2015-09-04 16:10:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ካህናት፣ የተናቁትንና የጠፉትን ለመደገፍ ጠንካራ ትከሻ ይኑራቸው


እ.ኤ.አ. መስከረም 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሺዩንስታት ሓዋርያዊ እንቅስቃሴ ኣባላት ካህናት ተቀብለው፦ ካህናት ከዚያ ልክ እንደ ኢየሱስ የሰብአዊ ፍጥረት የመጨረሻ ተብለው የሚገለጡት የተናቁትን ለመሸከምና ለመደገፍ የሚያበቃቸው ጠንካራ ትኸሳ እንዲኖራቸው የሚያደርገው ጸጋ ጋር የጸሎትና የአገልግሎት መንፈስ የተካኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል የሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ገለጡ።

እንደ ሙሴ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሸምጋዮች እንዲሆኑ በዚያ ያስተንትኖ ተራራ የሚወጡ በቀይ ባሕር ዳርቻ ሕዝበ እግዚአብሔር ከፈርኦን ጥቃት የሚከላከሉ እንደ ክርስቶስ  ማንም ዞር ብሎ የማያያቸው ላንዳፍታ እንኳ የሚመለከታቸው ለሌላቸው ቅርብ በመሆን ከሕዝብ ጋር በሕዝብ መካከል በመገኘት ሕዝቡን የሚያስፈልገውን ለመለየት የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል። አንድ ካህን ከሁሉም በፊት ቀድሞ የሚገኝ…

ከሥልጣን ጥማትና ሥልጣን ከመሻት አድነን

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እነዚህ የሹዩንስታት ካህናትን በአገረ ቫቲካን የዚያ የዛሬ 50 ዓመት በፊት በአባ ጆሰፍ ከንተኒኽ የተመሠረተው በካህናት ጥሪ እጅግ ባለ ጸጋ የሆነው እንቅስቃሴ አባላት ካህናት በብፁዓን ካርዲናሎች የጉባኤ አድራሽ ተቀብለው በለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን፦ የመጨረሻው የሚባለው ሥፍራ የካህናት መሆን አለበት፣ ካህን ፊተኛ ወይን የበላይ አይደለም ልክ እንደ ክርስቶስ ሕዝቡን በማፍቀርና ቅርብ በመሆን አብሮ ከሕዝብ ጋር የሚጓዝ የደከሙትን የሚደግፍ መሆን አለበት….ተስፋ አልቦ የሆኑትን ለመደገፍና ለመሸከም እንድንችል ከሥልጣን ጥማትና ሥልጣን ከመሻት ፍላጎት እንድንላቀቅ ጌታ ጠንካራ ትከሻ ይሰጠን ዘንድ ጸጋውን እንለምን።

መንፈሳዊ የተልእኮ መርሆ በብልቃጥ ውስጥ የሚታጎር አይደለም

እያንዳንዱ መንፈሳዊ ማኅበር መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ገዳማት ከመንፈስ ቅዱስ የተቀበሉት የተልእኮ መንፍሳዊ መርሆ ልክ እንደ አንድ ባህላዊ ቅርስ በቤተ መዘክር እንዲስተነተንና እንዲጐበኝ የሚቀመጥ አይደለም፣ መንፈሳዊው መርሆ ሳይበከል ማቀብ ማለት ባንድ ብልቃጥ ውስጥ ማጎር ማለት አይደለም፣ ከልሎ ማስቀመጥ ሳይሆን ከተጨባጩ ዓለም ጋር እንዲገናኝ ከሁሉም ሰዎች የተለያየ ችግር ካለባቸው ሰዎች ጋር የሚገናኝና የሚያገናኝ መሆን አለበት።

አለ ምንም ፍርሃት ከተጨባጩ አለም መጀመር

አንድ ካህን የሕዝብ ገጠመኝ የሚኖር በቅድሚያ ከእግዚአብሔር ጋር ጥብቅና ጥልቅ ግኑኝነት ያለው ከዚህ የመጀመሪያው ፍቅር በመንደርደር ይኸንን ፍቅር በጸሎት በመኖር ገዛ እራሱን በግብረ ሠናይ ተእልኮ አጥምዶ ለጸሎት ጌዜ የሌለው መሆን አይገባውም፣ እግዚአብሔር ከዚህ ዓይነቱ የግብራዊ ሞያ አገልጋይ ብቻ ሆኖ ከመገኘት ፈተና ያድነን፣ ጆሮአቸው በእግዚአብሔር ልብ እጆቻቸው በጊዜ ምት ላይ ያኖሩ መሆን ይገባቸዋል።

ተጨባጩን ዓለም አትፍሩ ተጨባጩን ሁነት እንደ መልካም ነገር ተቀበሉት፣ ከተጨባጩ ዓለም ለሚሰጠው አገልግሎት ምርጫ ምልክት ይገኛል፣ ወንድሞቻችን እህቶቻችን ጋር ስንገናኝ በተለይ ደግሞ ለእነዚያ በዓለም ዓይን የማይታዩት የተናቁ እምብዛም ትኵረት የማያገኙትን እግዚአብሔር እንደሚያፈቅራቸው የሚያረጋግጥላቸው ቅርበት መኖር ይገባናል፣ ምክንያቱም ያለባቸው ችግርና ሁነት ግድ ሳንሰጥ የክርስቶስ ተጨባጭ አካል መሆናቸው ማስተዋል ይኖርብናል።

ታላቅነታችን በምህረትና በይቅር ባይነት ላይ የጸና ይሁን

የክህነት ጥሪና ተልእኮ እጅግ ውብ የሚያደርገው ለብቻ ሲኖር አይደለም፣ በግለኝነት የሚኖር ሕይወት አይደለም፣ የወንድማማችነት መንፈስ የሚኖርበት ጥሪ ነው። አደራ በምህረትና በይቅር ባይነት ታላላቅ እንሁን። መሃሪያንና ይቅር ባይሆች እንሁን፣ ጌታ ሆይ ይቅር በለኝ ይቅር ብያለሁና። መመዘኛችን ባለንጀራችን ነው። በማለት የለገሱት መሪ ቃል ማጠቃለላቸው ደ ካሮሊስ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.