2015-10-26 16:26:00

የሲኖዶስ የፍጻሜ ሰነድ፦ ቤተሰብ የዓለም ብርሃን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ የመከረው የ14ኛው መደበኛ ጠቅላይ ሲኖዶስ ከተጋባእያን ብፁዓን አበው በጠቅላላ 265 ውስጥ ብቃት ያለው የአብላጫው ድምጽ የሚጠይቀው 177 ድምጽ ያገኘው የፍጻሜ ሰነድ እንዲታተም ፈቃድ መስጠታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቅሰው ከገለጡ በኋላ የፍጻሜው ሰነድ በ 94 አንቀጽ የተከፋፈለ መሆኑም አስታውቀዋል።

የፍጻሜው ሰነድ ቤተሰብ በጨለማው ዓለም ብርሃን በሚል ርእስ ሥር የረቀቀው የፍጻሜ ሰነድ ቤተሰብ ብዙ ችግር የሚፈራረቅበት ቢሆንም ቅሉ ችግሮችን ለመግጠም የመጋፈጥ ዓቢይ ብቃት ያለው መሆኑ የሚገልጥ አንድ ወጥ ያለው የሲኖዶስ አበው፣ የሲኖዶስ የማወያያ ሰነድ በማስደገፍ ያካሄዱት ውይይት የሚያንጸባርቅ ጉባእያዊ ድምጽ መሆኑ ኢዛበላ ፒሮ ገለጡ።

የቤተሰብ ችግር የሚያትተው አንቀጽ

ይኽ ዓንቀጽ አብላጫው ድምጽ የሚጠይቀው በ 178 ተቀባይነት አግኝቶ የጸደቀ ሲሆን አባ ሎምባርዲ በሰጡት መግለጫም፦ ይኽ አንቀጽ የቤተሰብ ቁስል ብሎ የሚገለጠው በሕገ ቀኖናና በቤተ ክርስቲያን ደንብ መሠረት ከሕግ ውጭ ተብሎ የሚብራራው ቃል ኪዳን ያፈረሱ የተፋቱ ዳግም በፍትኃ ብሔር ትዳር መሥርተው ስለ ሚኖሩ ሰዎች ጉዳይ የሚመለከት ዓንቀጽ መሆኑ ሲታወቅ፣ እነዚህ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመመለስ የሚፈልጉ ሆነው ዳግም በቅዱስ ቁርባን ሱታፌ እንዲኖራቸው ለሚያቀርቡት ጥያቄ በጥልቅ የሚከታተል ልዩ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ላይ ያተኮረ ጉዞ የሚያመለክት መሆኑ ኢዛበላ ፒሮ አስታወቁ።

የፍጻሜው ሰነድ አወንታዊና ተቀባነት የሚል አቀራረብ ያለው ነው

አባ ሎምባርዲ የሲኖዶሱ የፍጻሜው ሰነድ አወንታዊና ተቀባይነነታዊ አቀራረብ ያለው ከሲኖዶስ የማወያያ ሰነድ በላይ ውይይት የተደረገበትና ብዙ ቀናት የፈጀ ነው እንዳሉ የገለጡት ኢዛበላ ፒሮ አያይዘው፣ የሲኖዱስ የፍጻሜው ሰነድ እጅግ ኃብታም ጥልቅና የተስተካከለ በሚገባ የተዋቀረ መሆኑ አመልክተው፣ አባ ሎምባርዲ በሰጡት መግለጫ ከዚህ ጋር በማጣመርም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባላቸው ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣን መሠረትም በቤተ ክርስቲያን የተሠራው ምስጢረ ተክሊል ይፈታልኝ ባይሆች የሚያቀርቡት የፍች ጥያቄ በቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤት በኩል በጥልቀት መጤን ያለበት ቢሆንም ረዥም ጊዜ የሚፈጅና የተንዛዛ እንዳይሆን በማለት የሰጡት ውሳኔ ያስገኘው ውጤት መሆኑ አባ ሎምባርዲ እንዳብራሩ ኢዛበላ ገልጠዋል።

