2015-07-03 17:39:00

በመንፈስ ቅዱስ የመታደስ እንቅስቃሴ ከር.ሊ.ጳ ጋር በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ


በመንፈስ ቅዱስ መታደስ የሚባለው ትልቅ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የተሓድሶ እንቅስቃሴ ዛሬ ከር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጋር አብሮ ለመጸለይ እየተሰባሰበ ነው፣ አሁን ፕሮግራማችን በሚተላለፍበት ወቅት ጉባኤ ጸሎቱ እየተካሄደ ነው፣ የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይን ሞልቶ ያለው የሕዝብ ብዛት ገና በውል ባይታወቅም እስከ 40 ሺ የሚገመት ነው፣

በመርሓ ግብሩ መሠረት መሪ ቃሎቻቸው “የአንድነት የሰላም መንገዶች! ለዘመናችን ሰማዕታትና ለመንፈሳዊ አንድነት የጸሎት ድምጽ!” የሚል ሆኖ ይህ እንቅስቃሴ ከጀመረበት ዘመን ጀምሮ ዛሬ 38ኛውን መደበኛ የተሓድሶ ጉባኤ ይጀመራል፣ በዚሁ ጉባኤ የሚካሄዱት ብዙ መንፈሳዊ ተግባሮች እንዳሉ ከእነዚህም የምስክርነትና ከተለያዩ አብያተ ክርስትያናት የአንድነትና የወንድማማችነት ሂደት እንዳሉም ተመልክተዋል፣

በመንፈስ ቅዱስ የመታደስ ሊቀ መንበር አቶ ሳልቫቶረ ማርቲነዝ ጉባኤውን “ለዘመናችን ሰማዕታት በተለያዩ ድምጾች የምንጸልይበት የጸሎት ጉባኤ ነው፤” ሲሉ ገልጸውታል፣ ባለነው ዘመን በተልያዩ የዓለማችን ክፍሎች ለክርስቶስ ሲሉ ሕይወታቸውን የሰው የሚሰደዱና በደማቸው የሚመሰክሩ ሰማዕታት እጅግ ብዙ ሲሆኑ ከተለያዩ አብያተ ክርስትያናት በመሆናቸው በደማቸው አንድነትን ስለመሰከሩ ኤኩመኒካዊ ወይንም የክርስትያኖች አንድነት ውይይትና ጸሎት በዚህ ምስክርነት በመጠንከሩ ይህንን መንፈሳዊ ኢኩመኒዝም ብለው ሰይመውታል የዚሁ የደም ኢኩመኒዝም በሕዝብ መካከል የአንድነትና የሰላም ጐዳና መሆኑንም ገልጠዋል፣ ለአቶ ሳልቫቶረ ማርቲነዝ ይህ የዛሬ የጸሎት ጉባኤ ያ አምና በጰራቅሊጦስ ከ50 ሺሕ በላይ በመንፈስ ቅዱስ የመታደስ አባላት በሮም ኦሊምፒክ ባደረጉት የጸሎት ጉባኤ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በመካከላቸው ተገኝተው በመጸለያቸውና በሰጡት አባታዊ ምክር እጅግ ደስ እንዳላቸው ለመግለጥና አጸፌታውን ያህል ለመመለስ ከኢጣልያና ከሌሎች አገሮች የማኅበሩ አባላት ተሰብሰበው ቅዱስነታቸውን ሰላም ለማለትና አብሮ ለመጸለይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እንዲገኙ እንዳቀዱ ተናግረዋል፣ ይህንን ያደረጉትም አምና ቅዱስነታቸው የመንፈሳዊ ኢኩመኒዝም ምስክርነት እንድንሰጥና በዓለም ውስጥ የምንገኝ የሰላም ሰዎችና ሴቶች እንዲሁም ጸሎትን በልባቸው ውስጥ አንደኛ ቦታ የሚሰጡ የአብያተ ክርስትያን ልዩነትን ተሻግረው በኅበረት በመጸለይ ይህችን በዓመጽ በጦርነት ድህነትና በተለያዩ ችግሮች ቆስላና ተከፋፍላ ላለቸው ዓለማችን ሰላም አንድነትና መረጋጋት እንድንጸልይ አደራ ባሉን መሠረት ነው ሲሉ ዛሬ ማምሻውን ስለዚሁ እንደሚጸለይ ገልጠዋል፣

ስለዚሁ በደም ምስክርነት የሚገኝ መንፈሳዊ የክርስትያኖች አንድነት የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳስ ተወካይ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ደይቪድ ሞክሶንም በበኩላቸው “ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እንዳመለከቱት በዚሁ በደም ምስክርነት በሚገኘው መንፈሳዊ የክርስትያኖች አንድነት ፊት ሲገኙና አንድን ክርስትያን የየትኛው ቤተ ክርስትያን አባል መሆኑን ሳይጠይቁ ክርስትያን በመሆኑ ብቻ ሲገደል የዚህ ዓይነት የአንድ ሰማዕት ደም ለሁሉም ክርስትያኖች የሚወክል ዓለም አቀፋዊ አጠቃላይ የክርስትያኖች ምስክርነት ይሆናል፣ ይህንን ደግሞ በመላው ዓለም ለሚገኙ አማኞች እንደሚያጠቃልል ነው፣ ር.ሊ.ጳ ስለዚሁ ጉዳይ ሲናገሩ ታላላቅ አብያተ ክርስትያናት እንደሚስማሙ ሲገልጽ ልዩነት ለመፍጠር ሊጠራን የሚችሉም ር.ሊ.ጳ ናቸው፣” ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፣

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከቅዱስነታቸው አብረው ከሚጸልዩና ከሚዘምሩ ደግሞ አንድረያ ቦቸሊና እስራኤሊትዋ ኖዋ ይገኛሉ፣ እስራኤሊትዋ ኖዋ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ብዙ ግዜ የዘመረች ሲሆን ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለመካከለኛው ምስራቅ ስለሚያደርጉት የሰላም ጥረት እጅግ እንደምታመሰግናቸውና በሚገነብዋቸው የሰላም ድልድዮች እጅግ እንደምታደንቃቸው የገለጸች ሲሆን ለቅዱስነታቸው እንዲተላለፍላት የፈለገችው መል እክትም እንደሚከተል ነው “የተከበሩ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቃላችሁና በተግባራችሁ ያ ጌታ ‘ጓደኛህን እንደገዛ ራስህ አድርገህ ውደድ’ ላለው ወርቃዊ ት እዛዝ አዲስ ትርጉም ሰጥተዋል፣ ቅዱስ አባታችን በዚሁ ጨለማ ከቦት ያለ ዘመናችን እጅግ የሚያስፈልግነን ብርሃን እየሰጣችሁን ስለሆነ እግዚአብሔር ይስልን፣ የጥረታችሁ ፍሬ ደግሞ የለጋስነት መንፈስ በመልበስ በተለይ ደግሞ ሰላም ያስገኝልን” ስትል ምኞትዋን ገለጸች፣








All the contents on this site are copyrighted ©.