2015-11-18 16:18:00

ብፁዕ አቡነ ዚሞውስኪ፦ አዲስ የልብ ምኅዳር መከላከል


ምሉእ የሰው ልጅ የሕይወት ሂደት የሚያከብር የታደሰ ጥረት አስፈላጊ ነው የሚል ሃሳብ የዚያ የጤናና የጤና ጥበቃ ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት “የጤና እንክብካቤ ባህልና ሰውና ተፈጥሮን የማገልገል ባህል” በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ከሕዳር 19 ቀን እስከ ሕዳር 21 ቀን 2015  እንዲመክር የጠራው 30ኛው ዓለም አቀፍ ዓውደ ጉባኤ ከሚያስተጋባቸው ሃሳቦች ውስጥ አንዱ መሆኑ ሊካሄድ ስለ ተጠራው ዓውደ ጉባኤ በማስመልከት ጳጳሳዊ የጤናና የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዝይግሙንት ዚሞውስኪና የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ኣቡነ ዣን ማሪየ ማተ ሙሲቪ ሙፐንዳዋቱና ምክትል ዋና ጸሓፊ አባ አውጉስቶ ከንዲ፣ የኢጣሊያ ያካባቢ ፈውስና ጤንነት የተሰየመው ማኅበር ሊቀ መንበር አንቶኒዮ ማሪያ ፓሹቲና በአርጀንቲና የምኅዳር ሕክምና ጥበቃ ማኅበር ሊቀ መንበር ሊሊያን ኮራ በጋራ በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራስ ተገኝተው ስለ ተጠራው 30ኛው ዓውደ ጉባኤ ርእሰ ጉዳይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መገለጡ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ አስታወቁ።

የዓውደ ጉባኤው ርእስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በመደጋገም የሚያሳስቡት ማስተናገድ የሚለው ቃል ያጠቃለለ ነው። መስተግዶ ሌላውን የመቀበል ተግባር እጅግ አስፈላጊ ነው፣ ድኻውን ማስተናገድ ለብቻቸው የተተዉትን ህሙማንን ማስተናገድ፣ ጉልበትን አጥፎ ጎንበስ ብሎ የወደቀውን ድኻው የታመመው ለብቻው የተተወው ማንሳት ለተሰጠንና ለሚሰጠን ምኅረት ትእምንርት ነው። ይኽ ደግሞ የሕክምና ባለ ሙያ የሚኖረው መሆን አለበት ያሉት ብፁዕ አቡነ ዚሞውስኪ አክለው፦ የዓውደ ጉባኤው ዳራውም የቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ “ወንጌላዊ ሕይወት” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት የሚያቀርበው ሥልጣናዊ ትምህርት  እንደሚሆን ማብራራታቸውም አኵይላኒ አስታወቁ።

በመቀጠልም አንቶኒዮ ማሪያ ፓሹቲ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ባስደመጡት ንግግር፦ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ በሽታዎች ከተፈጥሮ ብከላ ጋር ግኑኝነት ያላቸውና እንዳውም መንስኤው ያካባቢ ተፈጥሮ ብከላ መሆኑ በተለያዩ አገሮች በብሔራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከናወኑት የሥነ ሕክምና ምርምር ያስገኙት ውጤቶች ያረጋግጣል ሲሉ ሊሊያን ኮራ በበኩላቸውም የውኃ ሃብት ብከላ በተለያየ በሽታ ከዚህ ዓለም በሞት ከሚለየው ውስጥ 25% እንዲሁም ከአስራ አራት ዓመት እድሜ በታች ከሆኑት ውስጥ 36% ከዚህ ዓለም በሞት ለሚለየው ምክንያት ነው እንዳሉ ጃዳ አኵይላኒ ገልጠው የሚካሄደው ዓውደ ጉባኤ ጤንነትና ምኅዳር መካከል ያለው ግኑኝነት በጥልቀት ትንተናና በተለይ ደግሞ በስነ ምርምር የተረጋገጡት መረጃዎች በተለያየ መልኩ እንደሚያብራራ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ንግግር ያስደመጡት አካላት እንዳሰመሩበት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.