ምስጢረ ተክሊል የማይፈታ ነው የሚለው የአንቀጸ እምነት ትምህርት ዳግም ተስተጋብተዋል

የቤተ ክርስቲያን የአንቀጸ እምነት የሚያመለክተው ምሥጢረ ተክሊል አይፈታም የሚለው ትምህርት ጫና ወይንም ሸክም ሳይሆን ምሥጢረ ተክሊል የእግዚአብሔር ጸጋ ነው የሚል ሲሆን፣ ይኽ ደግሞ በክርስቶስ ላይ የጸና እውነትና ከቤተ ክርስቲያኑ ጋር ያለው ትሥሥር የሚገልጥ ነው። ሆኖም እውነትና ምህረት በክርስቶስ ዘንድ አንድ ናቸው፣ ከዚህ በመንደርደርም የቆሰለው ቤተሰብ ማስተናገድ ያለው አስፈላጊነትና ሆኖም የተፋቱት ዳግም በፍትኃ ብሔር ትዳር የመሠረቱት በቀጥታ በቅዱስ ቁርባን ሱታፌ የሚል ሳይሆን እነዚህ ምእመናን ውጉዛን እንዳልሆኑ የሚያብራራ ሆኖም ሁኔታቸውን ቀርቦ የሚያጠና በመንፈሳዊ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚሸኛቸው አብሮአቸው ግምገባ የማካሄዱ ሂደት የእረኞች ኃላፊነት ነው የሚል መሆኑ ኢዛበላ አስታውቀዋል።

የተወሳሰበው ሁኔታ የሚያጤን የእረኛ ኃላፊነት

ለይቶ የመረዳቱ ጉዳይ በዚያ ለማንም በማይካደው የእግዚአብሔር መኃሪነት ላይ እማኔ በማኖር  የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የሚተገብር መሆን አለበት፣ አለ ቃል ኪዳን አብረው የሚኖሩት ጉዳይ የመከታተሉ ሂደት የሚኖሩት ሁኔታ ገንቢነት ባለው በወንጌል ብርሃን ተመርቶ ወደ ምሉእ ምሥጢረ ተክሊልና ወደ ቤተሰብአዊነት የሚመራ ወደ መለወጥ የሚሸኝ መሆን አለበት የሚል ማለት መሆኑ ኢዛቤላ ፒሮ ገልጠዋል።

አንዳዊ ጾታዊ ስሜት አለ ምንም አድልዎ መመልከት ነገር ግን ተመሳሳይ ፆታ መካከል ውህደት ተቀባይነት የለውም

የሲኖዶሱ የፍጻሜው ሰነድ ካሰመረባቸው ነጥቦች ውስጥ አንዱ ስለ አንዳዊ ጾታ ስሜት ያላቸው ሰዎች የሚመለከት ሆኖ አንዳዊ ጾታዊ ስሜት አዝማሚያ ባላቸው ሰዎች ላይ አድልዎ እንዳይኖር በማሳሰብ ሆኖም ቤተ ክርስቲያን አንዳዊ ጾታስሜት ባላቸው ሰዎች መካከል ውህደት የማትቀበል መሆኑ ተመልክቶ ይገኛል፣ ከዚህ ቀጥሎም ስለ ስደተኞች ተፈናቃዮችና የሚሳደዱት ቤተሰቦች ጉዳይ በመጥቀውስ በዚህ ችግር ምክንያት ቤተሰብ ለመለያየት አደጋ የሚጋለጡና ለአዲስ የባርነት አደጋ ሰለባ ናቸው፣ ለእነዚህ የኅብረሰብ ክፍል ያንን የሰብአዊ መብትና ክብር ማክበር የሚል መስተንግዶ እንዲደረግላቸውና መስተንግዶውም ተስተናጋጁ ላስተናጋጅ አገር መኖር የሚገባው ግዴታና ኃላፊነት ማክበር ይጠበቅበታል የሚል ሃሳብ የሰፈረበት መሆኑም ኢዛቤላ ያመለክታሉ።

