2015-07-24 15:03:00

የፖላንድ ብፅዓን ጳጳሳት መግለጫ


በሰው ልጅ በኑባሬ ያለውን የመውለድ ባህርይ እንዲተካ በማድረግ  ልጅ ለመውለድ የዘጠኝ ወር የእርግዝና የጊዜ ገደም ለመቋቋም ለማይፈልጉ በመኻንነት ለተጠቁት ልጅ እንዲኖራቸው ለሚፈልጉት ሁሉ ልጅ እንዲኖራቸው ለማገዝ ልጅ እንደ ጸጋ ሳይሆን ገና ከመወለዱ በፊት እንደ ግኡዝ ነገር እንዲመረጥ የሚያደርግ የሥነ ሕይወት ክስተት ባህርያዊ የመዋለድ ሂደቱ በየምርምር ብልቃጥ ውስጥ የሚከውን ተግባር የአገሪቱ መንግሥት በፖላንድ እግብር ላይ እንዲውል የሚያዘው ያጸደቀው ሕግ የሰው ልጅ ክብር የሚጻረር መሆኑ የፖላንድ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሕጉን በመቃወም ባስተላለፈው መልእክት እንዳመለክተ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ይኽ ግብረ ገባዊና ሥነ ምግባራዊ መመዘኛ ሁሉ የሚጥስ የሰው ልጅ የብልቃጥ ውጤት የሚያደርግ የምርምር ሥልት ካቶሊካውያን ምእመናን እንዳይቀበሉት የፖላንድ ብፁዓን ጳጳሳት በማሳሰብ፣ ሕይወት ከባህርያዊ መጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት የማክበሩ ባህል በመኖር የሕይወት ባህል መስካሪያን ሆነው እንዲገኙና በተለያየ ምክንያት ልጅ መውለድ ለሚሳናቸው ሁሉ ወላጅ አልባ የሆኑት ልጆች በማሳደግ የወላጅነት ጥሪያቸው እንዲኖሩ ማሳሰባቸው የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ የፖላንድ መንግሥት ያጸደቀው ሕግ እግብር ላይ እንዲውል የአገሪቱ የሕገ መንግሥት አስከባሪው የበላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንደሚያስፈልግ አስታወቀ።        








All the contents on this site are copyrighted ©.