2015-09-16 16:10:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዓለም አቀፋዊ ዑደት


የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ እ.ኤ.አ. መስከረም 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከመስከረም 19 ቀን እስከ መስከረም 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በኩባና በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የሚያካሂዱት አስረኛው ዓለም አቀፋዊ ዑደት ርእስ ዙሪያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መንፈሳዊው ዑደቱ፦ ረዥን የተወሳሰበ ነገር ግን እጅግ የተዋበ ጉዞ በማለት እንደገለጡት የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጃንካርሎ ላ ቨላ አስታወቁ።

አባ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በመቀጠልም ቅዱስነታችቸ ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በኩባ ያካሄዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት በማስታወስ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኩባ በሚያካሂዱት ዑደት ሃቫናን ሆልጉይንና ሳንቲያጎን እንደሚጎበኙ ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአብዮት አደባባይ ኾሰ ማርቲ መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው በኵባ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተስፋና የማደግ ምልክት የሚል ትርጉም ያለው ለአምስት ሕጻናት ቅዱስ ቁርባን ይሰጣሉ እንዳሉ ላ ቨላ ገለጡ።

ምንም’ኳ በእቅድ ባይያዝም በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና በኵባው አዛውንቱ ነበር ርእሰ ብሔር ፊደል ካስትሮ መካከል ግኑኝነት ሊካሂድ ይችላል። ከወጣቶች ጋር በሃቫና ከዛም በዚያች ቅድስት ድንግል ማርያም ዘፍቅር ደል ኮርበ የኵባ ጠባቂ ቅድስት ተብላ የታወጀችበት ዝክረ 100ኛው ዓመት ምክንያት በሳንትያጎ በመጨረሻም ከኵባ ቤተሰብ ጋር በመገናኘት የኵባ ሐዋርያዊ ዕደታቸውን አጠናቀው ወደ ዋሽንገትን እንደሚነሱ የአባ ሎምባርዲ መግለጫ የጠቀሱት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ላ ቨላ አያይዘው፦ በዋሽንግተን በርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ አቀባበል ተደርጎላቸው የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ሐዋርያዊ ዑደታቸውን በይፋ ይጀምራሉ። በዋሽንግተን ለብፁዕ ኹኒፐሮ ሰራ ቅድስና ለማወጅ የሚያርገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ይመራሉ። በሚቀጥለውም ቀን በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ሕዝባዊ ምክር ቤት ተገኝተው ለሕዝብ ተወካዮች ንግግር በማስደመጥ በአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ንግግር ያስደመጡት ቀዳሜ ር.ሊ.ጳ. እንደሚሆኑም ነው። ከዛም ኔው ዮርክ በመሄድ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ንግግር ያስደምጣሉ፣ መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም. ባሸባሪያን ጥቃት የወደመውን የብዙ ሰው ሕይወት ለሞት የተዳረገበት በግራውንድ ዜር የሚል መጠሪያ ወደ ተሰጠው አደባባይ በመሄድ እዛው የሕሊና ጸሎት ያቀርባሉ፣ በፊላደልፊያ ለሚካሄደው ስምንተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ ለማስጀመር ወደ ፊላደልፊያ ይሄዳሉ። በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ዑደት ከእስረኞች በድኽነት ከተጠቁት የእገሪቱ ዜጎች በመገናኘት የተለያዩ ግብረ ሠናይ ለማነቃቃትና ቡራኬ ለመስጠት ሲሆን፣ በዚህ በኵባና በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ዑደት በኵባ 8፣ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት 18፣ በጠቅላላ 26 ንግግሮች እንደሚያስደምጡ የገለጡት አባ ሎምባርዲ አክለው ቅዱስታቸው እ.ኤ.አ. መስከረም 28 ቀን ወደ አገረ ቫቲካን ይነሳሉ እንዳሉ ላ ቨላ ገለጡ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም የላቲን አመሪካ ጉዳይ ለሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ፕሮፈሰር ጉዝማን ካሪኵይርይ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ 10ኛው የኩባና የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ሐዋርያዊ ዑደት በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ብዙዎች ይኸንን ሐዋርያዊ ዑደት ፖለቲካዊ አድማስ ያለው እንደሆነ አድርገው ሰፊ ትንተና እየሰጡበት ነው። ሆኖም ይኽ የቅዱስነታቸው ጉዞ ሐዋርይዊና ግብረ ኖላዊ ነው። ተልእኮ ነው። በክርስቶስ ፍቅር ሕዝቦችን በእምነት ለማጽናትና የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ቅርበት በቃልና በተግባር ለማረጋገጥ ነው።

ቅዱስነታቸው ለተናቁት ለተጠሙት ለተራቡት ለስደተኞች ቅርብ መሆናቸውና ሁሉም እያንዳንዱም ይኸንን ቅርበት እንዲኖር የተጠራ መሆኑና በተለይ ደግሞ መንግሥታት ለእነዚህ የኅብረተሰብ ክፍል ማእከል ያደረገ ሰብአዊነት የተካነ ፖለቲካ እንዲያረጋግጡ በመደጋገም ካለ መታከት የሚያቀርቡት ጥሪ ዳግም ለማስተጋባት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.