2015-10-07 15:57:00

ሲኖዶስ፦ እ.ኤ.አ. የጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. አንደኛው ውሎ የሲኖዶስ ክፍለ ጉባኤ


በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በሲኖዶስ የጉባኤ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ያለው አስራ አራተኛው ጠቅላይ መደበኛው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከአራት ሰዓት ተኩል እስከ ሰባት ሰዓት የሲኖዶስ የውይይት ማካሄጃ ሰነድ ቀዳሜ ክፍል ላይ በማተኮር ተከናውኗል፣ እርሱም በካቶሊካዊው አንቀጸ እምነት የሚገለጠው የምሥጢረ ተክሊል አስፈላጊነት ያስታወሰና ቤተ ክርስቲያን አወንታዊውነት ያለው የወቅታዊው ማኅበረሰብ ገጽታ መመልከት እንደሚገባት ያሳሰበና ይኽ ደግሞ የሺዩንስታት ሓዋርያዊ እንቅስቃሴ መሥራች አባ ከንተኒኽ “ቤተ ክርስቲያን ጀሮዋ በእግዚአብሔር ልብ እጆችዋን ደግሞ በጊዜ ትርታ ወይንም ህርመት ላይ ታኑር” ሲሉ የገለጡት ሓሳብ የሚያስተግባ መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ከዚህ በመንደርደርም የሲኖዶሱ ውሎው ቤተሰብና በተለይ ደግሞ ቤተሰብ በዚህ ወቅታዊው ዓለም በሚደቅነው ተዛማጅና ግለኝነት ተግዳሮት ፊት ለመሸኘት የሚያበቃ አዲስ አግባብ የሚከተል ርህራሄና መስተንግዶ የሚያጣምር ማርያማዊ ገጽታ ያለው አስፍሆተ ወንጌል ያለው አስፈላጊነት እንዳሰበመረበት የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ በዚህ ሁሉም ነገር ፈጣንና ቅጽበታዊ በሆነበት ዓለም ቤተ ክርስቲያን ወደ አቢይ ፍስሃ ያቀና ረዥምና እርቁ ወደ አነጣጠረው ሂደት እርሱም ቤተሰብን ወደ የእግዚአብሔር እቀድ ለመሸኘት የምታገለግል ነች፣ ለዚህም ቤተ ክርስቲያን ቤተሰብና ጋብቻን የሚቀናቀን ለቤተሰብና ለጋብቻ አዲስ ትርጉም የሚሰጥ ርእዮተ ዓለማዊ መዝገበ ቃላት በብቃትና በሚገባ ለመግጠም በወቅታዊው ቋንቋ ማሰብና ማሰላሰል ይጠበቅባታል ማለቱንም አስታውቀዋል።

ከዚህ ጋር በማያያዝ ባልና ሚስት ባለ ትዳሮች በእምነትና በሚሥጢረ ተክሊል ግንዛቤ በሳል እየሆኑ እንዲያድጉ መደገፍ ያለው አስፈላጊነት ማለትም በትዳር ታማኝነት ያላው ክብርና ይኸንን ክብር በማስተዋል አቅቦ ለመኖር እንዲችሉ ለትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች ምስጋና ይሁንና ቀርቦ መደገፍ ያስፈልጋል። ስለዚህ ገና ለመጋባት ሲዘጋጁና ከተጋቡም በኋላ መቼም ቢሆን ድጋፉ ቀጣይ መሆን አለበት። ወጣቶች ደግሞ የፍቅር ውበትና በፍቅርና በትዳር መካከል ያለው ውስጣዊ ትስስር እንዲገነዘቡና ለይተው እንዲያውቁ መደገፍ ይኖርባቸዋል። ይኽ ክብር በባህል ዘርፍ እንዲሰርጽም ቤተ ክርስቲያን ያለባት የማነጽ ኃላፊነት መወጣት ይኖርባታል፣ ክርስቲያን ትምህርት ቤቶች የተስፋና የደስታ ቤተሰብ ለማሰናዳት የሚችሉ ሥፍራ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

ሌላው ርእስ፦ በቤተሰብና በተልእኮ መካከል ያለው ግኑኝነት ነው። በቤተ ክርስቲያንና ለቤተ ክርስቲያን ሕይወት የወንጌላዊ ልኡካን ቤተሰቦች ምስክርነት አስፈላጊ ነው። ቤተሰብ በዚህ ተልእኮ በሚገባ የተሰናዳ እንዲሆን ሕንጸት ማግኘት ይኖርበታል። ምክንያቱም ወንጌላዊ ልኡካን ቤተሰብ የሚሰጡት ምስክርነት ታማኝና አሳማኝ እንዲሆ የሚደግፍ ነው። ለቤተሰብ የሚቀርበው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጽኑና ቀጣይነት ያለው መሆን አለበት። ለቤተሰብ የሚቀርበው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ይኽም የሕይወት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ሆኖ መለወጥ እንዳለበት በማስተዋል ነው። ስለዚህ ቤተሰብ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነውና መቼም ቢሆን ተስፋ እንዳይቆርጥ ማበረታታት አስፈላጊ መሆኑ ውሎው እንዳሰመረበት የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ቤተክርስቲያን እናትና መምህር በመሆንዋም ማንንም ካለ መፍረድ በተወሳሰበ የትዳርና የቤተሰብ ችግር የሚገኙትን ለቤተሰብ አባላት ሁሉ ቅርብ በመሆን የምትደግፍ ጓደኛና ወዳጅ መሆኗ ውሎው በማሳሰብ፣ የመውደቅ ገጠመኝ ያጋጠመውን ሁሉ በትዕግስት በምህረትና በተለይ ደግሞ በእውነት የዘወትር እይታዋ በእግዚአብሔር ላይ ያነጣጠረ ድጋፍ በማቅረብ ቤተሰብና የቤተሰብ አባላት መሸኘት አለባት እንዳለ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

