2015-09-02 16:11:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ብፁዕ አቡነ ፓስቶረ፣ ጥበብና የጋለ ስሜት ለወንጌል


በራዲዮ ቫቲካን ለረዥም ዓመት እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ በመሆን ያገለገሉት ብፁዕ አቡነ ፍራንኮ ፓስቶረ እ.ኤ.አ. ነሓሴ 31 ቀን 2015 ዓ.ም. በ88 ዓመት ዕድሜያቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፔየትሮ ፓሮሊን ፊርማ የተኖረበት ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልእክት፦ ብፁዕ አቡነ ፓስቶረ ጥበብና የጋለ ስሜት ለወንጌል የኖሩ በማለት እንደገለጡዋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያስተላለፉት መልእክት የነፍሴ ኄር ብፁዕ አቡነ ፓስቶረ ለቀብር ሥነ ሥርዓት ሮማ በሚገኘው የካቶሊክ ተግባር ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ያረገው የፍትሃት መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ማሪያ ቸሊ ጋር በሁባሬ የተሳተፉት የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ኣቡነ ኑንዚዮ ጋላንቲኖ መሆናቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ በፍትሃት የቅዳሴው ሥነ ሥርዓት የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ሰርጆ ማታረላ፣  መሳተፋቸው ጠቅሶ ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ማሪያ ቸሊ ነፍሴ ኄር ብፁዕ አቡነ ፓስቶረ ባገለገሉት የቤተ ክርስቲያናዊ ተልእኮ ሁሉ ቸር የዋህ ጥበብ የተካኑ ነበሩ በማለት እንደገለጡዋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.