2015-07-29 16:19:00

ሶሪያ፦ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዮሓንስ አስረኛ፦ በአገራችን ለአገራችንና ለሕዝባችን


መካከለኛው ምስራቅ በአቢይ አሳሳቢ ውጥረት የሚገኝና በሶሪያ ባለው ግጭትና ጦርነት ምክንያት አገሪቱና ሕዝብ ወደ ተስፋ መቁረጥ አዝማሚያ ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ የተጋለጠ ቢሆንም ቅሉ የአገሪቱ የኦርቶዲክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን አገራቸውን ለቀው ለመውጣት እንደማይፈልጉና የሶሪያ ማኅበረ ክርስቲያን መጻኢ በሶሪያ ነው ብለው የሚያምኑ መሆናቸው የአንጽዮኪያና የመላ መካከለኛው ምስራቅ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ዮሐንስ አሥረኛ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በመካሄድ ላይ ባለው የመላ አንጽዮኪያና የመካከለኛው ምስራቅ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ማረጋገጣቸው ሲር የዜና አገልግሎት ገልጦ፣ ይኽ በእንዲህ እንዳለም እ.ኤ.አ. ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባስደመጡት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ በሶሪያ የተጠለፉት ኢየሱሳዊ ካህን አባ ዳሎሊዮና ሁለት የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዩሃና ኢብራሂምና  የብፁዕ ፓትሪያርክ ዮሓንስ አሥረኛ ወንድም ብፁዕ አቡነ ፓኡል ያዚጅ በዚያ ክልል የታገቱት ሁሉ ነጻ እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርበው እንደነበር ያስታውሳል።

ከተጠለፉ ውስጥ ሁለተኛ ዓመታቸውን ካስቆጠሩ ውስጥ ሌሎች ሜጥሮፖሊታና ካህናቶች ጭምር እንዳሉና የዓለም አቀፍ ማኅብረሰብ የታገቱት ሁሉ ነጻ እንዲለቀቁ ጥሪ ከማቅረብ ዝምታ የመረጠ እንደሚመስልም ብፁዕ ፓትሪያርክ ዮሓንስ አሥረኛ ገልጠው፣ በሶሪያ ሰማዕታት ባሕታውያን ገዳማውያን ካህናትና ደናግል ምእመናን ክርስትና በልባቸው በቃልና በሕይወት ሕያው በማድረጋቸው ምክንያት ለተለያየ ችግር ተጋልጠው ይገኛሉ፣ የሶሪያ ክርስቲያኖች ካህናትና ደናግል በምንም ምክንያት አገራቸውና ሕዝባቸውን ለቀው እንደማይወጡና የአገሩቱ ማኅብረ ክርስቲያን የነበረ የአገሪቱ ባህልና ታሪክ  ክፍል ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ለሶሪያ ሕዝብ ትብብርና ድጋፍ

በመካከለኛው ምስራቅ የሚታየው ግብረ ሽበራ ቀዳሚ ተጠቂው የክልሉ ማኅበረ ክርስቲያን ነው። በሶሪያ በኢራቅና በሊባኖስ ባለው ግጭት ሳቢያ እጅግ ለከፋ አደጋ የተጋለጠው ማኅበረ ክርስቲያን ነው። በብዙ ሹሕ የሚገመቱ ክርስቲያኖችም በክልሉ አክራሪ እስላማዊ ታጣቂ ኃይሎች ከሚጥሉት የሽበራ ጥቃትና ቅትለት ገዛ እራሳቸውን ለማዳን አገራቸውን ጥለው እየተሰደዱ ናቸው። በብዙ መቶዎች የሚገመቱትም ለሞት ተዳርገዋል፣ አቢያተ ክርስቲያኖች ወድመዋል ተዘርፈዋል፣ የአገሪቱ የክርስትና ባህል ሃብት የሆኑት ብራናዎች መጽሓፎች ተቃጥለዋል ቅርሶች ወድመዋል፣ ሆኖም የክልሉ ክርስቲያን ክርስትናው በስደት ሳይሆን በአገሩ ለመኖር የሚሻ ነው። ከክርስቶስ የሚለየን ምንም ነገር የለም። የክልሉ ክርስቲያን ለተለያየ አደጋ የተጋለጠ ቢሆንም ቅሉ፣ በአገሩት ክርስትናን መኖር የሚል ነው። ይኸንን ፍላጎቱና ፈቃዱ ለመኖር እንዲችልም የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ትብብርና ድጋፍ እንደሚያሻው ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዮሐንስ አሥረኛ ገልጠው፣ ለመካከለኛው ምስራቅ ማኅበረ ክርስቲያን መጻኢ የሁሉም ድጋፍ አደራ እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ውይይት አብሮ መኖር ባህላዊ እድገት

በመካከለኛው ምስራቅ የሚታየው ጸረ ሰብአዊ ተግባር ሁሉ እንዲወገድ የክልሉ ሕዝብ በክልሉ  የሚገኙት የተለያዩ ሃይማኖቶች በሰላም ለመኖር እንዲቻል በጋራ ውይይትና ሰላማዊ የጋራ ኖሩ የሚል የባህል እንድገት እንዲያነቃቁ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዮሐንስ አሥረኛ ባሰሙት ንግግር ጥሪ አቅርበው፣ አበይት ሃይማኖቶች የሚባሉት የተወለዱበት ክልል እየወደመ ነው። ዛሬ እርዳታና ትብብር እየጠየቀ ነው። እርዳታና ትብብር ይገባዋል እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.