2015-11-16 16:25:00

አባ ሎምባርዲ፦ የምኅረት ዓመት የማይሸጋገር ውሳኔ ነው


በዓለም በተለይ ደግሞ በፓሪስ አሸባሪያ የከወኑት አሰቃቂው የሽበራ ጥቃት ግምት በመስጠት እንዲህ ባለ የጥላቻ መንፈስ እጅግ ቀጣይ በሆነ መንገድ በሚግለጥበት ባለው በአውሁኑ ወቅት የኢዮበሊዮ ቅዱስ የምኅረት ዓመት ማሸጋገር የሚሻል መሆኑ የሚሰጠው አስተያየት በማስመልከት፣ የቅድስት መንበር የዜና ኅትመት ክፍል ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ቅዱስ ዓመት ማሸጋገር የማይቻል ብቻ ሳይሆን፣ የቅዱሱ ዓመት ጥልቅ ትርጉሙ በማብራራትም ማሸጋገሩም ከመልእክቱ ጋር የማይዛመድ ሃሳብ ነው። ቅዱስ ዓመት መልእክቱም ምህረት ነው። ፍርሃትን የሚቃወም የሚጻረር ምህረት። ፍርሃት ጥላቻ ቂም በቀል ሁሉ የሚቃወም ተግባር መሆኑ ገልጠው፣ በፓሪስ የብዙ ሰው ሕይወት ለሞትና ለመቁሰል አደጋ የዳረገው ከተጣለው አሰቃቂው የሽበራ ጥቃት ምክንያትም በቅርቡ የሚጀመረው ቅዱስ የምኅረት ዓመት ማሸጋገሩ ለፍርሃት እጅ መስጠትና ምኅረት የሚለው ቃል ያለው ትርጉም ያለ መረዳት ይሆናል። የጥላቻ መንፈስ ያደረበት የግድያ ተግባር በእውነት ትርጉም የለሽ፣ ትርጉም ሊኖርው የማይቻል ጸረ ሰብአዊ ተግባር ነው። ለዚህም ነው የሽበራ ተግባር የሚባለው፣ ሌላውን ማስፈራራት፣ ሰላም መንሳት ዕለታዊ ኑሮ በፍርሃት የተሞላ ማድረግ። ይክ ደግሞ ያሸባሪያኑ ተቀዳሚ ዓላማ ነው። እንዲህ ባለ ተግባር ፊት የምኅረት ዓመት እንዲቆይ ማድረጉ የዚያ የሽበራው ጥቃት ሰለባ መሆን ማለት ነው። ስለዚህ ያንን ጸረ ሰብኣዊ ተግባር የሚቃወም ቅዱስ ዓመት ነው ብለዋል።

እርግጥ ነው ጥንቃቄና ጥንቁቅነት ያሰፈልጋል፣ ኃላፊነት በተካነው መንገድ መመራት፣ አምክንዮ የተካኑ ውሳኔዎች ማረጋገጥ ያስፈልጋል፣ መኖር ቀጣይ ነው፣ ሰለዚህ መኖር አለብን፣ ሰላምና የእርስ በእርስ መተማመን ግንባታ መቀጠል ይኖርበታል፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እርስ በእርስ በመፈቃቀር የሚገለጥና የሚኖር ነው። ስለዚህ ይኽ ደግሞ ፍርሃት ጥላቻና መራራቅ ለሚዘራው መንፈስ የሚቃወም መንገድ ነው። እግዚአብሔርን ማፍቅር ለሰው ልጅ ሕይወት ጠላት መሆን የማጣጣም ትጋጭ መንገድ ነው።

ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ፦ የምኅረት መልእክት ለዚያ ድንግዝግዝና ጨለማ በተሞላው አስጨናቂው የጦርነትና የጥላቻ መንፈስ በተከናነበበት ወቅት ይኖር ለነበረው ሕዝብ የተላለፈ ነው በማለት የገለጡት ሃሳብ እውነት ነው። ዛሬም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እየተገማመሰ የሚፈጸም ሦስተኛው የዓለም ጦርነት በማለት የሚገልጡት በዓለም እየታየ ያለው ግጭትና የጥላቻ መንፈስ እየተስፋፋ ባለበት ወቅት ያ የምኅረት መልእክት እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በመሆኑም የምኅረት ዓመት ይቆይ ማለቱና ማሸጋገሩ በእውነቱ ተገቢ እንዳልሆነ ያብራሩት አባ ሎምባርዲ አያይዘው፣ የምኅረት ዓመት በጥበብ በጥንቃቄ በብርታትና እጅግ በላቀ መንፈሳዊነት መኖር ይገባል፣ ምንም’ኳ ጥላቻና ግጭት ቢታይም በተስፋ ወደ ፊት ማለት ያስፈልጋል፣ በዚህ ጎዳናም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይመሩናል በማለት የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.