2015-09-18 16:36:00

የቅድስት መንበርና የሉሰምበርግ ግኑኝነት


እ.ኤ.አ. መስከረም 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባትችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አገረ ቫቲካን ለጉብኝት የገቡትን የሉሰምበርግ መራሔ መንግስት ኻቪየር በተል ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ያሰራጨው መግለጫ ይጠቁማል።

መርሔ መንግሥት በተል ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ተሰናብተው በቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ፖል ሪቻርድ ጋላገር ከተሸኙት ከቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ጋር መገናኘታቸው የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ፦ በተካሄዱት ግኑኝነቶች የሁለቱ አገሮች የተዋጣለት መልካም ግኑኝነት የተናቁትን በድኽነት የተጠቁትን ስደትኞችና ተፈናቃዮችን በመደገፍ ተግባር እጅግ በበለጠ ለማጠናከር ያለው አስፈላጊነት፣ የሃይማኖት ነጻነትና መንፈሳዊ እሴት ማክበር ለማኅበራዊ ጣምራነት መሠረት መሆኑ እንደተሰመረበት ያመለክታል።

ግኑኝነቱም ሉሰምበርግ የኤውሮጳ ኅበረት ተረኛ ሊቀ መንበር መሆን ትኵረት የሰጠ እንደነበርና ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ ኤውሮጳዊ ብሎም ዓለም አቀፍ ነክ ጉዳዮች ላይ በማነጣጠር በተለይ ደግሞ ግጭት ጦርነት የስደተኛ ጸአት፣ ንኡሳን የማኅበርሰብ አባላት ንኡሳን ኃይማኖቶች መብትና ነጻነት በተሰኙት ርእሰ ጉዳዮች ሰፊ ውይይት መካሄዱ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.