2015-10-02 15:54:00

አባ ተስፋዬ ታደሰ የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ የመጀመሪያ አፍሪቃዊ የኮምቦኒ ማኅበር 14ኛው ጠቅላይ አለቃ ሆነው ተመረጡ


በመላ ዓለም ከሚገኙት የኮምቦኒ ልኡካነ ወንጌል ተጠሪ አለቆችና የማኅበር ጠቅላይ አለቃና አማካሪዎች በሮማ 18ኛው ጠቅላይ ጉባኤ እያካሄዱ መሆናቸው ሲገለጥ፣ እ.ኤ.አ. መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ተጋባእያኑ ማኅበሩ በጠቅላይ አለቃነትና እንዲሁም የጠቅላይ አለቃ መማክርት በመሆን ያገለገሉት የአገልግሎት ተልእኮ ዘመናቸውን ላጠናቀቁት የሚተኩ ጠቅላይ አለቃና መማክርት ለመምረጥ ባካሄደው የምርጫ ሥነ ሥርዓት አማካኝነት በምልኣተ ድምጽ ኢትዮጵያዊው የማኅበሩ አባል ባለፉት ስድስት ዓመታት የማኅበር የመሠረተ ሕንጸት የመላ ያፍሪቃ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተጠቃሚ አገሮች ጉዳይ ለጠቅላይ አለቃ አማካሪ በመሆን ያገለገሉት አባ ተስፋዬ ታደስ ገብረስላሴን መርጠዋል።

ኣባ ተስፋዬ ታደሰ በኢትዮጵያ ሐረር ክፍለ ሃገር እ.ኤ.አ. መስከረም 22 ቀን 1969 ዓ.ም. የተወለዱ ገና የሦስት ወር ሕፃን እያሉ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ አዲስ አበባ ተዛውረ በአዲስ አበባ ያደጉ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 26 ቀን 1995 ዓ..ም. ማዕርገ ክህነት የተቀበሉ ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ የሥነ ምስልምና የጥናት መንበረ ጥበብ ሊቅነት ያሰመሰከሩ መሆናቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ አባ ተስፋዬ ታደስ የአረብኛ ቋንቋ በሚገባ ለማወቅ ወደ ግብጽ ከተላኩ በኋላ ከ 1997 ዓ.ም. ጀምረው ለሦስት ዓመት በካርቱም ያገለገሉ መሆናቸው ጠቅሶ፣ አባ ተስፋዬ የመጀመሪያ ኢትዮጵያው ብቻ ሳይሆኑ የመጀመሪያ አፍሪቃዊ የማኅበሩ 14ኛው ጠቅላይ አለቃም ናቸው።

አባ ተስፋዬ ለዚህ አዲስ ተልእኮ እንደተመረጡም ሚስና የዜና አገልግሎት ላቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ ሲመልሱ፦ ዳኒኤል ኰምቦኒ በሳቸው መመረጥ ሳይሆን ማኅበሩ የመጀመሪያ አፍሪቃዊ ጠቅላይ አለቃ በማግኘቱ ምክንያት ደስተኛ እንደሚሆን ነው ብለው ለእኔና የምወክለው ተልእኮም አንጻር የተሰጠኝ ተልእኮ ትልቅ ኃላፊነት ነው፣ አፍሪቃውያን የማኅበሩ አባላት መሆን ከጀመሩ ቆይተዋል፣ ሆኖም ማኅበሩ ጠቅላይ አለቃ በማድረግ አንድ አፍሪቃዊ ሲመርጥ ለመጀመሪያ ጊዜው ነው። አሁን አፍሪቃ ቤተኛ ነች። የቅዱስ ዳንኤል ኮምቦኒ ልጆች ወንድሞቼ በእኔ ላይ ያላቸው እምነት አድሰዋል፣ ኮምቦኒ ለአፍሪቃ ከነበረው ፍቅር አንጻር በእውነቱ ደስ እንደሚሰኝ ነው። ከአንዲት በአፍሪቃ ከምትግኘት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውሁዳን ለሆኑበት አገረ ኢትዮጵያ ዜጋ ነኝ። ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ትንሽ ብትሆንም መላይቱን አፍሪቃ ለመወከል በቅታለች።

እንደ ኮምቦናውያን መጠን በድኽነት ለተጠቁት ድኻ እንዲሆን ለተገደደው ለተናቀው የወንጌል ኃሴት ለማካፈል የተጠራን ነን፣ ይኽ የተልእኮው ባህል ዳግም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እያሳሰቡት ካለው የወንጌል ኃሴት በሚል ርእስ ሥር ባቀረቡት ሐዋርያዊ ምዕዳን ዳግም በታደሰ ኃይለኛ መንፈስ የሚቀጥል ነው ብለው ማኅበሩ በኤውሮጳ እያከናወነው ያለው ተልእኮ ምን ተመስሎውን ገልጠው የኮምቦኒ ማኅበረ አባላት በኤውሮጳ የሚገኙባቸ አገሮች ጠቀስ በማድረግ ኤውሮጳ ልኡካነ ወንጌል የሚያስፈልጋት አገር መሆንዋ እየተካሄደ ያለው ስብሰባ እንዳሰመረበትም አስታውሰው፣ ከአገር ተልቆ የሚሰጥ አገልግሎት ሳይሆን ማኅበሩ ካለው ዓለም አቀፋዊነት ባህርይ የሚነቃቃ ተልእኮ መሆኑ አብራርተው፣ ማኅበሩ በአሁኑ ወቅት ለስድተኞችና ተፈናቃዮች በመስተንግዶ በመጀመሪያ የእርዳታ አቅርቦትና በሕንጸት ዘርፍ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ አብራርተው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.