2015-11-18 16:15:00

ብፁዕ ካርዲናል ትርኩሶን፦ አማዞን ለየት ያለ መጻኢ ይገባዋል


ምድር የጋራ ቤት ነች በመሆኑም በማንኛውም የምኅዳር ብከላ አማካኝነት ለአደጋ ማጋለጥ አይገባም፣ ስለዚህ አደጋ ሲባል፣ የተፈጥሮ አየር ብከላ አመጽ ግጭት የሰው ልጅ ለሞት የመዳረጉ ጸረ ሰብአዊ ተግባርና ክልሎች፣ አካባቢዎች ታሪካዊ ቅርሶችና ታሪካዊ ክልሎች ባጠቃላይ ምኅዳር ማውደም የሚለው ጸረ ምኅዳርና ጸረ ኅያዋን ተግባር የሚያጠቃልል መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይሴባሕ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት በጥልቀት እንደሚያብራራው ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶም እ.ኤ.አ. ህዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም. በኮሎምቢያ ርእሰ ከተማ ቦጎታ በተከፈተው ረፓም የተሰየመው  የመላ አማዞን ክልል ቤተ ክርስቲያናዊ ድረ የተሰየመው ማኅበር በከፈተው ዓውደ ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር እንዳሰመሩበት በኰሎምቢያ ከምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተላለፈ መግለጫ ይጠቁማል።

በፓሪስ የተጣለው የሽበራ ጥቃት አስነዋሪና ጸረ ሰብአዊ ተግባር ነው

የፍትህና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን የመላ አማዞን ክልል ቤተ ክርስቲያናዊ ማኅበር የጠራው ዓውደ ጉባኤ በንግግር ሲከፍቱ ባሰሙት ንግግር የመላ አማዞን ክልል ምኅዳርና ማኅበራዊ ነክ የሆኑትን ርእሰ ጉዳዮች ላይ በማተኮርና ባሻገርም በፓሪስ የተጣለው ያሸባሪያን ጥቃት በበርይሩት ባግዳድ እንዲሁም በሶሪያ ያለው ግጭት ሁሉን በማስታወስ ይኽ ጸረ ፍጥረትና ተፈጥሮ ድርጊትም ሥልጣኔዎችና የምንኖርባት ምድር የሚጎዳ ነው። ማንኛውም ዓይነት ተፈጥሮና ፍጥረት ሁሉ ለአደጋ የሚያጋልጥ ተግባር መቃወምና እንዳይከሰት ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት ነው እንዳሉ በኰሎምቢያ ከምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተሰራጨው መግለጫ ያመለክታል።

አማዞን ለየት ያለ መጻኢ ይገባዋል

ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን ባስደመጡት ንግግር፦ የምንኖርበት ዓለም እጅግ ሰፊና ጥልቅ ተግዳሮት የተሞላው መሆኑ በማብራራት፣ ሕዝቦች እነዚህን ኅብረ ተግዳሮች ገጥሞ በመቅረፍ ምኅዳርና ኅያዋን ለማቀብ ጥረት ያደርጋሉ፣ በዚህ በአሁኑ ወቅት ጭለማ በተሞላው ዓለም ኤውሮጳ ለአደጋ ተጋልጣ ባለችበት በአሁኑ ወቅት አካባቢና ተፈጥሮ ጭምር ለስጋት ተጋልጦ ባለበት በአሁኑ ወቅት ይኽ ቤተ ክርስቲያናዊ የመላ አማዞን ክልል ማኅበር ተፈጥሮ ለመንከባከብ እያከናወነው ያለው ጥረት ተፈጥሮና ፍጥረት በማክበር ለመኖር አብነት ነው እንዳሉ የገለጠው በኮሎምቢያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መግለጫ አክሎ፣ አማዞን ለየት ላለ መጻኢ የተገባ ነው። ቅድስት መንበር ይኽ አማዞናዊ ማኅበር የሚያቀርባቸው እቅዶች በማጤን የዚያ ክልል ነዋሪ ሕዝብ መብትና ክብር እንጠበቅ ጥሪ በማቅረብ ለሰብአዊና ለምኅዳር ጤንነት አበክራ እንደምታገለግል ማረጋገጣቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.