2015-10-21 17:22:00

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፤


ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ! እንደምን አደራችሁ! ባለፈው አስተንትኖአችን ወላጆች ለልጆቻቸው በፍቅር አቅደው ከጽንስ ግዜ ጀምሮ ስለሚገቡት ቃል ተመልክተናል፣ በዚህ አስተንትኖ አጠቃላይ የቤተሰብ ባህርይ ቃል በመግባት የተገነባ ነው ለማለት ይቻላል፣ ይህንን በደንብ እናስተንትነው፣ የቤተሰብ ማንነት ቃል በመግባት የተመሠረተ ነው! የሚለው ሓሳብን፣ ስንመለከት ቤተሰብ ባልና ሚስት አንዱ ለሌላው በሚገቡበት የፍቅርና የመተማመን ቃል ኪዳን በሕብረት ለመኖር ነው፣ ይህ ደግሞ ልጆቻቸውን የመቀበልና በሚገባ ለማሳደግ ኃላፊነትን ሲያጠቃልልል እንዲሁም አዛውንት ወላጆቻቸውን መንከባከብና በቤተሰብ ውስጥ የሚገኙትንም ደካማዎችን የመንከባከብና የመርዳት ኃላፊነት አለባቸው።

በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ወላጆችም ይሁን ልጆች ሁሉም በየፊናው በተሰጠው ችሎታ አንዱ ሌላውን የመርዳትና እንዲሁም ጉድለቶችም ካሉ ጉድለቶቹንም መቀበል አስፈላጊ ነው። ሙሽሮች ቃል ሲገቡ ከሁለቱ ባሻገር የአባቶች እናቶች እና ሕጻናት ደስታና ሥቃይ መካፈልን በማጠቃለል ለሰብአዊ አብሮ መኖርና የጋራ በጎ የሆነውን ለመካፈል ዝግጁና ተቀባይ ለመሆን ነው፣ የዚሁ ተቃራኒ በሆነ ሕይወት የሚኖር ቤተሰብ ዝግና እርስ በእርሱ የሚጋጭ ቤተሰብ በመጀመሪያ እንድትወለድና በሕይወት እንድትንኖር ያበቅዋትን ቃል ኪዳን ያፈርሳል ይገድላልም። የቤተሰብ ማንነቷ የሚታወቀው ቃል ኪዳንዋን በመጠበቅ በመላው ዘመደ አዳም እየሰፋችና እየተስፋፋች የምትሄድ መሆኑን እንዳትረሱ አደራ። 

ባሁን ወቅት የቤተሰብ ክብር መለያ የሆነው ታማኝነት የተዳከመ ይመስላል። ይህም በተለይም እኔነትን በማዳመጥና እራስን ለማስደሰት ሲፈጠር ቅድመ መመሪያ ነፃነት በማለት ሰበብ ሲሰጠው ይህም ከእውነተኛው ነፃነት ጋር እንደማይተሳሰር ነው። ቃል በሕብረት ለመኖር የገቡትን ሕግን ለማክበር ብቻ አይደለም።  ማንኛውም ሰው ስላለበት ሃላፊነትና ሀብት ብቻ ሊወደድና ሊፈቀር አይፈልግም። በጓደኝነት መካከል እንኳን ያለው የፍቅር ሃይል የጓደኝነት ነፃነትን ሳያስተጓድል የሚቀጥል ጓደኝነት ነው። ስለዚህ ፍቅር ነፃነት ነው፡ ለቤተሰብም የምንገባው ቃል ኪዳን በነፃነት ነው። ነፃነት ከሌለ ጓደኝነት አይኖርም! ነፃነት ከሌለ ፍቅር አይኖርም! ነፃነት ከሌለ ትዳር አይኖርም።

ስለዚህ ነፃነትና ታማኝነት በመደጋገፍና በመስማማት በግላዊም ይሁን በማህበራዊ ኑሮ አብረው በመኖር ይጓዛሉ እንጂ ኣንዱ ሌላውን አይቃረንም። በማህበራዊም ይሁን በግላዊ ሕይወት በተለያዩ ዘርፎች በሃላፊነት ቃል የገባነው ወይም የገቡልንን ሳይከበርና ሳይፈጸም ሲቀር ምን ያህል ብልሽትና ጉድለት እንደሚያስከትል እስቲ እናስበው።

