2015-11-11 15:05:00

ቅዱስ አባታችን፦ ለሁሉም የተገባ ሰብአዊ መብትና ክብር የሚያከብር ሥራ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በፊረንዘ ከተማ በተካሄደው አምስተኛው የኢጣሊያ ቤተ ክርስቲያን ብሔራዊ ዓውደ ጉባኤ ለመሳተፍ ወደ ከተማይቱ ከመሄዳቸው ቀደም በማድረግ ፕራቶ ከተማን ጎብኝተው እዚያ ለከተማይቱ በለገሱት ምዕዳን፦

የከተማይቱ ሕዝብ ላደረገላቸው አቀባበል በዚያች ከተማ የሚኖሩት ስደተኞች ባጠቃላይ ሁሉንም አመስግነው የፕራቶ ሕዝብ በከተማይቱ የሚገኘው ስደተኛ ተዋህዶና ካስተናጋጅ ባህል ጋር ተዋውቆ ገዛ እራሱን በማስተዋወቅ ለመኖር የሚያግዘው እድል ስለ ፈጠረለትና ይኽ ደግሞ ሌላውን ችላ በማለት በግድ የለሽነት መመልከት የሚለው ጎጂ ባህል የሚያገል ኃይል ነው ብለዋል። በጋራ መኖር ከባድ የሚያስመስለው በተለያዩ መንገድ ለሚሰበከው አመለካከት እጃችሁን ሳትሰጡ የምትኖሩት ሰላማዊ የጋራ ኑሮ አቅቡ ተንከባከቡ አደራ።

የሰውል ልጅ ሰብአዊ ክብር የማይክድ ሥራ

ስደተኞች ለአዲት አገር ትልቅ ሃብት መሆናቸው ይኸው የፕራቶ ከተማ ተጨባጭ ምስክር ነው፣ ከተማይቱ ለሰላማዊ የጋራ ኑሮ የሙያ ትምህርት የሚቀሰምባት ከተማም ነች፣ ስለዚህ የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብር የሚጠይቀው የተገባ መስተንግዶ የተገባ ሥራ ለሁሉም ማረጋገጥ ያለው አስፈላጊነት ያሳሰቡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አያይዘው በቅርቡ በዚያ ክልል የተገደሉት ሁለት የቻይና ስደተኛ ዜጎችን አስታውሰው፣ ለሞት የተዳረጉት ሁለቱ ሴቶች በሰው ልጅ ላይ የሚከሰተው በደል ምስክር ነው። ስለዚህ ሁሉም ስደተኛውም ይሁን ተወላጁ ዜጋ ካለ ምንም ማመንታት በጋራ ማንኛው የሰብአዊ ክብር ሰራዥ ተግባር በጋራ እንዲዋጉ አደራ ብለዋል።

ቅን ሰላምና ፍትህ የተረጋገጠበተ ኅብረተሰብ ማነጽ የሁሉም እንደየ ኃላፊነቱ ግዴታ ነው። በኃሰት ግልጸት አልቦ በሆነው ምርጫ መልካም የሆነውን ነገር ለመገንባት አይቻልም፣ በክልሉ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ወደ ውጫዊው ክልል በመውጣት ለህዝብ ቅርብ በመሆን መደገፍ ይኖርባታል፣ ጥሪዋም ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.