የሴቶች አክብሮት ሕፃናትና ለአረጋውያን ጥበቃ

ሌላው በፍጻሜው ሰነድ ሰፊ አስተንትኖ የተሰጠበት በጠቅላላ ቋሚ የቤተሰብ ሕይወት መግለጫ ለሆኑት ለሴቶች ለወንዶች ለሕፃናትና ለአረጋውያን የተሟላ ጥበቃና ያላቸው የየራሳቸው ሚና ማክበር ያለው አስፈላጊነት የሚያብራራ ሲሆን፣ ለሴቶች በቤተ ክርስቲያን ለሚገባቸው አገልግሎት ሕንጸት ስለ ሕፃናት በተመለከተ ደግሞ ወላጅ አልባ የሆኑትን የማሳደግ ውበትና ውህበት ይኽም ያንን የተሰናከለው ቤተሰብአዊ ግኑኝነት ዳግም መልሶ የሚያጎናጽፍ በሚል ክብር ላይ የጸና ሆኖ፣ እጓለሞታ የአካል ጉዳተኞች፣ በቤተሰብ እምነት የማስተላለፉ ተልእኮ ያላቸው አረጋውያንና አያቶች ተጠቅሞ መጣል ከሚለው እንደ ጥራጊ ከሚመለከተው ባህል መጠበቅና መንከባከብ ያለው አስፈላጊነት በማብራራት፣ እንዲሁም ያላገቡት በቤተ ክርስቲያንና በኅብረተሰብ ዘንድ ያላቸው ሚና ትኵረት እንዲያገኝ የሚል መሆኑም ኢዛቤላ ያመልክታሉ።

አክራሪነት ግለኝነት ድኽነትና ሥራ አጥነት ለቤተሰብ ስጋት ናቸው

በዚህ በአሁኑ ወቅት ቤተሰብ ላይ የሚያንዣብበው ስጋት እርሱም ክርስትናን የሚያገል ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ አክራሪነት፣ እየሰፋ በመሄድ ላይ ያለው ግለኝነትና ለእኔ ባይነት፣ አዲሱ የሥነ ፆታ ትምህርት፣ ግጭቶች ስደት ድኽነት ያልተረጋጋ የሥራ እድልና ሥራ አጥነት ሙስናና ቤተሰብ ከሕንጸትና ከባህል የሚያገል ለዚህ አደጋ የሚያጋልጥ፣ የኤኮኖሚው ሂደት ሰውን ሳይሆን ገንዘብ ማእከል የሚያደርግ ዓለማዊ ትሥሥር የተካነው ሂደት፣ ችላ ባይነት፣ አስጸያፊ ስእሎችና የወሊድ ቁጥር ማነስ የተሰኙትን በቤተሰብ ላይ የሚያንዣብብ አደጋ መሆናቸው ሲኖዶሱ በፍጻሜው ሰነድ እንዳሰመረበት ፒሮ ገለጡ።

ለምሥጢረ ተክሊል ሕንጸት

ይኽ የብፁዓን ሲኖዶስ አበው የፍጻሜ ሰነድ ለምሥጢረ ተክሊል የሚሰጠው ሕንጸት ማበረታታትና በተለይ ደግሞ ምሥጢረ ተክሊል ለመቀበል ጥያቄ ለሚያቀርቡ ወጣቶች የተሟላ ተገቢ ቅድመ ዝግጅት ይኽም የንጽሕናና ገዛ እራስ እንደ ጸጋ ለሌላው መስጠት በሚል ክርብ ላይ የጸና ሕንጸት ማግኘት እንደሚገባቸው ያሳስባል። በዚህ እይታም ጾታዊ ስሜትና ወሊድነት ላይ ያነጣጠረ ልጆች በውስጣቸው የፍቅር ተዘክሮና ተስፋ ይዘው የሚጓዙ እጹብ ፍሬ መሆናቸው ያስገነዝባል። እንዲሁም የር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድተኛ ሰብአዊ ሕይወት የተሰኘው አዋዲ መልእክት ላይ የጸና የጾታዊ ስሜት ሕንጸት፣ ቤተሰብ የመመሥረትና የውፉይ ሕይወት ጥሪ ላይ ያነጣጠረ ሕንጸት መካከል ያለው ግኑኝነት በሚያብራራ፣ ከዚህ ጋር በማያያዝም የጾታዊ ስሜት የአካላዊ የአባታዊ ኃላፊነትና ወላጆች ለልጆቻቸው ያለባቸው የእምነት ሕንጸት ጉዳይ በተመለከተም ያለባቸው ኃላፊነት በጥልቀት እንደሚያብራራ ፒሮ አስታወቁ።

ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት እቃቤ

መንግሥታትና የመንግሥት ተቋማት ቤተሰብ የሚደግፍ ፖለቲካ እንዲንከባከቡና እንዲያነቃቁ ብፁዓን አበው በፍጻሜው ሰነድ በማሳሰብ በፖለቲካው ዓለም የሚጠመዱት ካቶሊካውያን ምእመናን ቤተሰብ ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት መከላከል ላይ ታምነው በዚሁ ዘርፍ እንዲያገለግሉ የጣፋጭ ሞትና ጽንስ የማስወረዱ ውሳኔ እንዲቃወሙ በማሳሰብ ቀጥሎም ስለ ቅይጥ ጋብቻም ላይ በማተኮርም ይኽ ዓይነቱ ጋብቻ በተለያዩ ሃይማኖቶችና በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ለሚደረገው የጋራው ውይይት ድጋፍ መሆኑ፣ አውንታዊ ገጽታውን በማበከር የሃይማኖት ነጻነት እንዲሁም የሕሊና ነጻነት ማክበርና መከላከል ያለው አስፈፈላጊነት ማሳሰባቸው ፒሮ ገለጡ።

ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን ለማበሰር የምትጠቀምበት ቋንቋ ማደስ ይገባታል

የቤተሰብ ወንጌል የሰው ልጅ ጥልቅ ጥባቄ (ጥልቅ ፍላጎት) ምላሽ የሚሰጥ እንዲሆን ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምበት ቋንቋ ማደስ እንደሚገባት ብፁዓን አበው በፍጻሜው ሰነድ በማሳሰብ፣ ይህ ደግሞ አስፍሆተ ወንጌል ደንቦች ማቅረብ ብቻ ሳይሆን የቤተሰብ መልካምነት የመኖር ብቃት የሚያሰጥ ጸጋ ማበሰር ማለት መሆኑ እንዳሰመሩበት ፒሮ አስታወቁ።

ቤተሰብ የጥልቅ ሰብአዊ ስሜት መልህቅ የሚቀመጥበት ወደብ ነው

በመጨረሻም የሲኖዶሱ የፍጻሜው ሰነድ የቤተሰብ ውበትና ውህበት በማበከር በዚያ የኅብረተሰብ እድገት አቢይ አስተዋጽኦ የሚሰጥ የጥልቅ ሰብአዊ ስሜት መልህቅ የሚቀመጥበት ወደብ መሆኑ የሚያረጋግጥ በወንድና በሴት መካከል በሚታሠረው ቃል ኪዳን ላይ በሚጸናው ትዳር ላይ የተገነባ በዚህ በተዋከበው ዓለም የሰብአዊ ምኅዳር የሆነው ቤታዊ ቤተ ክርስቲያን ነው፣ ስለዚህ በመንግሥታውያን መዋቅሮች ዘንድ እንክብካቤ ማግኘትና መበረታታት አለበት የሚል ሃሳብ የሰፈረበት መሆኑም ፒሮ አመለከቱ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ስለ ቤተሰብ ጉዳይ የሚመለከት ሰነድ ሲኖዱሱ ይማጸናል

የሲኖዶስ አበው ቤተሰብ ጉዳይ መክሮ ያጸደቀው የፍጻሜ ሰነድ ለቅዱስ አባታችን በማቅረብ ቅዱስነታቸው ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ ሐዋርያዊ ምዕዳን ተመጽነዋል፣ ይክ የሲኖዶስ አበው ተማጽኖ ምን ማለት መሆኑ አባ ሎምባርዲ ሲያስረዱ፦ ጥያቄው ሲኖዶሱ ያጸደቀው የፍጻሜ ሰነድ ማጠቃለያ ሳይሆን ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ተላልፎ እሳቸውም ይዞታውን ገምግመውና በጥልቀት ተመልክተው እንዳለው መጽደቅ ወይንም በዚህ በቀረበው የፍጻሜ ሰነድ ላይ ተንተርሰው መታከል ያለበት በማከል መቀየር የሚገባውን በመቀየር ምዕዳን የማቅረቡ ኃፊነት የሳቸው መሆኑ የሚያመለክት ጥያቄ ነው እንዳሉ ኢዛበላ ፒሮ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.