2015-09-14 19:21:00

ብፁዕ ሳሙኤል በነዲክት ዳስዋ የደቡብ አፍሪቃ የመጀመርያ ብፁዕ


የዛሬ ሃያ አምስት ዓመት በደቡብ አፍሪቃ ለእምነቱ ሲል የሞተው ብፁዕ ዳስዋ የትምህርተ ክርስቶስ መምህር እንደነበረና ለሥራውም እጅግ ታታሪና ቀናተኛ እንደነበረ ይመለከታል፣ ብፁዕ ዳስዋ ምእመንና የቤተሰብ አባት እንደነበረ በደቡብ አፍሪቃ ቤተክርስትያንም እንደ የመጀመርያ ብፁዕ ይታወሳል፣ ሥርዓተ ብፅዕናው ትናንትና እሁድ በቶሆያንዱ በሚባል የደቡብ አፍሪቃ ከተማ ተካሂደዋል፣ ሥር ዓቱን የፈጸሙት ደግሞ በቅድስት መንበር ስለቅዱሳን ጉዳይ የሚመለከት ማኅበር ኃላፊ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ነበሩ፣

ብፁዕነታቸው ባቀረቡት ስብከት የብፁዕ በነዲክት ዳስዋ ባህላዊ ስም “ጺማንጋድዞ” ሲሆን ትርጉሙም ተአምር መንክር ማለት ሲሆን እውነትም የብፁዑ ሕይወት የእግዚአብሔር ጸጋ ተአምር ሲሆን እ.አ.አ ሰኔ 16 ቀን 1946 ዓም ምባሄ በሚባለው ትንሽ መንደር ክርስትያ ካልሆኑ ቤተሰቦች ተወለደ፣ አራት ወንድሞችም ነበሩት፣ ወላጆቹ ሲሞቱ እርሱ የወንድሞቹ ኃላፊነት ወሰድ፣ በ17 ዓመቱ በነደቶ ሪዚማቲ የሚባል ትጉህ የትምህርተ ክርስቶስ መምህር ጋር ተገናኘ ወዲያውኑ የክርስትና እምነትን በመቀበል ተጠመቀ የክርስትና ስሙም በነዲክት እንዲሆን መረጠ፣ እርሻ ደስ ይለው ስለነበረም ችግረኞች በዚሁ ዘርፍ ይረዳ ነበር፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ሆነ ቀጥሎም የትምህርት ቤተ ሃላፊ ሆነ፣ ልጆቹም በትምህርትና በስፖርት እንዲዳብሩ አደረገ፣ በመንደሩም ቤተክርስትያንና ቤተትምህርት እንዲሠሩ አደረገ፣ በ30 ዓመት ዕድሜው ሻዲ ኤቨሊን ሞንያይ ከምትባል ትዳር መሥርቶ 8 ልጆች ወለደ፣ ከ1980 እስከ 1990 በቍምስናው ብዙ አገልግሎት በትምህርተ ክርስቶስም ይሁን በሥርዓተ አምልኮ አገልግለ. ነገር ግን በጥር ወር 1990 ሁኔታ ተቀያየረ እንደ አጋጣሚ በመንደሩ አንድ ተፈጥረአዊ የአየር መለዋውጥ አደጋ አጋጥሞ ብዙ ቤቶች ሲፈርሱ በመብረቅም ተቃጠሉ፣ የመንደሩ መሪዎች ጠንቋዮችን ሰብስበው ይህ የአንድ መጥፎ ሰው መርገም መሆን አለበት ጥፋተኛውን ሊያገኝ የሚችል አንድ ጠንቋይ ጠርተው አረሜናዊ ሥርዓቶች ለማካሄድ ሲዘጋጁ በነዲክት ግን እምነቴ ይህን ይቃወማል” ሲል ሁኔታዎች የባህርያ የንጐዳጓድና የበርቅ ጉዳይ ናቸው ብሎም ሊገልጥላቸው ይሞክራል፣

ነገር ግን በጣላቻና በመጠራጠር አንድ ቡድን መንገድ ላይ ይዞት እየጨፈጨፈና እየረገመ በድንጋይና በዱላ እየደበደቡ እንዲሁም የተፈላ ዋይ ሲያፈሱለት ሕይወቱ እስኪያፍልፍ ድረስ በጸሎትና በይቅርታ ታገለ፣ ሰማዕትነቱ ወዲያውኑ ብሩህ ሆነ፤ ብፁዕ በነዲክት የሚያስምረን ነገር ካለ በሕይወታችን የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እና የሕይወት ቃሉ እውነተኛ ምስክሮች እንድንሆን ነው ሲሉ አሳስበዋል፣  








All the contents on this site are copyrighted ©.