2015-07-29 16:11:00

የመላ አፍሪቃ አገሮችና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ የአፍሪቃ - ዓመት፦ ዕርቅ


የመላ አፍሪቃና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ ዝክረ 46ኛው ዓመት ምሥረታ ምክንያት ጉባኤው እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚዘልቀው ለሰላማዊ የጋራ ኑሮ እርቅ የሰፈነባት አፍሪቃ በሚል ርእስ ሥር የአፍሪቃ የዕርቅ ዓመት በጋና ርእሰ ከተማ አንካራ ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ መከፈቱ ካናአ የተሰየመው በአፍሪቃ የሚግኘው ካቶሊካዊ የዜና አገልግሎት ካሰራጨው ዜና ለማወቅ ተችለዋል።

የአፍሪቃ መሓላ በሚል ርእስ ሥር ለተደረሰው ሐዋርያዊ ምዕዳን ለሚያቀርበው ጥሪ መልስ

ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በአፍሪቃ ለእርቅ ለፍትሕና ለሰላም በሚል ርእስ ሥር ለተካሄደው ሁለተኛው ልዩ ጉባኤ የመላ አፍሪቃና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በማስደገፍ እ.ኤ.አ. በ 2011 ዓ.ም. የአፍሪቃ መሓላ በሚል ርእስ ሥር የለገሱት የድኅረ ሲኖዶስ ሓዋርያዊ ምዕዳን ያቀረበውን ጥሪ በማስተዋል በአፍሪቃ ለአንድ ዓመት በክፍለ ዓለም ደረጃ የእርቅ ዓመት በማነቃቃት፣ የእርስ በእርስ በሁሉም የአፍሪቃ ኅብረተሰቦች መካከል እርቅ እንዲረጋገጥ፣  የሰው ልጅ ለእርስ በእርስ ጥላቻና አንዱ በሌላው ላይ ለፈጸመው መደል የእግዚአብሔር ምሕረት በመለመን የእርስ በእርስ መታረቅ እውን እንዲሆን ይኸንን ሃሳብ ማእከል ያደረገ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚዘልቅ የእርቅ ዓመት በአፍሪቃ በመላ የአፍሪቃ አገሮችና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ የጉባኤው ዝክረ 46ኛው ዓመት ምሥረታ ምክንያት ማወጁ ካናአ የዜና አገልግሎት ባሰራጨው ዜና አመለከተ።

ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በለገሱት የአፍሪቃ መሓላ የተሰየመው ድኅረ ሲኖዶስ ሓዋርያዊ ምዕዳን አማካኝነት በአፍሪቃ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የዕርቅ የፍትህና የሰላም መሣሪያ ሆና እንድትገኝ በማለት ያቀረቡት ጥሪ በአፍሪቃ እርቅ ይቅር መባባል ምንኛ አስፈላጊ መሆኑ የሚመሰክር ነው።

የመላ አፍሪቃና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ ገንዘብ ያዥ ብፁዕ አቡነ ቻርለስ ፓልመር ቡክለ በጉባኤው ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ጋብሬል ምቢሊንጂ ስም የመላ አፍሪቃና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ዛሬ በይፋ በጋና የተከፈው የአፍሪቃ የእርቅ ዓመት ምክንያት የተለያዩ መንፈሳዊና ባህላዊ መርሐ ግብሮች እንዲያነቃቁና በተለይ ደግሞ በአፍሪቃ የእርቅ ዓመት ያነጣጠረበት ዓላማ መሠረት በማድረግ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የፍትህና ሰላም ድርገቶች አማካኝነት የተለያዩ ዓውደ ጥናቶችና ዓውደ ጉባኤዎች እንዲነቃቁ ጥሪ ማቅረባቸው የገለጠው ካናአ የዜና አገልግሎት አክሎ፦ የመላ አፍሪቃ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ሰበካዎች እንደ የአካባቢያቸውና የሰበካቸው አመችነት ለመላ አፍሪቃና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ቁጠባና ገንዘብ ሃብት ርእስ ዙሪያ ባካሄደው 16ኛው ስብሰባው የአስፍሆተ ወንጌል እቅዶች ፍትህና ሰላም ለማነቃቃት በአፍሪቃ የሚገኙት ካቶሊካውያን የመገናኛ ብዙኃን መርጃ የሚውል አንድ እሁድ ምጽዋት እንዲሰበሰብ ጥሪ ማቅረባቸው አስታውቀዋል።

37 የአፍሪቃ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች 8 ክልላዊ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የሚያቅፈው የአፍሪቃና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ እ.ኤ.አ. በ 1969 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድተኛ በኡጋንዳ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት ባካሄዱት ወቅት ተመርቆ የተመሰረተ መሆኑ ካናአ የዜና አገልግሎት ከሰጠው የዜና ምንጭ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.