2015-11-16 16:29:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በእያንዳንዱ ስደተኛ የማይሻረው ውሉደ እግዚአብሔር የመሆን ክብር አለ


በእያንዳንዱ ስደተኛ ውስጥ ያ የማይሻረው የእግዚአብሔር ልጅ የመሆን ክብር አለ። የሚል ቅዉም ሃሳብ ማእከል ያደረገ መልእክት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የዛሬ 35 ዓመት በፊት ለተቋቋመው የኢየሱሳውያን ማኅበር የስደተኞችና ተፈናቃዮች አገልግሎት ማእከል አባላት እ.ኤ.አ. ህዳር 13 ቀን 2015 ዓ.ም. አገረ ቫቲካን በሚገኘው ቀለመንጦስ የጉባኤ ኣዳርሽ ተቀብለው ማስደመጣቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ በማያያዝ፦ ይኽ የአገልግሎት ተቋም ለተፈናቃዮችና ስደተኞች የተሟላ አገልግሎት የሚያቀርብ መሆኑም ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን ይኽ ሰብአዊ አገልግሎት የሰው ልጅ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ ያለው ክብሩ እውቅና የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ የሚመሰክር ነው እንዳሉ ይጠቁማል።

ስደተኛው በአኃዛዊ መግለጫ ሥር የሚገለጥ ቁጥር ሳይሆን ክብር ለበስ ሰው ነው

በአሁኑ ወቅት ከተለያየ ችግር ገዛ እራሱ ለማዳን የሚሰደደው ሁሉ ፈልጎ ሳይሆን ተገዶ ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን በተባበሩት መንግሥታት ሥር በአሁኑ ወቅት 60 ሚሊዮን  ስደተኛ መኖሩ የሚገልጥ የተሰጠው አኃዛዊ መግለጫ በማስታወስ ለኢየሱሳውያን የስደተኞችና የተፈናቃዮች ማአክል ባስተላለፉት መግለጫ ሥፍር ቁጥር የሌለው የስደተኞች ጸዓት ከመካከለኛው ምስራቅ ከአፍሪቃና ከእስያ ወደ ኤውሮጳ የሚገባው ብዛት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ወዲህ ያልታየ ጸዓት መሆኑ ገልጠው ስደተኛ በአኃዝ የሚገለጥ ቁጥር ሳይሆን ክብር ለበስ ሰው ነው ብለዋል።

የኢየሱሳውያን የስደተኞችና ተፈናቃዮች መርጃ ማእከል 45 የተለያዩ ውጥኖች አማካኝነት የተሟላ ድገፍ የሚያቀርብ መሆኑ ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን፣ ቀርቦ መሸኘት ማገልገልና ለስደተኛው መብትና ክብር ተሟጋችነት የሚል መሆኑም ገልጠው በዚህ መልኩም የተሟላ በሚሰዋ ፍቅር አብነት ሥር የሚመራ ሰብአዊና ቁሳዊ ድጋፍ የሚያቀርብ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

አባ አሩፐና ይኽ የኢየሱሳውያን የስደተኛ መርጃ ማእከል

የዛሬ 35 ዓመት በፊት የኢየሱሳውያን ማኅበር ጠቅላይ አለቃ የነበሩት አባ ፐድሮ አሩፐ በዚያኑ ወቅት የተለያዩ አካላት በዓለማችን ክልል የሚኖሩት የማኅበሩ አባላት ለስደተኞችና ለተፈናቃዮች የሚሰጡት አገልግሎት ምስክርነት በማስተንተን ያንን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደማውያን የቆሰለው አካል በአሁኑ ወቅት የሚኖሩትን ለመደገፍና ለመንከባከብ ይኸንን የኢየሱሳውያን የስደተኞችና ተፈናቃዮች መርጃ ማእከል እንዲቋቋም በማድረግ፣ ለዚህ ማኅበራዊ ክስተት ምላሽ እንዲሰጥም በማነቃቃት ቁሳዊና ሰብአዊ ድጋፍ በማቅረብ ስለ ስደተኛው መብትና ክብር በመጣበቅ የሚያገልግል መሆኑ ቅዱስ አባታችን በማስታወስ እንደገለጡትም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የሕንጸት አገልግሎት የሚያቀርብ፣ ስደተኞችና ተፈናቃዮች ከተለያዩ ለአደጋ ከሚያጋልጡ ለክብር ሰራዥ ተግባሮች መገልገያ እንዳይሆኑ በመደገፍና ቅርብ በመሆኑ በመምራት ከተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራትና ብሔረ ማኅበራት ጋር በመተባበር በአሁኑ ወቅት በሶሪያ አፍጋኒስታ ማእከላዊት ረፓብሊክ አፍሪቃ፣ በዴሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎ በጠቅላላ ውጥረትና ግጭት በሚታይበት ክልል ተሰማርተው ለሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ በመሟገት የሚያገለግል ነው እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ማእከሉ በቅርቡ በይፋ የሚከፈተው የምኅረት ዓመት ምክንያትም የተለያዩ ጅምሮች በማረጋገጥ ከአንድ መቶ ሺሕ በላይ የሚገመቱት ስደተኞች ትምህርት የማግኘት መብት እንዲከበርለት የሚል እቅድ ወጥኖ ምኅረትን እናነቃቃ በሚል መርህ ቃል ሥር ስደተኞችና ተፈናቃዮች የትምህርት እድል እንዲፈጠርለት ቅስቀሳ እያካሄደ መሆኑ ዘክረው የሚሰጠው አገልግሎት ለስደት ተዳርጋ የነበረቸው ቅድስት ቤተሰብ በማስተዋል የሚከወን አገልግሎት ነው እንዳሉ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.