2015-11-11 15:02:00

ጂጂ ደ ፓሎ፦ ታሪካዊ ጊዜ፣ በምንም ተአምር ወደ ኋላ ለማለት ፈጽሞ አይቻልም


ቀደም ተብሎ እንደተገለጠውም የዚያ እ.ኤ.አ. ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በኢጣሊያ ፊረንዘ ከተማ የተካሄደው የኢጣሊያ ብሔራዊ ቤተ ክርስቲያናዊ ጉባኤ ዋናው ርእስ ሰብአዊነት የሚል፣ ሰብአዊነት ላይ ያተኮረ ያንን እውነተኛውን ሰበአዊነት በእያንዳንዳችን ዘንድ በኑባሬ ያለው ባህይር የሚቀናቀን የሚጻረረ ሁነት እየተፈጠረ ሰብአዊነት ለአደጋ የሚያጋልጥ በተለያዩ ርእዮተ ዓለም ፍልስፍናዎችና መሳይ ኃይማኖቶች አማካኝነት የሚሰበከው ሃሰተኛ ሰብአዊነት በሚገባ ለመግጠም ወደ አናሥር መመለስ ያስፈልጋል፣ እርሱም ሰብአዊነታች የእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ መሆን ላይ የጸና እንደሆነም ማስተዋል እንደሚያስፈልግ ዓውደ ጉባኤው አበክረዋል። ሰብአዊነታችን የእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ የሚል ነው፣ ይኽ ደግሞ የዚያ የወደመው ሰባአዊነታቸው ዳግም ሊያጎናጽፈን የመጣው የፍጹም ልጁ አርአያና አምሳያ መሆን ነው።

ቅዱስ አባታችን ለዓውደ ጉባኤው በለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን ቲዮሎጊያዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቤተ ክርስቲያናዊ ትርጉሙም ኢየሱስ ክርስቶሳዊ መሆኑ አብራርተዋል። ቤተ ክርስትያን ማኅበረ ክርስቲያን አገልጋዮች ካህናት ብፁዓን ጳጳሳት የመንፈሳውያን ማኅበር አባላት ሁሉ ይኸንን ውብ ሰብአዊነት መመስከር ይጠበቅባቸዋል፣ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስን ማበሰር ማለት ነው።

ሁሉም በተጠራበት ጥሪ በሚኖረው ሕይወት መውደቅና መነሳት ተመክሮ ያለው ነው። መድከም ያለ ቢሆንም ቅሉ ኃይላችን በድካማችን ላይ መሆኑ መታመን ይኖርብናል፣ ፍጹማን አይደለንምና፣ በኢየሱስ የሚያምን ቢወድቅም ኢየሱስ ኃይሉ ነው። ነጻ የሚያወጣው እውነት ነው። ስለዚህ አስመሳይ ሕይወት አለ መኖር፣ ፍጹም ሆነህ ለመቅረብ አለ መሞክር፣ ሰብአዊነትህን መኖር፣ የሚኖረው ሰብአዊነት ያ በክርስቶስ ዳግም የታደለን መሆን አለበት ይኸንን ቅዱስ አባታችን በተለያየ መልኩ በዓውደ ጉባኤው ተገኝተው እንዳብራሩ በዓውደ ጉባኤው የተሳተፉት ዓለማዊ ምእመን ጂጂ ደ ፓሎ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.