2015-07-24 14:58:00

የፊሊፒንስ ካቶሊካውያን ምእመናን በሥነ ምኅዳር ጥሪ


የመሬት የሙቀት ደረጃ ከ1.5 ዲግሪ በላይ ከፍ እንዳይል የፈለክ የሙቀት ደረጃ ከፍ እንዲል የሚያደርገው የተፈጥሮ አየር በካይ ጋዝ ልቀት በከፍተኛ ደረጃ እንዲጎድል እንዲሁም ለድኾች አገሮች በተለይ ደግሞ በተፈጥሮ ያካባቢ አየር ለውጥ ምክንያት ለተለያየ አደጋ ለሚጋለጡት አገሮች ድጋፍ የሚጠይቅ ከ 20 ሚሊዮን የፊሊፒንስ ሕዝብ ፊርማ የተኖረበት የአቤቱታ ሰነድ እ.ኤ.አ. ታሕሳስ ወር 2015 ዓ.ም. የተባበበሩት መንግሥታት ድርጅት በፓሪስ የተፈጥሮ ያካባቢ አየር ዙሪያ ለሚመክረው ዓውደ ጉባኤ እንደሚተላለፍ ሲገለጥ፣ የአቤቱታው ሰነድ አማካኝነት ፊርማ የማሰባሰቡ መርሃ ግብር ያነቃቃው 140 የተለያዩ የተፈጥሮ ያካባቢ የአየር ንብረት እንክብካቤ የሚያነቃቁት ካቶሊካውያን ማኅበራት የሚያቅፈው በቅርቡ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተፈጥሮ ያካባቢ የአየር ንብረት እንክብካቤ ጥበቃ በተመለከት የምትከተለው አመለካከትና የምታረማምደው እቀድ በአንድ ድምጽ ማስተጋባት በሚል አላማ የተቋቋመው ዓለም አቀፋዊ ካቶሊካዊ የተፈጥር የአየር ንብረት ተንከባካቢ ማኅበር መሆኑ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በተፈጥሮ የአየር ንብረት ላይ እይደረሰ ያለው የመቀያየር አደጋ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተፈጥሮና በፍጥረት ላይ እየደረሰ ያለው አደጋ ለማስወገድና የሁሉም የጋራ ቤት የሆነችውን መሬት ለማዳን የሁሉም ኅሊና ለማነቃቃት ይሴባሕ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት በመከተል በፊሊፒንስ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ጅምሮች እያከናወነች መሆንዋ የገለጠው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አክሎ የፊሊፒንስ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ይሴባሕ ዓዋዲ መልእክት መሠረት በማድረግ እያነቃቃው ያለው ተፈጥሮ የመንከባከብ ዓላማ የእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን የተሰየመው ዕለታዊ ጋዜጣ በመደገፍ ቀዳሚ ገጽ በመስጠት ፊሊፒንስ በተፈጥሮ የአየር ንብረት መቀያየር እጅግ በተደጋጋሚ ከሚጠቁት አገሮች አንዷ በመሆንዋም የዚያች አገር ህዝብ የተፈጥሮ የአየር ንብረት መንከባከብ ያለው አስፍፍላጊነት ከሁሉም በላይ ጠንቅቆ የሚያውቀው ጉዳይ ነው። እንዲህ በመሆኑም ተፈጥሮና ፍጥረት ለመንከባከቡ አቢይ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ያመለክታል።

ሰው የመሬት ተንከባካቢ እንጂ ጌታና ገዥ አይደለም

ባለፉት ቀናት የፊሊፒንስ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ይሴባሕ የተሰየመውን ዓዋዲ መልእክት  መሠረት በማድረግ ሰው የመሬት ተንከባካቢና ጠባቂ እንጂ ጌታና ገዥ አይደለም የሚለው የአመለካከትና የተግባር አቋም፣ ዓዋዲ መልእኽቱ የተፈጥሮ የአየር ንብረት የመቀያየር ጥያቄ ማእከል ማኅበራዊ ፍትሕ መሆኑ ያሰመረበት ሃሳብ መሠረት በማድረግ፣ የተፍጥሮ ሃብት በሚገባ እጥቅም ላይ ማዋልና መንከባከብ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለመጪው ትውልድ ጭምር የሚል መሆኑ የፊሊፒንስ ብፅዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ታህሳስ ወር 2015 ዓ.ም. በፓሪስ እንዲካሄድ የተባበበሩት መንግሥታት ድርጅት የተጠራው ዓውደ ጉባኤ ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት እንዳሰመሩበት ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.