2015-10-09 15:59:00

ሲኖዶስ፦ እ.ኤ.አ. የጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. የሲኖዶስ ውሎ


የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በመካሄድ ላይ ያለው 14ኛው ጠቅላይ መደበኛ ጉባኤ ሲኖዶስ እ.ኤ.አ. ከጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በተለይ ደግሞ የሲኖዶስ ውይይት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ዕለት በዕለት የሚያካሂደው ውይይት በተመለከተ በእያናንዷ ቀን የሚሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በመቀጠል፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በኢጣሊያ የአንኮናና ኦሲሞ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኤድዋርዶ መኒከሊ፣ የሶሪያ ስርዓት ለምትከተለው የአንጽዮኪያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በሊባኖስ ሊቀ ጳጳሳት የሶሪያ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ርእሰ ብፁዕ አቡነ ኢግናዚዩስ ዩሲፍ ሶስተኛ ዩዋና እንዲሁም በጋና የአክራ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፓልመር ቡክለ ተሸኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀትር በፊትና ከቀትር በኃላ ሲኖዶስ በተናንሽ ቡድኖች ተከፋፍሎ የሚያካሂደው ውይይት ቀጥሎ መዋሉ አስታውቀዋል።

አባ ሎምባርዲ የሲኖዶስ ተናንሽ የውይይት ቡድኖች ቅዋሜው የቡድኖቹ መራህያን እንዲሁም አፈ ቀላጤዎች ማንነት የሚገልጥ ሰነድ መሰራጨቱንም አስታውሰው በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ድረ ገጽ በኩል የሲኖዶሱ ውሎዎች በተመለከተ በተለያዩ ቋንቋዎች ሰፊና ጥልቅ የድምጽና የጽሑፍ ማስረጃ ጭምር ለማግኘት እንደሚቻል ከገለጡ በኋላ አያይዘውም በሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቸሊ ሊቀ መንበርነት የሚመራ በአይቮርይኮስት የካታኢዮላ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኢግናሰ በሲ ዶግቦ በፊሊፒንስ ይሰቡ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፓልማ እንዲሁም የሳን ኹዋን ፖርታ ሪኮ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሮበርቶ ኦክታቪዮ በአባልነት ያቀፈ የሲኖዶስ የማስታወቂያ ቢሮ መቋቋሙንም አስታውቀዋል።

አባ ሎምባርዲ እንዲህ ባለ መልኩ የጋዜጣዊ መግለጫ መድረኩን በማስጀመር ቀጥለው፦

ብፁዕ አቡነ ቡክለ

ብፁዕነታቸው አፍሪቃን ወክለው በዚህ የጋዜጣዊ መግለጫ መርሃ ግብር መገኘታቸው ቀደም በማድረግ ከገለጡ በኋላ አፍሪቃ 37 የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ያቀፈች በስምነት መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ መሰረት በማድረግ በጸኑት 8 የብፁዓን ምክር ቤቶች ኅብረትና በመጨረሻም የመላ አፍሪቃ አግሮችና ማዳጋስጋር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የሚያቅፍ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት እንዳለ ገልጠው እንዲህ ባለ መልኵ የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ቅርጸ ቅዋሜው ምን እንደሚመስል ካብራሩ በኋላ በመካሄድ ላይ ያለው ሲኖዶስ በቡድን ተከፋፍሎ በሚያካሂደው ውይይት አማካኝነት የሲኖዶስ ውይይት ማካሄጃ ሰነድ ላሰፈራቸው ጥያቄዎች መልስ በመስጠት እርሱም የቤተሰብ መጻኢና የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ላይ በማተኰር መሆኑ ገልጠዋል።

አፍሪቃ በዚህ ሲኖዶስ ሱታፌ ለቤተሰብና ለቤተ ክርስቲያን እርባና ላይ በማተኮር አለ ምንም ቅድመ ፍርድ በሁሉም መስክ አስተዋጽኦ ለማቅረብ ነው። በአፍሪቃ ያለው ቤተሰብና ባህሉ ያለው እሴት በተለይ ደግሞ በአባላት ቁጥር ብዛት ትልቅ ቤተሰብ የመሆኑ ጉዳይ ላይ በማተኮር ይኽ እሴት በአፍሪቃ ለቤተ ክርስቲያን እድገት መሠረት ነው ብለው የቤተሰብ መጻኢ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ነው ሲሉ በበኩላችው የሰጡት መግለጫ ሲያጠቃልሉ በመቀጠልም፦

