2015-09-30 15:49:00

ብፁዕ ካርዲናል መኒከሊ፦ ካቶሊካዊ ፍች ትርጉም አልቦ አባባል ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በፊላደልፊያ በተካሄደው ስምንተኛው ዓለም አቀፋዊ የቤተሰብ ዓውደ ጉባኤ በመሳተፍ እንዲሁም እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ከመላ ዓለም የተወጣጡ ብፁዓን ጳጳሳት ታጅበው በሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ የሚጀመረው ቤተሰብ ማእከል ያደረገ ሲኖዶስ፣ በሳቸው ሐዋርያዊ ዝክረ ነገር ቤተሰብ ማእከል መሆኑ የሚያረጋግጥ ነው። ቤተሰብ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከቤተ ክርስቲያን ውጭ በተለያየ መልኩ የሚሰጠው ትኵረት የሁሉም ፍላጎት መስኅብ መሆኑ አያጠያይቅም።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ያካሄዱት ዓለም አቀፋዊ ዑደት አጠናቀው ወደ አገረ ቫቲካን በተነሱባት አይሮፕላን ውስጥ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ በተለይ ደግሞ አንድ ጋዜጠኛ ቅዱስነታቸው በቅርቡ ያጸደቁት በቤተ ክርስቲያን ምስጢረ ተክሊል ያሰሩት እንዲፈታላቸው ለሚያቀርቡት ጥያቄ በቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤት ተጢኖ ይሻር ወይን አይሻርም ብሎ ለመበየን የሚፈጀው ጊዜ ረዥም በመሆኑ የተቀላጠፈ አሠራር እንዲኖረው የሚያሳስብ ውሳኔ ካቶሊካዊ ፍች በሚል ሃሳብ በተለያዩ የመንገናኛ ብዙኃን እየተገለጠ ስላለው ጉዳይ ምን ይላሉ ሲል ላቀረበላቸው ጥያቄ ካቶሊካዊ ፍች ብሎ ነገር የለም ምስጢረ ተክሊል አይፈታም የማይሻር ቅዱስ ምስጢር ነው። በማለት የሰጡት መልስ ላይ በማተኮር በኢጣሊያ የአንኰና ኦሲሞ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኤድዋርዶ መኒከሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እያቀረቡት ያለው ሓሳብ እርሱም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የምታቀርበው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ወቅታዊው ዓለም ግምት የሚሰጥ ወቅታዊው ዓለም ከሚያቀርበው ተጋርጦዎች ጋር ለመግጠም የሚችልና ተገቢ መልስ የሚያቀርብ መሆን አለበት የሚል ነው። ቤተ ክርስቲያን ሰው በማንኛው ዓይነት የሕይወት ሁነትና ደረጃ ቢገኝም ቀርባ ለመደገፍ የተጠራች ነች፣ በቤተ ክርስቲያን ቃል ኪዳን አስረው በፍትሐ ብሔር የተፋቱ ሌላ ትዳር መሥርተው የሚኖሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች አሉ። ሕገ ቀኖና ግልጽ ነው። ለተሰራው ምስጢረ ተክሊል ይፈታ እንዲባል የሚያደርጉት ምክንቶች በዝርዝር አስቀምጦታል። ስለዚህ አዲስ ነገር የለም፣ ኅዳሴው የቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤቶች የይፈታልኝ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚከተሉት የፍርድ ቤት አሰራር እንዳይንዛዛ ረዥም እንዳይሆን በሚል ሃሳብ ላይ የጸና ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.