2015-08-07 19:23:00

ውጥረቶችና ግጭቶች እንዴት አድርገን መፍትሔ ልናገኝላቸው እንችላለን? መልሱ ውይይት ነው፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ዛሬ አርብ ረፋድ ላይ በኢየሱሳውያን ማኅበር አማካኝነት ተሰብስበው በሮም ውስጥ ዓውደ ጥናት ሲያካሄዱ ከሰነበቱ የወጣቶች የቅዱስ ቍርባን እንቅስቃሴ አባላት ከሆኑ ከ1500 ወጣቶች ጋር ተገናኝተዋል፣

ወጣቶቹ ለዓለም በዓውደ ጥናት እየተካፈሉ ያሉና እፊታችን ወርኃ ነሓሴ 10 ቀን በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤያቸው ለመሳተፍ በዝግጅት የሚገኙ ናቸው፣ እነኚህ ወጣቶች ከ38 አገሮች የተሰበሰቡና የዚሁ እንቅስቃሴ አንድ መቶኛ ዓመት ለማስታወስ ለመጀመርያ ጊዜ በሮም እንደሚገኙ የተመለከተ ሲሆን ዕድሜያቸው ከ10 ዓመት እስከ የዪኒቨርሲቲ ደረጃ ላሉ ወጣቶች ያካተተና ለጸሎት ሓዋርያዊ አገልግሎት የተመሠረተና ከአንድ መቶ ዓመት በፊት በሉርድ አክባቢ ከሚገኙ የኢየሱሳውያን ማኅበር ተጀምሮ አሁን በ56 አገሮች ብታላቅ መንፈሳዊነትና አገልግሎት እየተነቀሳቀሰ መሆኑንም ከዚህ ጋር ተያይዞ የመጣ ዜና ያመለክታል፣

በጣልያን የሚገኘው የወጣቶች የቅዱስ ቍርባን እንቅስቃሴ አባላት ፕሮግራሙን ለማዘጋጀት እንግዶቹን ለመቀበልና ዓውደ ጥናቱን ለማካሄድ ብዙ እንደሰሩ ሲመለከት ከዚህ በላይ ደግሞ ወጣቶቹ በተለያዩ ቡድኖች ማለት እንደቋንቋዎቻቸውና አገሮቻቸው ጉርብትና ከ30-35 ሰዎች የያዘ ቡድን አቋቍመው በሮም ከተማ የሚገኝ ሌላ በኢየሱሳውያን የሚካሄድ “ሕይወት ያላቸው ድንጋዮች” የተሰየመ የወጣቶች እንቅስቃሴ አባላት የሆኑ 30 ወጣቶች ከኢየሱስ ጋር የመጓዝ ጣዕም በተለይ በሮም የሚገኙ የተለያዩ ታሪክ ያላቸው የክርስትና ሥነ ጥበባዊ ቅርሶችን በማሳየትና በመግለጥ እንደተባበሩ የጣልያን አገር የወጣቶች የቅዱስ ቍርባን እንቅስቃሴ ኃላፊ አባ ሎሪስ ፕዮራር ገልጠዋል፣ እንዲሁም ዛሬ ከቅዱስነታቸው ከመገናኘታቸው በፊት ስድስት ወጣቶች በቋንቋዎቻቸውና ባህሎቻቸው መሠረት ስለ ደስታ ስለማኅበርክርስትያን ክርስቶስን ስለማግኘት ስለቅዱስ ቍርባን ስለ ስብከተወንጌልና ተልእኮ ስለቤተሰብ እንዲሁም ወጣቶች ለቤተሰብ ምን አበርክቶ ሊያቀርቡ እንደሚችሉ የሚሉ ጥያቄዎች አቅርበው እንዳሉና ቅዱስነታቸው ምን መልስ እንደሚሰጡ በመጠባበቅ መሆናቸውን ገልጠው ነበር፣

ቅዱስነታቸው ወጣቶቹንና የዝግጅቱ መሪዎችን ተቀብለው ሰላምታ ካቀረቡና ከጸለዩ በኋላ የእንቅስቃሴው ኃላፊ እንዳለው ወጣቶቹ ጥያቄዎቻቸውን ለቅዱስነታቸው አቅርበዋል፣ ቅዱስነታቸውም ከምስጋና ጋር የሚከተለውን መልስ ሰጥተዋል፣