የሲኖዶስ አበው በቤተሰብ ውስጥ የሚታየው ድኽነት በድኽነት የተጠቃውና የሚጠቃው ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ በመምከር፣ የሰብአዊ መብትና ክብር ብሎም የጋራ ጥቅም በማነቃቃት በማኅበራዊነት በማኅበረሰብአዊነት ደረጃ በድኽነት የተጠቃውን ቤተሰብ ድጋፍ ማቅረብ፣ ይኽ ደግሞ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የዚህ ዓይነቱ በመደጋገፍ ተግባር አማካኝነት ለኅብረተሰብ መልካም ለውጥ ቀንደኛ ተወናያን እንዲሆን ያግዘዋል። ቤተሰብ የትብብር እውነተኛ ትምህርት ቤት ነች፣ ይኽ ማለት ደግሞ በኤኮኖሚያዊ ግምገማ ሳይሆን የክርስትና ሕይወት የሚኖርባት ቤተኛ ቤተክርስቲያን ትንሽ ቁምስና በመሆንዋ ምክንያት ነው።

ሌላው ነጥብ፣ በቤተሰብ ውስጥ የሚታየው ዓመጽ መቃወምና መዋጋት በገበያው ዓለም የሚቸረቸረው ሥነ ምግባር በመከተል ሳይሆን የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብርና መብት ብሎም ማኅበራዊ እድገት በማነቃቃት ቀርቦ በመመልከት መፍትሔ እንዲያገኝ ቀዳሜ ሆና መገኘት ያለው አስፈላጊነት በማስተንተን፣ በክርስቲያን ሴቶች ላይ የሚፈጸመው በደልና አመጽ ወይንም በውሁዳን ሃይማኖት አባላት በሆኑት ሴቶች ላይ የሚጣለው አመጽ የሚፈጸመው የወሲብ ዓመጽና እገታ ታማጽያኑ ሴቶች በመላ የሕይወት ዘመናቸው ጥሎት የሚያልፈው ስነ አእምሮአዊና አካላዊ ጠባሳ የሚያኖርባቸው አሰቃቂው ግፍ መዋጋትና ለእነዚህ የቤተሰብ አባላት የተሟላ ድጋፍ ማቅረብ። ከዚህ ጋር በማያያዝም በጨቅላነት እድሜያቸው ገና ላቅመ አዳምና ላቅመ ሄዋን ሳይደርሱ ለሥራው ዓለም የሚዳረጉት ዜጎች ርእሰ ጉዳይ በማስተንተን፣ ለዚህ ተግባር የሚዳርገውም ምክንያት አንዱ ድኽነት ነው። የዚህ ዓይነት ጸረ ሰብአዊ ተግባር የቤተሰብ መለያየት የሚያስከትለ ሲሆን፣ ስለዚህ በተገባ ሕግ ጉዳይ መዋጋት ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲያን በዚሁ ርእስ ዙሪያ ተገቢ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለማከናወን መጠራቷ የሲኖዶስ አበው እንዳሳሰቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ልጅ ለመውለድ ያልታደለች ቤተሰብ መንፈሳዊ ወላጅ መሆን ያለው ክብር እንድትገነዘብ ማነጽና ወላጅ አልባ የሆኑትን እንድታሳድግ ማበረታታት፣ ከዚህ ጋር በማያያዝም በእድሜ ለገፉት ለቤተሰብ አባላት ለወላጆችና ለአያቶች ለሚቀርበው ድጋፍ ደጋፊ ሆኖ መሸኘት ብቻ ሳይሆን ተዘክሮ መሆናቸው ግንዛቤ በመስጠት ያላቸውን ክብር እንዲስተዋል የሚያግዝ ድጋፍ ማቅረብና ለወጣት ትውልድ በእምነት ሕንጸት ያላቸው ክብር እውቅና መስጠት እንደሚያስፈልግም ውሎው አስታውሶ ከራስ ጋር ተመሳሳይ ወደ ሆነው ጾታዊ ስሜት ግፊት ያላቸው የቤተሰብ አባላት የቤተ ክርስቲያን አባላት ናቸው፣ ሆኖም ምሥጢረ ተኪል የቤተሰብና የሰው ምሉእነት መሠረት የሆነው በወንድና በሴት መካከል የሚጸና ቅዱስ ምሥጢር መሆኑ መቼም ቢሆን የማይዘነጋ መስተንግዶ ማቅረብ።

የሲኖዶሱ ውሎው በመጨረሻም በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል በሚደረገው የጋራ ውይይት ቤተሰብ ያላው ሚና ላይ በማተኮርና ይኽ ደግሞ በተለያዩ የሃይማኖት አባላት መካከል የሚፈጸመው ቅይጥ ጋብቻ ቀርቦ በመመልከት ድጋፍ ማቅረብ የሚያግዝ መሆኑ ያሰመረው ሲኖዶስ፣ በመጨረሻም ዕለት በዕለት ቤተሰብ በመደገፍ በማነጽ በማበረታታት አገልግሎትና በቤተሰብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተጠምደው ክህናታዊ ጥሪያቸውን የሚኖር ካህናት የሚሰጡት አገልግሎት አቢይ መሆኑ እውቅና በመስጠት ውሎው መጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.