2015-08-31 15:05:00

ብፁዕ አቡነ ባኛስኮ፦ የስደተኛው ጸአት እጅግ የሚያስደነግጥ አሳዛኝ ሁነት


የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ በሳቸው ሐዋርያዊ እረኝነት ሥር በሚመራው የጆኖቫ ሰበካ በመከበር ላይ ባለው የሁሉም ጠባቂ ቅድስት ድንግል ማርያም በዓል ምክንያት በጠባቂቷ እመቤት ቅዱስ ሥፍራ ተገኝተው ያረጋው መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው፦ ስደተኞች፣ ቤተሰብ፣ ሚሥጢረ ተክሊል፣ የኤኮኖሚ ቀወስ፣ በኢጣሊያ ደቡባዊ ክልል የሚታየው ሠራተኛ የመበዝበዙ ተግባር ማእከል ያደረገ ስብከት ማስደመጣቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ገለጡ።

የስደተኛው ጸአት ሰብአዊ ችግር ነው። ከዚህ ዓይነቱ ሰብአዊ ችግር ፊት ማንም የኤውሮጳ አገር ገዛ እራሱ ሊያሸሽ ወይንም ጀርባውን ሰጥቶ በቸልተኝነት ሊመለከተው አይችልም፣ ምንም’ኳ የዘገየ ቢሆንም ቅሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን መስከረም ወር 2015 ዓ.ም. በሚካሄደው በተባበሩት መግንሥታት ድርጅት ጠቅላይ ጉባኤ የስደተኛው ጸአት ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲወያይ ያቀረበቱ ጥሪ ተገቢ ነው ያሉት ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ አክለው፦

የስደተኛው ጸአት የሁሉም ኃላፊነት ነው

የጀርመን መራሔ መንግሥት አንገላ መርከል ወደ ኤውሮጳ የሚሰደደው ዜጋ በተመለከተ የስደተኛው ጸአት የሚያስደነግጥ አሳዛኝ ሁነት በማለት የሰጡት መግለጫ ከዚህ ቀደም የነበራቸው ፖለቲካዊ አስተያየት ወደ ጎን ያደረጉ ይመስላል እንዳሉ ደ ካሮሊስ ገለጡ።

ቤተሰብ፦ አባት እናትና ልጅ

የግል ሰብአዊ መብትና ክብር አየተባለ እየተስፋፋ ያለው አዲስ የቤተሰብ ትርጉም በተመለከተ ቤተ ክርስቲያን ያላት አስተያየት የማያሻማ ነው። ቤተሰብ ሲባል አባት አናትና ልጅ የሚያጠቃልል፣ ይኽ ደግሞ የኢጣሊያ ህገ መንግሥት በትክክል የሚገልጠው ሃሳብ ነው። ስለዚህ ይኽ በቃል ኪዳን የሚጸናው የአንድ ወንድና አንዲት ሴት ጋብቻ ልጅ ለመውለድ ባህርይ ክፍት ነው። በተለያየ በሽታ ምክንያት ልጅ መውለድ ሊያዳግት ይችላል፣ ሆኖም ጋብቻ በመሠረቱ ልጅ ለመውለድ ባህርይ ክፍት ነው። ቤተሰብ የማኅበርሰብ የኅብረተሰብ ማእከል ነው፣ ልጅ ይወለዳል እንጂ አይመረትም እንዳሉ ደ ካሮሊስ ገለጡ።

ሠራተኛ የመበዝበዙ ተግባር ያብቃለት

በኢጣሊያ ደብባዊ ክልል በሠራተኛ ላይ በተለይ ደግሞ በእርሻ ሥራ በሚሰማሩት ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ብዝበዛና የሚያጋጥም የሞት አደጋ እንዲያበቃለትና መንግሥት የእነዚህ ሠራተኞች ደህንነት ሰብአዊ መብትና ክብር ዋስትና እንዲያሰጥ ያላሰለሰ ጥረት እንዲያደርግ ኃላፊነት አለበት ብለው ተከስቶ ካለው የኤኮኖሚ ቀውስ ለመላቀቅ ባለ ሃብቶች በኢጣሊያ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያውሉ ጥሪ እንዳቀረቡ ደ ካሮሊስ አስታውቀዋል።     








All the contents on this site are copyrighted ©.