ጥያቄዎቹን በማቅረባችሁ አመሰግናለሁ፣ በጥያቄዎቹ መጀመርያ ላይ ቀልቤን የሳቡ ሁለት ቃላት አሉ፤ እነኚህ ቃላት በዕለታዊው የሕይወት ኑሮአችን በግለሰብ ደረጃም ይሁን በማኅበረሰብ እንዲሁም በቤተሰብ ደረጃ አብረውን የሚጓዙ ናቸው፣ ቃላቱም “ውጥረትና” “ግጭት” የሚሉ ናቸው፣ ማጋት ድዮፕ በቤተሰብ ዙርያ ስላለው ውጥረት ብዙ ተናግረዋል እንዲሁም ግረጎርዩስ ሃንዘል ስለ ግጭት ብዙ ተናግረዋል፣ ግን እስቲ ልጠይቃችሁ! ቤተሰብና ማኅበረሰብ አለ ውጥረትና ግጭት ምን በሆኑ ነበር፤ እንደሚመስለኝ መቃብር ቤት በሆኑ ነበር፣ ምክንያቱም ውጥረትና ግጭት የሌለበት ቦታ በሞቱ ነገሮች ብቻ ነው፣ ሕይወት ያለ እንደሆነ ውጥረት አለ እንዲሁም ግጭት ስለዚህ እያንዳንዳችን መፍትሔ መፈለግ አለብን! በሕይወቴ ውስጥ እውነተኛ ውጥረቶቹ የትኞቹ ናቸው! ከየትስ ይመጣሉ! ለምን! እንዴትስ ናቸው ከዚህ የሚከሰቱ ግጭቶች! ብለን እንጠይቅ ምክንያቱም ሁላችን በሰላም ከኢየሱስ ክርስቶስ በመንግሥተ ሰማያት በምንገኝበት ብቻ ነው የእነዚህ መኖር የሚያከትመው፣ ነገር ግን አትፍሩ ውጥረቶች ያሳድጋሉ ብርታትንም ያጐለብታሉ፣ ወጣት እንደመሆናችሁ መጠንም ይህ ብርታት ይኑራችሁ፣ አለበለዚያ ካሁን በፊት እንዳልኩት ብርታት የሌለው ወጣት ያረጀ ከዕድሜው በፊት ጥሮታ የገባ ነው፣ በ20 ዓመት ዕድሜያቸው ጥሮታ ገብተው ሁሉንም ቢያገኙም ገና ውጥረቱና ግጭቱ እንዳለ ነው፣ ስለዚህ ዋነኛው ጥያቄ እነኚህን ውጥረቶችና ግጭቶች እንዴት አድርገን መፍትሔ ልናገኝላቸው እንችላለን ነው ዋናው ጥያቄው፤ አጠቃላይ መልሱ ውይይት ነው፣ በአንድ ቤተ ውይይት ካለና እያንዳንዱ የቤተሰብ አካል የሚሰማውን የልቡን ከተናገረና ሌሎቹ ተቀብለውትና አክብረውት የገዛ ራሳቸውን ሓሳብ ለውይይት ሲያቀርቡ መፍትሔው ቅርብ ነው፣ ውጥረትን አትፍሩት! እንዲሁም ብልጣ ብልጥ መሆንም ያስፈልጋል! ምክንያቱም ውጥረት ለውጥረት የምትሻው ከሆንክ ሁሌ ግርጭት ውስት ትገኛለህ! ነገር ግን ውጥረት የሚመጣው ወደ ውህደት ለመጓዝ ነውና በዚህም ለብስለት ያደርሱናል እንዲሁም ውጥረቶችን በውይይት ለመፍታት ያስችሉናል፤ ምክንያቱም ውይይት በቤተሰብም ይሁን በማኅበረሰቦችና የተለያዩ ቡድኖች አንድነትን ለመፍጠር ይረዳናል፣ ሌላው ላስጠንቅቃችሁ የምፈልገው ደግሞ ድርቅ ብሎ በውጥረት መቀር አደገኛ ነው፣ ለመጣቀለል ያህል አለምንም ውጥረትና ችግር የሚኖር ወጣት ጥሮታ የገባ ነው እንዲያው የሞተ ወጣት ለማለት! ነገር ግን ዘወትር በውጥረትና ግጭት የሚኖር ወጣትም ሕመምተኛ ወጣት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፣

ግረጎርዮስ ስለ ግጭት ብዙ ተናግረዋል! በተለያዩ ባህሎችና አከባቢዎች ግጭቶች አስቸጋሪ ናቸው ነገር ግን ልዩነቶችን ለመረዳት ስለሚያስችሉን በጎ ነገርም አላቸው! አንድ ግጭት መልካም ውጤት እንዲኖረው ወደ አንድነት ያተኮረ መሆን አለበት ይህንን የሚያደርገው ደግሞ ያለውን ልዩነት ጠብቆ ነው፣ የሌላውን ማንነትና ልዩነት አውቀን እስካልተቀበልን ድረስ አንድነት ሊገኝ አይቻልም፣ ስለዚህ ውይይት የውጥረትና ግጭት መፍትሔ ሆኖ አንድነት የሚፈጥረው ልዩነቶቻችን በመቀበል ነው ሲሉ መቻቻልና መከባበር ዋና የውጥረትና ግጭት መፍትሔ መሆኑን በማመልከትና ሌሎች ጥያቄዎችን በመመለስ ወጣቶቹን ካበረታቱ በኋላ ብኅብረት በየቋንቋዎቻቸው ሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ እንዲጸልዩ አድርገው በሰላምታና ሐዋርያዊ ቡራኬ ተሰናብተዋቸዋል፣ 








All the contents on this site are copyrighted ©.