2015-09-02 16:21:00

የምሉእ ሥነ ምኅዳር አንገብጋቢነት


በካሪታስ ለሚጠራው ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር ቅርንጫ በኢጣሊያ አስረኛው የተፈጥሮ ጥበቃ ቀን ምክንያት በማድረግ፦ የምንኖርበት ዓለም ከቀን ወደ ቀን ያካባቢ አየር ብከላ እርሱም በሥነ ምኅዳር ቀውስ እጅግ እየተጠቃ ነው። ይኽ ቀውስ አንድ የተሟላ ሥነ ምኅዳር ያለው አስፈላጊነት የሚያበክር መሆኑ በስፋት የሚያብራራ የጥናት ሰነድ ማቅረቡ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጃኮሞ ዛንዶኒኒ አስታወቁ።

የተጠናቀረው የጥናት ሰነድ በማስደገፍ የካሪታስ ቅርንጫፍ በኢጣሊያ ምክትል አስተዳዳሪ ፓውሎ በቸጋቶ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ባለፉት የመጨረሻ ሰላሳ ዓመታት ወዲህ የታየው የተፈጥሮ ቀውስ፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ፣ ሃይለኛ ዓውሎ ነፋስ ወዘተ የመሳሰሉት የብዙ ሰው ሕይወት ለሞትና ለመቁሰል አደጋ የዳረጉት ለመፈናቀል አደጋ ያጋለጠው አለ ቤትና ንብረት ያስቀረው የተፈጥሮ አደጋ ክስተት በቁጥር ከፍ እያለ መምጣቱ ገልጠው፣ የባህር ከፍታ እጅግ እየጨመረ መምጣቱ የተለያዩ ወቅታዊ የሥነ ምርምር ጥናቶች እንደሚያረጋግጡት ጠቅሰው፣ የምድረ በዳ ክልል መስፋፋት የመሳሰሉት ሁሉ ግምት በመስጠት ለተፈጥሮ አደጋ መስፋፋትና ክስተቶች ምክንያት ከሚባሉት ውስጥ አንዱ የካባቢና የተፈጥሮ አየር ብከላ ነው። በመሆኑም ጥያቄው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደሚሉትም ሥነ ምህዳራዊ ጉዳይ የሚመለከት ሆኖ፣ ይሴባሕ በሚል አዋዲ መልእክታቸው ምሉእ ሥነ ምኅዳር አስፈላጊ መሆኑ በጥልቀት አስምረውበታል። የአካባቢ ጉዳይ የሚመለከተው ጥያቄ አካባቢያዊ ብሎም ሰብአዊ ማኅበራዊ ፖለቲካዊ ጥያቄ ነው ብለዋል።

የአካባቢ ጉዳይ የሚመለከት ጥያቄ የሕዝቦች ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር ለስደት የሚያጋልጥ ነው። ስለዚህ የሥነ ምኅዳር ቀውስ ሁሉን የሚነካ ፍጥረትና ተፈጥሮ ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ ነው። ለምሳሌ በኮንጎ የሚገኘው የተፈጥሮ ሃብት እጥቅም ላይ ለማዋል የተለያዩ የማእድ አውጭ ኢንዳስትሪዎች የሚከተሉት አሠራር አካባቢው በከፋ ሁኔታ እየበከለ ነው። ጉዳዩ የአካባቢ ብከላ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩም ማኅበራዊ ችግር ብሎም የጤና ጥበቃ ጉዳይ የሚመለከት ነው። እነዚህ ድርጅቶች ሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ለአደጋ መጋለጥ የዜጎች ጤና መታወክ ምክንያት ሆነው ይገኛሉ። ስለዚህ የሥነ ምኅዳር መቃወስ ሁሉን የሚነካ እንጂ አካባቢ ብቻ የሚመለከት ጉዳይ እንዳልሆነ አብራርተዋል።

የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የተፈጥሮ ጥበቃ ቀን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፈው መልእክት የበረሃማው ክልል መስፋፋት፣ በዓለም እየተከሰተ ያለው የውኃ እጥረት፣ የውኃ ብከላ አደጋ የመሳሰሉት ማእከል በማድረግ ይኸንን አደጋ ሁሉ ከሥነ ምኅዳር ቀውስ ጋር ያለው ግኑኝነት ላይ በማተኮር የሰጠው መግለጫ ምሉእ ሥነ ምህዳር ያለው አስፈላጊነት የሚያስዝገነዝብና ያለው አንገብጋቢነት የሚያሳስብ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.