2015-08-31 14:54:00

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፦ ስደተኞች በተመለከተ ከመወቃቀስ ይልቅ ኃይላችን በማሰባሰብ ስለ እነርሱ ድጋፍና መስተንግዶ እንትጋ


ስድተኞች በተመለከተ የሚሰጠው አሉታዊ አስተያየትና መወቃቀስ ችግሩን የሚያባብስ ዜጎች ተማረው ስደተኛው እንደ ችግር ለመመልከት የሚገፋፋቸው ተግባር ነው። በመሆኑም በመዲትራኒያ የባህር ክልል የሚታየው በስደተኛው ላይ እያጋጠመ ያለው የሞት አደጋ የዕለት በዕለት ገጠመኝ ሆነዋል፣ ይኽ አይነቱ ዘግናኝ ስቃይና ሞት በመላመድ የማያዝኑ የማያነቡ ስለ ስደተኛው የማይቆረቆሩ ሆነን እንዳንገኝ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ሮማ በሚገኘው በጀመሊ አቢይ ሕክምና ቤተ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ለህሙማንና ለህክምና ቤቱ ሰራተኞች እ.ኤ.አ. ነሐሴ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት አደራ እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጓራሺ ገለጡ።

ብፁዕነታቸው ባሰሙት ስብከት በአሁኑ ወቅት በመታየት ላይ ያለው የስደተኛው ጸአት ከዚህ ቀደም ያልታየ አቢይ የሰብአዊ አደጋ ነው። ይኽ ዓለም አቀፋዊ ማኅበራዊ ክስተት በጥልቀት አጢኖ መፍትሔ ለማፈላለግና ለሚሰቃየውና ለሚሰደደው ሁሉ ኃይልና አቅም በማስተባብር ለመደገፍና ለመተባበር እንትጋ እንጂ መወቃቀሱ ትርጉም የለውም። የስደተኛው ጸአት የሚገታው ስደተኛውን ባለ ማስተናገድ ሳይሆን ባንጻሩ ለስደት የሚዳርገው መሠረታዊ ምክንያት መፍትሔ ማፈላለግ ነው። ስደተኛው ማባረር ፈጽሞ መፍትሔ አይሆንም፣ በሶሪያ በኢራቅ በመሳሰሉት አገሮች ያለው ሁኔታ እንመልከት፣ የምዕራቡ ዓለም የዚያ ክልል ውጥረትና ሁከት መፍትሔ እንዲያገኝ ምን እያደረገ ነው? የሚል ጥያቄ አቅርበው፣ ቤተ ክርስቲያን ስለ ስደተኛው በተመለከተ ጉዳይ አስተያየት ስትሰጥ በቃል ብቻ ሳይሆን ቀርባም ሰብአዊ ድጋፍ በማቅረብ ትገኛለች፣ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን ለምታካሂደው ትብብርና ደጋፍ ብሎም ስለ ስደተኛው የምታስተላልፈው መልእክት የጣልቃ ገብነት ተግባር ሳይሆን ወንጌላዊ ጥሪዋ ነው እንዳሉ ጓራሺ አመለከቱ።

ቤተ ክርስቲያን ስለ ስደተኛው በተመለከተ መልእክት ከማስተላለፍ አትቆጠበም፣ ሁሉም ለተሰደደው ዜጋ ትብብር እንዲያቀርብና የተከፈተ በርና ልብ እንዲኖረው አደራ ከማለት አትቦዝንም፣ ልዩነት ቅንና ተባባሪ ዓለም ለማነጽ ለሚደገፍ ግብረ ሰናይ የሚያበረታታ እንዲሆን ታንጻለች፣ ይኽ ደግሞ ወንጌላዊነት ነው። ይኸንን መፈጸም ማለት ጣልቃ ገብነት ነው ብሎ መግልጡ አቢይ ስህተት ነው እንዳሉ ጓራሺ አስታወቁ።

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ባስደመጡት ስብከት አገረ ቫቲካን ደካማው የሚጎዳው የሚሰቃየው ህሙማን ሁሉ በፖሊቲካው በኤኮኖሚውና በማኅብራዊው ዘርፍ ሁሉ አቢይ ትኵረት ሊደርግለት ይገባል፣ እነዚህን የኅብረተሰብ ክፍል ማእከል ማድረግ ስልጣኔ ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ ጥሪ ጭምር ነው። ይኽ አይነቱ ደካማዊ የኅብረተሰብ ክፍል ማእከል የማድረጉ ጥሪ ለምሉእ የሰብአዊ እድገት የሚበጅ ነው። ሰው ግብረ ሙያዊ ወይንም መንፈሳዊ አካል አርጎ ነጣጥሎ መመልከቱ ስህተት ነው እንዳሉ ይገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጋራሺ በማያያዝ ብፁዕነታቸው መሥዋዕተ ቅዳሴውን አሳራገው እንዳበቁም በጀመሊ ህክምና ቤት የሚገኘው በጡንቻ መስለል የሚሰቃዩትና እንዲሁም የሕጻናት የሕክምና ክፍል እንደጎበኙም አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.