2015-07-15 16:08:00

አባ ሎምባርዲ፦ እውነተኛ ለውጥ ስለ ድኾች ከሚኖር ሕይወት ይጀምራል


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 5 ቀን እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. በሦስት የላቲን አመሪካ አገሮች ያካሄዱት ዘጠነኛው ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት አጠናቀው አገረ ቫቲካን እንደገቡ በዚህ ሐዋርያዊ ዑደት ከሸኙዋቸው አንዱ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ከሐዋርያዊ ዑደት የሚፈልቀው ዋና መልእክቱ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ሲያብራሩ፦ በቅድሚያ ይላሉ በቅዱስ አባታችን ዙሪያ ሥፍር ቁጥር የሌለው ሕዝብ ሲሰበሰብ ማየቱ ሁሉም አስደንቀዋል፣ የሕዝቡ አቀባበል ያኗናር ሥልት ቅዱስነታቸው ለመቀበል ያሳየው ተሳትፎ የኖረው ያቀባበል ሥልት ካለው ባህል አንጻር ብቻ ሳይሆን ካለው ጥልቅ እምነት የመነጨ ነው። ይኸንን የሕዝቡ የእምነት ጥልቀትም ቅዱስ አባታችን ጠንቅቀው የሚያውቁት ነው። የዚህ ክፍለ ዓለም ተወላጅ መሆናቸውም መዘንጋት የለብንም።

ያስደመጡት ምዕዳን ያቀረቡት ስብከቶችና የሰጡት አስተምሆሮ ሥነ ሐሳብ ላይ የጸና ሳይሆን ከሕይወት ጋር የተቆራኘ ከቀጥተኛ ገጠመኝ የመነጨ ነው። ለምሳሌ መጋብያን ለሕዝብ ቅርብ እንዲሆኑ፣ ከሕዝብ ሕይወት የተለዩ እንዳይሆኑ አደራ በማለት ያቀረቡት ጥሪ ይመሰክረዋል። የዚያ ክፍለ ዓለም ሕዝብ ከገጠመኝ የሚወለድ ቀጥተኛ አነጋገር የሚወድ ብቻ ሳይሆን የባህሉ ጥያቄ ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸውን በዚህ በሦስቱ የላቲን አመሪካ አገሮች ባካሄዱዋቸው ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት የሸኙዋቸው ቅዱስነታቸው ለዚያ ክፍለ ዓለም ሕዝብ ያላቸው ፍቅር አክብሮት አድናቆት በቅርብ የገዛ እራሱ ተመክሮ ለማድረግ በቅተዋል። የሕዝቡ ምሉእ ሰብአዊና መንፈሳዊ እድገት እንዲረጋገጥ ከፍቅር የመነጨ ጥልቅ ድጋፍ ከሚሰዋ ፍቅር የመነጨ ትብብር ያሻዋል፣ ሆኖም በዚህ ለምሉእ ሰብአዊ እድገት በሚደረገው ጥረት ሕዝቡ ንቁ ተሳታፊ ነው። ከዚህ አኳያ ሲታይ የቅዱስ አባታችን መልእክት ይኸንን ንቁ ተሳታፊነት የሚያበረታታ በተለይ ደግሞ በዚህ የምሉእ ሰብአዊ እድገት ጎዳና የተናቀው የተነጠለው ድኻው የበለጠ ንቁ ተሳታፊ ሲሆን የምሉእ እድገት ጥረት የተረጋገጠ ምሉእነት እንደሚኖረው ቅዱስነታቸው ከራሳቸውና ከዚያ ክልል ሕዝብ ገጠመኝ አንጻር በመንደርደር አስምረውበታል።

ወቅታዊው የዓለም ሁኔታ በጠቅላላ የሕዝቦች የአካባቢ ሁኔታ የተመለከትን እንደሆን ለውጥ ያለው አስፈላጊነት የሚያሳስብ ነው። ኤኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ መሥተዳድራዊ ሰብአዊ ለውጥ እጅግ አንገብጋቢ ነው። የምንኖርበት ዓለምና የሕዝቦች ታሪክ ይኸንን ለውጥ አንገብጋቢ መሆኑ በተለያዩ ክስተተኖች አማካኝነት ያመለክትሉናል። ይኽ ለውጥ እውነተኛ ለውጥ እንዲሆን እንዲጨበጥና እግብር ላይ እንዲውልም ማሕበራዊ ፍትሕና ትብብር መሠረት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ገልጠዉታል። የድኻው የኅብረተሰብ ክፍል መሠረታዊ ጥያቄ መልስ ለመሰጠት ሲቻል የሚፈለገው ለውጥ ሊጨበጥ የሚቻል መሆኑም አስምረውበታል። ድኾች የወንጌል ማእከል ናቸው፣ ሆኖም በወንጌላዊ ተልእኮ ብቻ ሳይሆን በሁሉም መስክ ማእከል መሆን እንዳለባቸው በማሳሰብ፣ ድኾችን ማእከል ማድረግ የእውነተኛና የተስተካከለ ለውጥ መሠረት ነው። ከሕዝባውያን እንቅስቃሴዎች ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት የገለጡትና ያብራሩትም እውነት ነው። ይኽ ደግሞ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ለመላ ሰው ዘር የሚመለከት ነው በማለት ያካሄድት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.