2015-11-23 16:30:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የትምህርት ዕድል ለሁሉም፣ ለያይ ግንብ ማቆም ውድቀት ነው


ካቶሊካዊ የማንነት መለያ ጥያቄ እንጂ የግጭት መንስኤ አይደለም በሚል መርህ ቃል ሥር ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሥነ ሕንጸት ርእስ ሥር የደነገገው ውሳኔ ዝክረ 50ኛው ዓመትና እንዲሁም ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ Ex Corde Ecclesiae - ከቤተ ክርስቲያን ልብ በሚል ርእስ ሥር ለካቶሊካውያን መናብርተ ጥበብ ተቋሞችና ትምህርት ቤቶች የሰጡት የመመሪያ ውሳኔ ዝክረ 25ኛው ዓመት ምክንያት ከ 62 አገሮች የተወጣጡ 149 ልኡካን ያሳተፈ ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከህዳር 18 ቀን እስከ ህዳር 21 ቀን 2015 ዓ.ም. መካሄዱ ሲገለጥ፣ ይኽ ዓውደ ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተገባእያኑን ተቀብለው በለገሱት ሥልጣናዊ መርሕ ቃል መጠናቀቁ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አመለከቱ።

ክርስቲያናዊ እምነት በቃልና በተግባር በሚመሰክር ሕይወት ማነጽ እንጂ ሌላው ሃይማኖቱን እንዲክድ መወትወት ማለት አይደለም

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚህ ኅብረአዊነት በሚኖርበት ዓለም ይዞታና በተለይ ደግሞ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሕዳጣን በሆነችበት ክልል የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ምንና እንዴት መገለጥ አለበት የሚል ከተጋባእያኑ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ አለ ሰብአዊነት ካቶሊካዊ ሕንጸት ብሎ ነገር የለም፣ ምክንያቱም ካቶሊካዊ መለያ ትስብእተ ዘእግዚአነ ነው። ስለዚህ በክርስትያናዊ መንፈስ ማነጽ ማለት ትምህርተ ክርስቶስ ብቻ ማቅረብ ወይንም በአቢያተ ትምህርት ካቶሊክ ያልሆነውን ሃይማኖቱን ለማስካድና ካቶሊክ እንዲሆን የሚወተውት ስልት መከተል ማለት ሳይሆን ሕጻናት ወጣቱ ትውልድ በሁሉም ተጨባጭ ሕይወት ሰብአውያን እሴቶች ለመኖር እንዲችሉ በሰብአዊነት ማነጽ ማለት ነው።

ሕንጸት ልብን ለጌታ መክፈት፣ ለንገሮች ማዳ ወደ ሆነው ማቅናት

በአሁኑ ወቅት የሕንጸት ቀጥተኛው ዓላማ እውን በሆነ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው። ይኽ አዲሰ አወንታዊ ፕላቶናዊነት የሚያንጸባርቅ የሕንጸት ስልት ያንን  ከነገር ማዶ የሆነው ምንጣቄ የሚዘነጋ ሆኖ ነው የሚታየው፣ ስለዚህ አቢይ የሕንጸት ቀውስ ለምንጣቄ ገዛ እራስ መዝጋት የሚል ነው። በኑባሬ በሰው ዘንድ ያለው ወደ ላይ የማቅናት ባህርይ የሚያከብር ሕንጸት እንጂ በምድራዊነት ላይ ያተኰረ ሕንጸት ምሉእነት የለውም፣ በመሆኑም ካቶሊካዊ ሕንጸት የተሟላ መሆን አለበት እንዳሉ ጂሶቲ ገለጡ።

ሃብታሙን ከድኻው የሚያገል ሕንጸት ማስወገድ

በቤተሰብና በትምህርት ቤት መካከል ስላለው ግኑኝነት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ቅዱስ አባታችን ሲመልሱ፦ ሕንጸት ትምህርት የማቅረቡ ስልት ለይ ለምርጦች የሚል ድኻው ከሃብታሙ ሃብታሙም ከድኻው የሚለይና ትምህርት የማግኘት ሰብአዊ መብትና ክብር ለተወሰኑ ምርጦች ሆኖ ይታያል፣ ይኽ አይነቱ የተዛባው ሕንጸት ማስተካከልና ትምህርት የማግኘት ሰብአዊ መብትና ክብር ለሁሉም መሆኑ የሚገልጥና የሚኖር ካቶሊካዊ ሕንጸት ያስፈልጋል፣ በአሁኑ ወቅት ሕንጸትና ቤተሰብ መካከል ያለው መራራቅ ማስወገድ ያስፈልጋል እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው፦