አዎን ወንድሞቼና እህቶቼ ታማኝነት በሃላፊነት የምንገባው ቃል ነው ይህም ሃላፊነት በመታዘዝ በገባነው ቃል በነፃነት እያደግና እየጠነከርን ይፈጸማል። ታማኝነትና እምነት ከሌሎች ጋር መካፈልን ይጠይቃሉ በሕብረት መኮትኮትና መመገብ የሚፈልጉ ተስፋዎች ናቸው። እንዲያውም ስለ ታማኝነት በሃሳቤ የመጣውን ላካፍላችሁ አያቶቼ ሲተርኩልኝ በኛ ግዜ አንድን ነገር ለመስራት ይሁን ለመገንባት ቃል ሲገባ የቃል ሃላፊነቱ ምልክት መጨባበጥ ነበር፣ መጨባበጥ ማሕበረሰባዊ ምልክት ሲሆን ዋና መሰረቱም ቤተሰብ ነው። ወንድና ሴት የወደፊት ሕይወታቸውን አንድ ላይ የሚጋዙትትም በዚሁ መጨባበጥና መያያዝ ነው፣

የሰው ዘር ቃሉን በታማኝነት ካከበረ ታላቅ ነገር ነው። የታማኝነት ውበትን ከተመለከትን እንፈራለን! ታማኝነት የሚጠይቀውን ድፍረትና ጥንካሬ ካናናቅን እንጠፋለን። ምንም አይነት ፍቅር ወዳጅነትና ደስታ በሕይወታችን አይኖረንም። የገባነውን ቃል በታማኝነት መኖርና መፈጸም ምን ግዜም ቢያስደንቅም ታማኝነት በገንዘብና በሃይል አይገዛም አይሸጥም ያለ መስዋዕትነትም ልንጠብቀው አንችልም።

የፍቅርን እውነት ቤተሰብ ካልሆነ ማንም ትምህርት ቤት ሊያስተምረን አይችልም። ምንም አይነት ሕገ መዋቅር እንኳን የዚህን የሰው ልጅ ዘር ትልቅ ሃብት የሆነውን ፍቅር ሊያስተምር አይችልም። የመጀመሪያውን ፍቅር የሚገለጠው ሲወልድ ሲዋለድ ከሚመጣው የስጋ ዝምድና ፍቅር ነው።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ በማሕበራዊ ኑራችን ለፍቅርና ለታማኝነት አስፈላጊነው ክብር መስጠትና መገንባት አስፈላጊ ነው። ዛሬ ከምን ግዜም በበለጠ በብዙ ሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች ቤተሰብን የሚመሰርቱ የገቡትን ቃል ኪዳን ሳይጠብቁ የሚያፈርሱ ብዙዎች ናቸውና የፍቅር መሰረት የሆነውን ቃል አይዘንጉ። የእግዚብሔር ቃልም ታማኝነት የፍቅር መጀመሪያው መሆኑን በመግለጥ በዘፍጥረት ብዙና ተባዙ ምድርንም ሙላት በማለት የባረካት።

ቅዱስ ጳውሎስም ይህ የቤተሰብ መተሳሰር በማናውቀው ምሥጢራዊ መንገድ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና በቤተክርስትያኑ መካከል ባለው መተሳሰር እንደተገለጠ ያረጋግጥልናል፣ ስለሆነም በቃል ኪዳን ታማኝ ሆኖ መገኘት በእግዚአብሔር ጸጋና ምሕረት በመጠጋት ለቤተክርስትያን እንደየክብር ስጦታ ሆኖ ይገኛል፣ ስለዚህ ጉዳይ እየጸለዩና እየተወያዩ ላሉ የሲኖዶስ አባቶች ጳጳሳት እግዚአብሔር ሥራቸውን እንዲባርክ እንዲሁም ለጌታና ለኪዳኑ ታማኝ በመሆን አመርቂ ውጤት እንዲያስገኙ እንጸልያላቸው፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.