2015-10-12 15:54:00

ሲኖዶስ፦ እ.ኤ.አ. የጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ውሎ ጽማሬ


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. የሲኖዶስ አበው በትንናሽ ቡድን ተመዳድበው እያካሄዱት ያለው ውይይት በሲኖዶስ የውይይት ማካሄጃ ጠቅላይ ሰነድ “የቤተሰብ ጥሪ የመለየት (የመርዳት) ችሎታ” በሚል ርእስ ሥር የተጠናቀረውን በማስደገፍ ቀጥሎ ውሏል።

በዚህ በተካሄደው ውይይትም ሚስጢረ ተክሊል አይሻርም የሚለው የአንቀጸ እምነት ትምህርት፣ ምእመናን አይሻርም ሲባል ለመሸከሙ የሚያዳግት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ቀንበር አለ መሆኑ በሚገባ እንዲያስተውሉ ለመደገፍ በሚል እይታ መሠረትም እንዲጤን የሚያስገነዝብ የአደራ ጥሪ ቀርበዋል።

ቤተሰብ በባህርዩ ልኡክ መሆኑ በማስተዋል ቤተሰብና በአስፍሆተ ወንጌል መካከል ያለው ግኑኝነት ውሎው መክሮበት፣ በዚህ ጉዳይ ላይ በተለይ ደግሞ ወላጆች ወደ ወንጌል እንዲቀርቡ የሚያደርጉ በመሆናቸው የልጆች ሚና ላይ በማተኮር ከዚህ ጋር በማያያዝም እምነት በማስተላለፍ ተእልኮ የወላጆች ሚና ዙሪያ ውይይት ተካሂደዋል።

ቤተሰብ የቅድስና የተስፋ የአስፍሆተ ወንጌል ስፍራ ነው፣ የቤተሰብአዊ ሕይወት፣ የዚያ በዕለታዊ ሕይወት የሚኖር ቅድስና የሚገለጥበትና ቤተሰብ ያለው የእምነት አድማስ የሚያስተውል ሲሆን ኅብረተሰብ ለመለወጥ የሚችል አካል ይሆናል።

የሲኖዶስ ብፁዓን አበው በቡድን ተከፋፍለው ባካሄዱት ውይይት በተለያየ ችግር የቆሰለው ቤተሰብ ጉዳይ ላይ በማተኮርም ቤተ ክርስቲያን በምህረት በፍቅር በትእግሥት እይታ ቅርብ በመሆን ስለ ምሥጢረ ተክሊል በተመለከተ እውነት በግልጽ በብርታት ልታበስር ይገባታል፣ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት በምስጢረ ተክሊል ዙሪያ እውነተኛ ተገቢ ተስተውሎ ያለ አይመስልምና።

ቤተሰብ የጸሎት ሥፍራ መሆኑና ይኽ ደግሞ በቅዱስ ቁርባን ስታፌ የሚል ሲሆን፣ በቅዱስ ቁርባን ሱታፌ ጸላይ ቤተሰብና ሰላም የተካነ ቤተሰብ ያጸናል፣ ለዚህም ነው ቤተሰብ ቤታዊ ቁምስና ለመሆን የሚያበቃው፣ በመጨረሻው ከቀትር በፊት የተካሄደው ውሎው ጦርነት አመጽ የሕይወት ዋስትና እጦት ባለበት ክልል የሚኖር ቤተሰብ የተጋረጠበት ለስደት ለመፈናቀል አደጋ ስለ ሚዳርገው ችግር ርእሰ ዙሪያ ውሎው መክረዋል።

ከቀትር በኋላ በተካሄደው ውይይት በሲኖዶስ የውይይት መርሃ ሰነድ ያለው ክፍል ሁለት ላይ በማተኮር ቤተሰብ እግዚአብሔር በዓለም ላይ ባለው እቅድ ያለው የተባባሪነት ሚናው ለይቶ እንዲያስተውል ክርስቶሳዊ ማእከልነት የተካነ ሕንጸት ያስፈልገዋል። ስለዚህ ቤተሰብ የራሱ ተልእኮ ዳግም ለይቶ ማወቅና በተለይ ደግሞ ከዚያ ከገዛ እራሱ ማንነት ጋር በትግል በሚኖር በወሊድ ቁጥር ማነስ እጅግ በተጠቃው ኤውሮጳ ያለው አስፈላጊነትና በዚህ በሥነ አኃዝ የተራቀቀ የመገናኛ ብዙኃንና የማኅበራዊ ድረ ገጽ እጅግ እየተስፋፋ በመምጣቱም ምክንያት ሰብአዊ ግኑኝነት በሃሳብ እንዲኖር እየተገደደ ባለው ዓለም ከክርስቶስ ጋር የመገናኘት ግላዊ ተመክሮ ማነቃቃት አስፈላጊ መሆኑ ውሎው አስምሮበታል።

በተናንሽ ቡድን በመከፋፈል ውይይት የሚያካሂዱት የሲኖዶስ አበው የሲኖዶስ ውይይት ማካሄጃ ሰነድ በማጤን ሃሳብ በመለዋወጥ መታከል ይገባዋል የሚሉትን በተለይ ደግሞ በተጨባጭ ሁኔታ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት እግብር ላይ መዋል ይገባዋል የሚሉዋቸውን ሃሳብ እንዳቀረቡም ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.