ብፁዕነታቸው ፓትሪያርክ ዩሰፍ ሦስተኛ ዮዋና

ከሳቸው ቀደም በማድረግ መግለጫ የሰጡት ብፁዕ አቡነ ቡክለ በአፍሪቃ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እድገት እየታየ መሆኑ የሰጡት መግለጫ ደስ የሚያሰኝ መሆኑ ፓትሪያርኩ ጠቅሰው ሆኖም በመካከለኛው ምሥራቅ የማኅበረ ክርስቲያን ቁጥር እየጎደለ መምጣቱንም ገልጠው፣ ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ ነው ብለዋል። በክልሉ ባለው ሁከት ሳቢያ ሁሉም እንደምያውቀው ቤተሰብ ለሞት ለከፋ ለስደት ለመበታተን አደጋ ተጋልጦ ይገኛል። በኢራቅና በሶሪያ ያለው ሁኔታ መመልከቱ ይበቃል ብለዋል።

ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ፓትሪያርክ ካህናት ገዳማውያም የተለያዩ የመንፈሳውያን ማኅበራት አባላት ለዚያ ክልል ሕዝብ በተለያየ መስክ ደጋፊ በመሆን በሰብአዊና በመንፈሳዊ አገልግሎት እየሸኙት ናቸው፣ በዚያ ክርስትና በተወለደበት ክልል  ክርስቲያናዊ ባህል ቀጣይነት እንዲኖረው ዋስትናውም የዚያ ክልል ቤተ ክርስቲያን አባላት ወጣቶች ቤተሰቦች ናቸው። ስለዚህ በገዛ አጋራቸው እንዲቀሩ የዚያ ክልል ቤተ ክርስቲያን በማበረታታት እንዲሁም በገዛ አገሩ ለመኖር የሚያግዘው እድል እንዲፈጠርለትም ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አቤት የምትል የሁሉም ቤት ነች ብለዋል።

ብፁዕነታቸው ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች በማሰባሰብ በሰጡት ምላሽም፦ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የማኅበረ ክርስቲያን ጉዳይ አሳሳቢ ነው። በተለይ ደግሞ ክርስቲያንና የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ቤተሰቦች ለከፋ አደጋ ተጋልጠዋል። ማኅበረ ክርስቲያን አገሩ ለቆ እንዳይወጣ የዚያ ክልል ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም ጭምር ድጋፍ እያቀረበች ነው ብለው መካከለኛው ምስርቅ በኤውሮጳም በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ጭምር ተክደዋል፣ ዛሬ በዚያ ክልል ሰላም እንዲረጋገጥ ለእነዚህ አገሮች ጥሪ አናቀርባለን ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል መኒከሊ

ሲኖዶሱ በተለያዩ ተናንሽ ቡድኖች በመከፋፈል ውይይቱ እየቀጠለበት ነው። እነዚህ ቡድኖችም የሲኖዶስ የውይይት ማካሄጃ ሰነድ ቀዳሜ ክፍል ዙሪያ እየመከረ ነው። በዚህ ቀዳሜው የሰነዱ ክፍል የቤተሰብ ኵላዊ ገጽታ የሚያንጸባርቅ መሆኑ በዚህ አጋጣሚም ለጋዜጠኞቹ አስታውቀዋል።

የሰው ልጅ የቤተሰብ ሕይወት ነው፣ ሕይወት ደግሞ ተገናኝ በመሆኑም በዚህ የሕይወት ተገናኝ ባህርይ ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው አስተዋጽኦ እንዳለም ነው። ሲኖዶሱም የአስተዋጽኦው ምን ተመስሎው ዙሪያ እየመከረ መሆኑ አብራርተዋል።

የሲኖዶስ ንኡሳን ቡድኖች የሚያካሂዱት ውይይቶች ክፍት ግልጽ የወንድማማችነት መንፈስ የተካ የተለያዩ አስተያየቶች የሚቀርብበት ነው። ሆኖም ዕለት በዕለት የሰባት ሰዓት ጥልቅና ረዥም ውይይት ማካሄድ አድካሚ ነው። ቢሆንም አገልግሎት ነው ብለዋል።

አባ ሎምባርዲ፦ አንድ ጋዜጠኛ እርሱም በሲኖዶስ ውስጥ ሴራዊ ሂደት አለ ወይ ሲሉ ላቀረቡላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፦ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያን ለቤተ ክርስቲያን ነው። ስለዚህ የማኅበረ ክርስቲያን ጉዳይ ነው። በመሆኑም ሴራዊ ሂደት የሚለው አገላለጥ የማይወክለው የማይመለከተው ጉዳይ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.