2015-09-14 15:36:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ሙስናና ግብረ ብልሽት ቅን ኤኮኖሚ በማነቃቃት መዋጋት


እ.ኤ.አ. መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሮማ የአበዳሪዎችና የትብብር ባንክ ቤቶች በጠቅላላ 7 ሺሕ የሚገመቱትን በባንክ ቤቶች ሊቀ መንበር ፍራንቸስኮ ሊበራቲ የተሸኙትን ሠራተኞች በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው፦ ትብብርና ጸረ ሙስና ተግባሮችን በማራመድ ኤኮኖሚ ሰብአዊነታዊ ማድረግ በሚል ቅዉም ሓሳብ ላይ ያነጣጠረ መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረድዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ ገለጡ።

ቅንነት የተላበሰ ኤኮኖሚ

ጥንቃቄና ጤናማ የመስተዳድር ሂደት መቼም ቢሆን ለሁሉም አስፈላጊ ነው። ይኽ ደግሞ ቅንነት የተካነው ኤኮኖሚ እንዲስፋፋና እንዲበረታ ያደርጋል። በርግጥ የባንክ ቤት ሠራተኞችና በጠቅላላ ባንክ ቤቶች የሚሰጡት አገልግሎትና የሚያከናወኑት ሥራ ጥንቃቄና ሕጋዊነት የሚጠይቅ ነው። በዚህ በአሁኑ ወቅት በሁሉም ሥፍራ ሙስናና ምግባረ ብልሽት በሚታይበት ወቅት ቅን ኤኮኖሚ ማነቃቃት እጅግ አስፈላጊ ነው። ቅንነት በሁሉም ሥፍራና በሁሉም መስክ ማነቃቃትና መሠረት እንዲይዝ ማድረግ ያስፈላጋል እንዳሉ አኵይላኒ አስታወቁ።

እንደ ጣዖት የሚመለክ ገንዘብ ሳይሆን ሰውን ማእከል ማድረግ

የትብብር ባንክ ቤቶች ከሌሎች ባክን ቤቶች ለየት የሚያደርጋቸው ኤኮኖሚ ሰብአዊነት ማድረግ የሚለው የሁሉም ባንክ ቤቶች ዓላማ ትብብር የተሰኘ እሴት ስኬታማ ለማድረግ የተመሠረቱ በመሆናቸው ነው። ሰብአዊነትና ቤተሰብ ላይ ያተኮሩ ናቸው፣ ስለዚህ የኤኮኖሚው ሂደት ሰው እንጂ እንደ ጣዖት የሚመለከው ገንዘብ መሆን የለበትም፣ ሰውን የሚያዘው መዋዕለ ንዋይ ሳይሆን የመዋዕለ ንዋይን አዛዥ ሰው ነው ብለዋል።

በጋራ ስለ ሁሉም ለሁሉም

የኤኮኖሚ ተባባሪነትና ማሕበራዊነት የተሰኙትን ገጽታዎች ማረጋገጥ ያለው አስፈላጊነት ቅዱስ አባታችን ሲያሳስቡ ትብብር አንድ ወደር የማይገኝለት አቢይ ድርጅት ነው። ሆኖም በትብብር ላይ የጸና ድርጅት ዓላማው በጋራ ስለ ሁሉም ለሁሉም የሚል ነው። ስለዚህ የእነዚህ የትብብር ባንክ ቤቶች ተግዳሮት በጋራ ለሁሉም በተሰኘው የመተሳሰብና የመደጋገፍ የሚል ተግባር ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አክለው፦ የሚያጋጥሙትን ችግሮች በሚገባ ኃይል ለመግጠም በአሁኑ ወቅት ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ለተለያየ አደጋ የተጋለጡት ቤተሰቦችና ድርጅቶች የትብብር ባንክ ቤቶች ኃይላቸውን በማሰባሰብ ደጋፍያን ሆነው መገኘት እንጂ ሰውን ለገንዘብ ሃብት ማካበቻ መገልገያ መሣሪያ ለማድረግ መራወጥ አይገባቸውም እንዳሉ አስታውቀዋል።

ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል በተለይ ደግሞ በሥራ አጥነት በእጅጉ የተጠቃው ወጣቱ ትውልድ ለመደገፍ ያነጣጠረ የኤኮኖሚ እቅድ መደገፍ እንዳላበት ያሳሰቡት ቅዱስ አባታችን፣ ማኅበራዊ የድጎማ አበል ኤኮኖሚ ማነቃቃት ይኽ ደግሞ ጤና ጥበቃ ትምህርት የመሳሰሉት ለማኅበራዊ ጥቅም ያተኰሩ አውታሮች ሁሉ ለሁሉም በሚገባ አገልግሎት ለመስጠተ እንዲችሉ መደገፍ ካለው አስፈላጊነት ጋር በማያያዝ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጋር ትሥሥር ያለው አገልግሎት ለሁሉም መሆን አለበት፣ ስለዚህ ትብብርና መደጋገፍ ዓለማዊነት ትሥሥር መሆን አለበት እንዳሉ አኵይላኒ ገለጡ።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የለገሱት ምዕዳን ሲያጠቃልሉ፦ ቤተ ክርስቲያን ትብብርና መደጋገፍ የተሰኙትን እሴቶች በሚገባ የምታወቅ የዕለት በዕለት ገጠመኟ መሆኑም ገልጠው፣ ይኽም ካህናት ምእመናን በክርስቲያናዊ የትብብር መንፈስ ተነቃቅተው በጋራ ለጋራ ጥቅም የሚሰጡት አገልግሎት አሁንም በምንኖርበት ዓለም ትብብርና መደጋገፍ እንዲስፋፋ ማነቃቃት ነው፣ የጋራ ጥቅም በሁሉም መስክ ማስቀደም ያስፈልጋሉ እንዳሉ አኵይላኒ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.