2015-08-26 16:24:00

ሱታፌና አርነት፦ በሥራና የሥራ ፖለቲካ ኅዳሴ ላይ ማተኰር


በኢጣሊያ ሪሚኒ ከተማ ሱታፌና አርነት የተሰየመው ካቶሊካዊ ማኅበረሰብ የሚያዘጋጀው ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የአሕዛብ የወዳጅነት ቀን መርሃ ግብር በመቀጠል የዘንድሮው ዓውደ ጉባኤው የሰው ልጅ ተስኖ፣ ምኞትና ምኞቱ ምንድር ነው? በሚል ጥያቄአዊ መርህ ቃል ሥር  እ.ኤ.አ. ነሐሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት መከፈቱ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚጠቃለለው ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. የኢጣሊያ መራሔ መንግሥት ማተዮ ረንዚ የኢጣሊያ ቺዚል የተሰየመው የሠራተኞች ማኅበር ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ አና ማሪያ ፉርላን የኤኮኖሚ ሊቅ ጁሊዮ ሳፐሊ ንግግር ማስደተመጣቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጓራሺ አስታወቁ።

የሥራ እድል የሚፈጥሩ የተለያዩ ድርጅቶች ተናንሽና አበይት ኢንዳስትሪዎች፣ ኅዳሴና ሥነ ምርምርና ሕንጸት በተመለከተ ንዋይ የሚያፈሱ ድርጅቶችና ኢንዳስትሪዎች የግብር ክፍያ ቅነሳ ሊደረግላቸው ያስፈልጋል፣ ይኽ ደግሞ እነዚያ ለኤኮኖሚ እድገት በተለያየ መስክ የሚረባረቡት ድርጅቶችና ኢንዳስትሪዎች ማበረታታት ማለት ይሆናል እንዳሉ ጓራሺ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያወጁት የምኅረት ዓመት ለሮማ ከተማ አቢይ አጋጣሚ ነው። ሆኖም በአሁኑ ወቅት እንደሚታየው ደግሞ በከተሞች የማጓጓዣ አገልግሎት መስጫ ድርጅቶች የሚፈጽሙት ሥራ የማቆም አድማ በኢዮበልዩ ዓመት ከታየ በእውነቱ ለኢጣሊያ አቢይ ኅፍረት ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢጣሊያ ታማኝነት የሚያጎድል ነው ብለው አያይዘውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሥራ ያለው ክብር ደግም መልሶ መስጠት ያስፈልጋል፣ ይኽ በኢዮበልዩ ዓመት እጅግ ከፍ ባለ መልኩ መመስከር አለበት እንዳሉ ጓራሺ አመለከቱ።








All the contents on this site are copyrighted ©.