2015-10-09 16:06:00

ሊቢያ


የሊቢያው አምስተኛውን ዓመቱን እያስቆጠረ ያለው በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ዘንድ እውቅና የተሰጠው በቶብሩክ ያለ መንግሥትና እንዲሁም በትሪፖሊ ያለው እስላማዊ ሃይማኖት አናሥር ያደረገው መንግሥት በጸናበት አገሪቱ ለሁለት ለከፈለው የድኅረ ጋዳፊ ውዝግብ ለመቅረፍ አዲስ የሰላም ምዕራፍ ለመጀመር በሚያግዛት መንገድ ለማገኘት የበቃች እንደምትመስል ይነገራል።

ይኽ በሞሮኮ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገላጋይነት ሥር የተካሄደው የሰላም ድርድር በሊቢያ የአገራዊ አንድነት መንግሥት እንዲቆም የሚል ሲሆን፣ ይኽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን በመወከል በርናርዲኖ ለዮን በገላጋይነት ሚና ያሳተፈው የሰላም ድርድር የትሪፖሊው ምክር ቤት በተባበሩት መግንሥታት ገላጋይነት የቀረበው የሰላም ሰነድ ደጋፊ ድምጽ የሰጠበት ሲሆን የተደረሰው ስምምነት አወንታዊ እርምጃ ነው። ይኽ ያለፈው የአምስት ዓመት የእርስ በእርስ ግጭት እንደ የተባበሩት መንግሥታት መግለጫ መሠረትም 2.4 ሚሊዮዮን በብዛት ሕጻናት የሚገኝበት የአገሪቱ ሕዝብ ለከፋ ሰብአዊ አደጋ ከማጋለጡም አልፎ የብዙ ሕዝብ ሕይወት የቐጨ መሆኑ ሲታወቅ፣ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተሟልቶ እግብር ላይ ውሎ በአገሪቱ የተሟላ ሰላም ለማረጋገጥ ጉዞው ረዥም ቢመስልም ወደ የተሟላ ሰላም የሚሸኝ አዲስ ምዕራፍ መሆኑ ይነገራል።

የተባበሩት መግንሥታት ድርጅት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን ስለ ተደረሰው ስምምነት የተሰማቸው ደስታ ሲገልጡ በእውነቱ ይኽ የተገኘው መልካም እድል ባክኖ እንዳይቀር የሁሉም የሊቢያ ዜጎች አስተዋጽኦና የሁሉም አገሮች ትብብር ያሻዋል ሲሉ። የኤውሮጳው ኅብረት በበኩሉም ለሚጸናው የአገራዊ አድነት መንግሥት ተጨባጭ ድጋፍ ለማቅረብ ዝግጁነቱ ይፋ አድርገዋል።

በሊቢያ የሚረጋገጠው ሰላም የስደተኛው ጸአት ጉዳይ መፍትሔ እንዲያገኝ በማድረጉ ሂደት አቢይ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ነው ሲሉ በሮማ ሊውስ መንበረ ጥበብ የሥነ ዓለም አቀፍ ጉዳይና የሥነ ሰብኣዊ መብትና ክብር ጉዳይ መምህር ፍራንቸስኮ ከሩቢኒ የተደረሰው ስምምነት በማስደገፍ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስተያየት ሰጥተዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.