2015-10-09 16:01:00

አባ ስፓዳሮ፦ የቤተ ክርስቲያን ኅዳሴ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ክፍት የሆነ ተኪዶ ማለት ነው


የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል በሁለት ሳምንት አንዴ ለሚታተመው ካቶሊካዊ ሥልጣኔ ለተሰየመው በማኅበሩ ለሚታተመው መጽሔት ዋና አዘጋጅ አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ በመጽሔት የመጨረሻው ኅትመት ዘንድ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቤተ ክርስቲያን ኅዳሴ፦ ኢግናዚዮሳዊ አናሥር ያለው ነው” በሚል ርእስ ሥር ባቀረቡት ጽሑፍ፦

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የኢየሱሳውያን ማኅበር ካህን ናቸው፣ በመሆናቸውም ስለ ቤተ ክርስቲያን ኅዳሴ ያላቸው ራእይ ከኢየሱሳዊው ማኅበር መንፈሳዊነት ራእይ ጋር የሚገናኝ ነው። ይኽ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር የሚለውጥና የሚያድስ መንፈሳዊ ኅዳሴ የሚል መሆኑ አባ ስፓዳሮ ባቀረቡት ጽሕፉ በስፋት በማብራራት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ብዙዎን ጊዜ ኢየሱሳዊ ካህን ቅዱስ ፒየትሮ ፋቭረ አስተንፍሶ አብነት ሲያደርጉ አለ ምክንያት አይደለም።

ቅዱስ አባታችን ኅዳሴው እንዴትና በምን መንገድ መከወን እንዳለበት የሚያዝ መርሃ ግብር የላቸውም፣ የሚያሳስቡት ኅዳሴ የመለየት ችሎታ እርሱም የአስተውሎ ብቃት ማእከል ያደረገ ነው።  በጠሩት ሲኖዶስ አማካኝነትም ቤተ ክርስቲያንን በማንቀሳቀስም በመለየቱና በማስተዋሉ ሂደት ትነቃቃ ዘንድ እያደረጉ ናቸው። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ኅዳሴ በመንፈስ ቅዱስና በተቋምነት መካከል ያለው የተወያይ ውጥረት ውጤት ነው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለ ውጥረት ነው። ውጥረቱ ደግሞ አወንታዊ ነው። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ውስጣዊ ለውጥ በማለት ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የገለጡት ሃሳብ የሚያንጸባርቅ ነው። ቤተ ክርስቲያን በጉዞ ያለ ሕዝብ እንዲሁም ተቋም ነች፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮም ቤተ ክርስቲያን ታማኝ ነጋዲ የእግዚአብሔር ሕዝብ በማለት ይገልጡዋታል። ቅዱስ ኢግናዚዮስም ቅድስት ሥልጣናዊት ቤተ ክርስቲያን በማለት የገለጠው ሃሳብ ጋር ያጣመረ ኅዳሴ ነው  በማለት በስፋት ያብራራሉ።   








All the contents on this site are copyrighted ©.