2015-08-03 19:32:00

ር.ሊ.ጳ፤ “ቅድስት ተረዛ ዘአቪላ የእውነተኛ እውቀት እና እሴቶች ምንጭ ናት”


“ቅድስት ተረዛ ዘኢየሱስ የሕይወት መምህር” በሚል መሪ ሓሳብ በእስፐይን እየተካሄድ ላለው ዓውደ ጥናት ለማበራታትና በመንፈስ ከሳቸው አብረው እንዳሉ ለማመልከት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፕየትሮ ጳውሊን አማካኝነት በጻፉት መልእክት “ቅድስት ተረዛ ዘአቪላ የእውነተኛ እውቀት እና እሴቶች ምንጭ ናት” ሲሉ በቅድስት ተረዛ ዘኢየሱስ ትምህርቶችና አስተንትኖዎች የሚገኛ የጸሎት ትምህርትን ገልጠዋል፣

በሚካሄደው ዓውደ ጥናት የቅዱስነታቸው መል እክትን ተቀብለው ለጉባኤው ተሳታፊዎች ያነበቡት የአቪላ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኼሱስ ጋርስያ ቡሪሎ ሲሆኑ በጉባኤው ለተገኙት ከ26 አገሮች በላይ ለመቱና ለእስፐይን የጸጥታ ጥበቃ ሚኒስትሪ ኃላፊ ሚኒስተር ጆርጅ ፈርናንደስ ድያስ በተገኙበት ነበር፣ ቅዱስነታቸው በዚሁ የቅድስት ተረዛ 500ኛ ዓመት ምክንያት በተዘጋጀው ዓውደ ጥናት አማካኝነት በአገሩ በሚገኙ መካነ ጥበባት ማለትም ካቶሊካዊ ዪኒቨርሲቲዎች ሁሉ “በአስቸጋሪ ግዝያት የሚያገልግሉ እንደ ቅድስት ተረዛ ዘኢየሱስ የመሳሰሉ ኃያል የእግዚአብሔር ጓደኛሞች እንዲያፈሩ ይሁን” ሲሉ አሳስበዋል፣   








All the contents on this site are copyrighted ©.