምትገኙ ሁላችሁ “ጌታ ኢየሱስ ሕይወቱን ለኔ ሰጠ፣ ብላችሁ እንድትመሰክሩ እወዳለሁ” ሁላችን በኅብረት ጌታ ኢየሱስ ሕይወቱን ለኔ ሰጠ እያንዳንዳችንን ከኃጢአቶቻችን ነጻ ሊያወጣን ሕይወቱን ሰጠ፣ የኢየሱስ መንግሥት ኃይል ማለትም ፍቅሩን እንደገና መረዳትም ይህ ነው ስለሆነም የኢየሱስ ንግሥትነት ከድክመታችንና ኃጢአታችን ነጻ ያደርገናል እንጂ አይጨቍነንም፣ ለዚህም የመልካሙ ሌባ ምሳሌ ማየት በቂ ነው! በዛች ግዜ “ጌታ ሆይ በመንግሥትህ አስታውሰኝ አለው ጌታም ከእርሱ ጋር በመንግሥቱ እንደሚኖር አረጋገጠለት፣ እስቲ ሁላችን በኅብረት ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ እንበል ሲሉ ከተማጠኑ በኋላ በአደባባዩ የነበሩ ሁላቸው “ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ በኅበረት ደግመዋል፣

የመል አከ እግዚአብሔር ከደገሙ በኋላም በባርሰሎና ስለተካሄደው የፈደሪኮ ዘበርጋ እና 25 ጓደኞቹ በእስፓኛ ያቀረቡት የመስዋዕትነት ምስክርነትና በትናንትናው ስለታወጀው ብፅዕናቸው አስመልክተው ገና ዛሬም በዘመናችን ስለሚካሄደው የወንድሞቻችንና እኅቶቻችን የሰማዕትነት ምስክርነት እንዲሁም በክርስቶስ ባላቸው እምነት ስለሚሰደዱ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን እንድንጸልይ አሳስበዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.