2015-07-29 16:22:00

ታይዘ፦ አንድ አዲስ የትብብር ባህል ማነቃቃት


የታይዘ ማኅበረሰብ ምሥረታ ዝክረ 75ኛው ዓመትና እንዲሁ የማኅበሩ መሥራች ወንድም ሮጀር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩበት እ.ኤ.አ. ነሐሴ 16 ዝርከ አሥረኛው ዓመት ምክንያት በመላ ዓለም የሚገኙት የታይዘ ማኅበር ወንድሞች እንደሚገናኙና በዚህ በታይዘ ማኅበረሰብ አዘጋጅነት እ.ኤ.አ ከ ነሓሴ 9 ቀን እስከ ነሐሴ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚካሄደው መንፍሳዊ ባህላዊ መርሃ ግብር ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ የተለያዩ ሃይማኖቶች ተክታይ ወጣቶች በማሳተፍ ሊካሄድ በእቅድ መያዙ ሲር የዜና አገአልግሎት ገለጠ።

አንድ አዲስ የትብብር ባህል ማነቃቃት

ይኽ መንፈሳዊው መርሃ ግብር በጸሎት ዘነግህ ቀጥሎም ደስታ የዋህነትና ምህረት በሚል ርእስ ሥር አስተንትኖ የምስክርነት ቃል የሚቀርብበት ዓውደ ጉባኤ ከሰዓት በኋላም የማኅበሩ ወጣት አባላት የትብብር እሴት በተመለከተ የሚኖሩት ገጠመኝ በመለዋወጥ በትብብር የሚኖር መንፈስ ላይ ያነጣጠረ ከሚቀርበው የምስክርነት ቃል ቀጥሎ የተለያዩ የስነ ቅብና የታይዘ ወጣት አባላት ጉዳይ የሚያትት የፎት ግራፍ ትርኢት እንደሚቀርብ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ለሚደረገው ግኑኝነት አቢይ አጋጣሚ

በዚህ ሊካሂድ በእቅድ ተይዞ ባለው የታይዘ ዓውደ ጉባኤ ከተለያዩ ሃይማኖቶች የተወጣጡ ከመቶ በላይ የሚገመቱ ምሁራን አስተምሮ እንደሚያቀርቡና የክርስቲያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካዲናል ኩርት ኮኽ የሚገኙባቸው የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን የሚያቅፈው የአቢያተ ክርስቲያን የጋራ ምክር ቤት ጠቅላይ ዋና ጸሐፊ ክቡር መጋቤ ኦላቭ ፍይክሰ ቲቫይት፣ በኤውሮጳ የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን የሚያቅፈው ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር መጥሮፖሊታ አማኑአል፣ የፈረንሳይ ፈደራላዊ የፕሮተስታንት አቢያተ ክርስቲያን ማኅበር ሊቀ መንበር መጋቤ ፍራንስዋ ክላቫይሮልይ የኪንሻሳ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ላውረንት ሞሰንግዎ ፓሲንያ፣ የፈረንሳይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የማርሰይለ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጀርገ ፕንቲየር፣ የአውቱን የስታራበርግ የኦራንና የአልጀሪ ብፁዓን ጳጳሳት የሚገኙባቸው ከተለያዩ ሃይማኖቶች የተወጣጡ ልኡካን እንደሚሳተፉ የታይዘ ማኅበር ይፋዊ ድረ ገጽ ያሰራጨው ዜና የጠቀሰ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የወንድም ሮጀር ዝክረ እረፍት

እ.ኤ.አ. ነሓሴ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ ከመቶ በላይ የሚገመቱ የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎችና ከመላ ዓለም የተወጣጡ የታይዘ ማኅበር አባላት ወጣቶች ያሳተፈ የወንድሞ ሮጀር የተዝካር የጸሎት ሥነ ሥርዓት እንደሚፈጸም የገለጠው የታይዘ ማኅበር ይፋዊ ድረ ገጽ ያሰራጨወ ዜና የጠቀሰው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ እ.ኤ.አ. ከነሓሴ 30 ቀን እስከ መስከረም 6 ቀን 2015 ዓ.ም. የወንድም ሮጀ እሳቤ አስተዋጽኦ በቲዮሎጊያና ለቲዮሎጊያ ምርምር በሚል ርእስ ሥር ከአርባ ዓመት እድሜ በታች የሆኑት ወጣት የቲዮሎጊያ ሊቃውንት ያሳተፈ ልዩ ዓውደ ጥናት እንደሚካሄድ አታወቀ።  








All the contents on this site are copyrighted ©.