2015-07-20 16:43:00

የአፍሪቃ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት፦ ድኽነት ለማጥፋት መመዘኛዎች ማጽናት


መላ ማኅበርሰብ ከድኽነት ለማላቀቅ ተገቢ መመዘኛና የልማት የማስፈጸሚያ እርምጃዎች ያለው አስፈላጊነት በኢትዮጵያ የመቂ ስበካ ሐዋርያዊ መሥተዳድር ብፁዕ አቡነ አብራሃም ደስታ በመላ አፍሪቃ አገሮችና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛ ምክትል ሊቀ መንበር በጋና የኩማሲ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጋብሬል አኖክየ ስም በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ከተማ መዋዕለ ንዋይና ልማት በሚል ርእስ ዙሪያ በተካሄደው ሦስተኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር እንዳሰመሩበት ሲገለጥ፦

ድኽነት ለመዋጋት ከመንግሥታት ጽኑ መመዘኛ ይጠይቃል

የጋራ ጥቅም ማነቃቃት በተለይ ደግሞ በድኽነት የተጠቃውን ከድኽነት ማላቀቅ በእውነቱ በእሴቶችና የሰብአዊ መብትና ክብር በግልጽነት አሠራርና እርስ በእርስ መከባበር የተፈጥሮ ምሉእነት ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ ድጋፍ የተሰኙት የቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት ጭምር የሚያመለክተው ጽኑ መመዘኛዎችና አቋሞች በሁሉም አገሮች ማነቋቋት ያለው አስፍላጊነት ብፁዕ አቡነ ደስታ ባሰሙት ንግግር እንዳሰመሩበት የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

የመላ አፍሪቃና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ ልማትና የግብር ክፍያ ኃላፊነት ያለ መወጣት እርሱም ከግብር ክፍያ የማምለጥ ተግባር የሚከታተል አንድ ጉባኤ እንዲቋቋም ብፁዕ አቡነ ደስታ ባሰሙት ንግግር አማካኝነት ሃሳብ ማቅረቡና በልማት ሂደት የሚሳተፉት መስከረም ወር 2015 ዓ.ም. ሊካሄድ በተጠራው ዓለም አቀፍ ጉባኤ፣ የልማት እቅዶች እግብ ላይ ለማድድረስ ንቁና አቢይ ሚና ለመጫወት የሚችሉት አገሮች ሁሉ የሚያሳትፍ አንድ አካል እንዲቋቋም ብፁዕ አቡነ ደስታ ባሰሙት ንግግር ሃሳብ ማቅረቡ ጭምር የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ የመላ አፍሪቃና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ በዓለም የሚታየው የግብር ክፍያ የሚመለከተው ሕግ የመጣስ ወንጀል በተባበሩት መንግሥታት ሥር በሚቋቋም በአንድ አካል አማካኝነት የግብር ክፍያ ሕግ ጥሰት ለማስወገድ የሚደገፍ ተጨባጭ መመዘኛ እንዲረጋገጥ ሃሳብ ማቅረቡንም አስታውቀዋል። የአዲስ አበባው ጉባኤ እ.ኤ.አ. በ 2015 ዓ.ም. መስከረም ወር በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከ 2015 እስከ 2020 ዓ.ም. ይረጋገጣል ተብሎ ለሚጠበቀው የልማት እቀድ ማስተግባሪያ 2.500 ሚሊያርድ እንደሚያስፈልግ በማሳወቅ መጠናቀቁ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.