ሥርዓተኝነት እደ ጥበባዊነት ብቻ ከሚለው ሕንጸት መቆጠብ

በአሁኑ ወቅት ለአስተማሪ የሚከፈለው ደሞዝ በጣም ዝቅተኛ ነው ይኽ ሁነት መንግሥትና የፖለቲካው ዓለም ለትምህርት ግድ ያማይል መሆኑ ይመሰክራል፣ ሕንጸት ሲዛባና የተሟላ ሳይሆን ሲቀር ጥራት የሌለው ሆኖ የሕንጸት ዓላማ የማያንጽ ሆኖ ይቀራል። ቅዱስ ዶምቦስኮ በዚያ ትምህርት ለምርጦች በሚባልበት ዘመን ለተናቁት ለተነጠሉት በከተሞችና በህልውና ጥጋ ጥግ ለሚገኙት ሁሉ በማቅረብ በተግባር ተቃውሞታል፣ በመሆኑም ዓለም የተላመደው ሥርዓተኝነትና እደ ጥበባዊነት ብቻ የሚለው ሕንጸት ላደጋ የሚያጋልጥ ሰማእነት የተካነ ሕንጸት እጅግ አስፈላጊ ነው እንዳሉ አስታውቀዋል።

ሕንጸት ማንም የማይነጥል ለሁሉም

ሕንጸት የሚታነጸው ሰው የማያካትት መሆን የለበትም፣ የሚታነጸው ሰው ስሜት ፍላጎት ዝምባሌ የማያገል መሆን አለበት፣ የሚታነጸው ለሚሰጠው ሕንጸት ተወናያን መሆን አለበት፣ በሌላው ረገድ ደግሞ የግል ትምህርት ቤቶች ለምርጦች ለሃብታሞች ብቻ ሆነው ብቃት ያለው ትምህርት መመዘኝው የገዘንብ ሃብት መሆን የለበትም፣ ጥራት ያለው ትምህርት የሁሉም መብት ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን አያይዘው፦

ወደ ኅልውና ጥጋ ጥግ ማቅናት

እርዳታ ለማቅረብ ዓልሞ ወደ የከቶሞችና የህልውና ጥጋ ጥግ የመሄዱ ተግባር በዚህ ክልል ሆኖ የዚያ ክልል ሰው ሕይወት አብሮ በመኖር መሟላት ይኖርበታል፣ በቃልና በሕይወት ማነጽ ያስፈልጋል፣ ስለዚህ ሕንጸት ይኸንን መንገድ የሚከተል መሆን አለበት እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አመለከቱ።

ለያይ ግንብ መገንባት የአንድ አስተማሪ ውድቀትን ያመለክታል

ለያይና ምርጦች የሚል ቃል የሚተገብር የሕንጸት ዘይቤ፣ የሚጋረጥ ይኸንን ተግዳሮት ለመቅረፍ ሌላውን የሚያካትት ገዛ እራስ ክፍት ለማድረግ የሚያግዝ የሕንጸት ሥልት አስፈላጊ ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን፣ ገዛ እራስ ለመከላከል ሌላውን ለመነጠል ገዛ እራስ በብቃት ለመከላከል ተብሎ የሚገነባው ግንብ የውድቀትና ምልክትና ገዛ እራስ ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ ተግባር ነው። በታጠረው ግንብ ውስጥ ማነጽ ለምርጦች ብቻ የሚል ሕንጸት ያለ መረጋጋት ባህል የሚያስፋፋ ነው። ስለዚህ ማኅበራዊ ምርጠታዊነት ባይ ባህል የሚያስወግድ የተሟላ ሕንጸተ ያስፈልጋል በማለት ያስደመጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን ማጠቃለላቸው ጂሶቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.