2015-08-21 15:15:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሥልጣናዊ ትምህርት ስለ ቤተሰብና ሥራ ርእስ ዙሪያ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. እንደተለመደው ረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ ስልጣናዊ አስተምህሮ በለገሱበት ቀን በቤተሰብና በሥራ መካከል ያለው ግኑኝነት በማስደገፉ ሥራ የትርፍ አመክንዮ ታጋች ሲሆንና የሕይወት አፍቃሪና ወዳጅ ስሜት ሲያንቋሽሽ ሰብአዊ ሕይወት ይጎዳል፣ ሰብአዊ ክብር ጭምር ያጠፋል፣ የዚህ ችግር ዋጋ ከፋይና ሰለባ ቤተሰብ ነው። በተለይ ደግሞ ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል እጅግ የዚያ ችግር ተጠቂ ይሆናል በማለት ያሰመሩበት ሃሳብ አስደግፈው የቤተሰብ ጉባኤ ሊቀ መንበር ፍራንቸስኮ በለቲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቤተሰብ ሥራና የፍቅርና የወዳጅነት ስሜት እንዲሁም ዕለታዊ ኑሮ በተገባ ሁኔታ ለመኖር የበቂ የደሞዝ ክፍያ ላንድ ቤተሰብ የዕለታዊ ኑሮ ገጠመኝ ነው። ሰው ሥራ ይፈልጋል፣ ሥራ የሚፈልገውም ዕለታዊ ኑሮውን ለመግፋት ሳይሆን ለመኖርና ቤተሰብ ለመመሥረትም ነው። ለመኖርና ቤተሰብ ለመመሥረትም ጊዜና መጠለያ ይጠይቃል። ስለዚህ ሥራ የአንድ ሰው ሙሉ የሕይወት ጊዜ ለገዛ እራሱ የሚጠፍር መሆን የለበትም። ሥራ ለሰው እንጂ ሰው ለሥራ አልተፈጠረም።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የገለጡት ሃሳብ አቢይ ምልክትና ለሠራተኛው ዓለም አቢይ ድጋፍ ነው። የሳቸው ቃል እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. በሚላኖ ከተማ “ቤተሰብ ሥራና በዓል” በሚል ርእስ ሥር የተካሄደው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ የሚያስታውስ መሆኑ ገልጠው፣ የጊዜ እሴት ለሰው ልጅ መልሶ ማስረከብ ያስፈልጋል፣ ሥራ አስፈላጊ ነው ነገር ግን ከእጅ ወደ አፍ የሚለው አመክንዮ ሥር የሚገለጥ መሆን የለበትም ብለዋል።

የአዲሱ ዓለም ሕይወት አደረጃጀትና አወቃቀር ቤተሰብ እንደ ሸክምና መሰናክል አድርጎ የሚመለከት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሰጡት ሥልጣናዊ ቃል የገለጡት ሃሳብ በእውነቱ የምንኖርበት ዓለም የማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሂደት መሠረት በማድረግ የሚከተለው መርሃ ግብር የሚወልደው አቢይ ችግር ነው። ሥራና ቤተሰብ የማይጣጣም አገናኝቶ ለሁሉም ተገቢ ጊዜ ሰጥቶ ማስተዳደርና መኖር የማይቻልበት ዓለም እየገነባን ነው። ይኽ አዲሱ የዓለም ሂደት የሰው ልጅ ያምራችነት ጥሪውን የሚያንቋሽሽ ጊዜንና ሕይወትን የሚያዋርድ ነው። ቅዱስ አባታችን እንዳሉትም አዲሱ የሥራው ፖለቲካ ጎሊያድ፣ ቤተሰብ ደግሞ እንደ ዳዊት የሚኖርበት ዓለም እየፈጠርን ነው ያሉት ሃሳብ በጥልቀት ማስተንተን ይበጃል፣ ቤተሰብ እርሱም ሰው ማእከል ያደረገ የኤኮኖሚ ፖለቲካ ለኤኮኖሚ መቃወስ መሠረታዊ መፍትሔ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.