2015-10-05 15:07:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ትህትና ጽኑ መከታ ነው


ገዛ እራሳችንን በብቃት ለመከላከል የከበረው ገድል በእግዚአብሔር ድጋፍ የሚኖር ትህትና ነው። ዲያብሎስ ሃብት ትምክህትና ሥልጣን በተሰኙት መንገዶች የሚፈትን መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራችነስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 3 ቀን 2015 ዓ.ም. እንደ ተለመደው በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኃይል አባላት ያሳተፈ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በለገሱት ስብከት እንዳሰመሩበት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ገለጡ።

የዲያብሎስ ወጥመድ

ቅዱስ አባታችን ጥበቃና መከላከል ላይ ባነጣጠረ ተልእኮ በቅድስት መንበርና በአገረ ቫቲካን አገልግሎት የሚሰጡት ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኃይል አባላት ያንን ከዮሐንስ ራእይ የተወሰደው የዕለቱ አንደኛውን ምንባብ ጠቅሰው በእግዚአብሔርና በዲያብሎስ መካከል የተነሣው ጦርነትና እንዲሁም የዕለቱ ወንጌል ኢየሱስ በዲያብሎስ መፈተን የሚያወሳው መልእክት ላይ በማተኮር የዲያብሎስ ወጥመድ ምን ተመስሎውን በማብራራት፣ ጌታ ከዚህ የዲያብሎስ ወጥበት እንዲጠብቀን እንጸልይ።

ምድራዊ ኃብት ለምግባረ ብልሽት በቀላሉ ይዳርጋል

ያጥንታዊው ፈታኙ እባብ ለሰው ልጅ መሠረታዊ አስፈላጊ የሆኑትን ዳቦ ንብረትና መርህነት ተገን በማድረግ አወንታዊ ባህርያቸውን ቀየር በማድረግ ሰውን ለመፈተን ይጠቀምባቸዋል። በዓለም ምግባረ ብልሽት እጅግ ተስፋፍቶ ይታያል፣ ይኽ ደግሞ ብዙዎች መንፈሳቸውን ለዲያብሎስ በመሸጣቸው ነው።

ትምክህትና ትዕቢት

ዲያብሎስ ጌታችንን ወደ ተራራ እንዲወጣ በማድረግ ገዛ እራስህ ከዚህ ወደ ታች በመወርወር መለኰታዊ ግርማህ አሳይ ሲል፣ የእዩልኝ ፈተና ያቀርብለታል፣ ሶስተኛው ፈተና ደግሞ ትዕቢት፣ ሁሉም በእግርህ ስር ይገዛልህ ዘንድ የዓለም ሥልጣን ይኸውልህ ተገዛልኝ ሁሉም ይገዛልኃል፣ ይኽ ደግሞ ለብዙዎቻችን የሚያጋጥም ፈተና ነው፣ ሲያከብሩን ሲወድሱን ደስ እንሰኛለን፣ እንመካ ዘንድ ያደርገናል፣ ገዛ እራስህ እንደ እግዚአብሔር ማሰብ፣ ትልቁ ፈተናም ይኽ ነው። ጌታ ነኝ ማለት።

ምርጫው ትህትና መሆን አለበት

ሁሉንም ዲያብሎሳዊ ዓይነት ፈተና ገጥሞ ለማሸነፍ እንደ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል በመጠቀም ከዲያብሎስ ጋር ውይይት እንደማያስፈልግ አምኖ ትህትናን መኖር ነው። ቅዱስ አባታችን ጳጳሳዊ የስዊዝ ዘብ አባላት የጌታ መልካምነት በዓለም መስካሪያን እንዲሆኑ ትህትና እንዲኖሩ አሳስበው፣ የእነዚህ የጸጥታ ኃይል አባላት አገልግሎ ከባድ መሆኑም ገልጠው አገልግሎታቸውን በሚገባ እንዲወጡ ቅዱስ ሚካኤል መልአክ አማላጅነት እንዲጸልዩና እርሱም ከሁሉም ዓይነት ፈተና እንዲጠብቃቸው በትህት እንዲኖሩ በእምነት ነቅተው እንዲገኙ አደራ ብለው የለገሱት አስተንትኖ እንዳጠቃለሉ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.