2015-07-01 19:11:00

ዕብራውያንና ክርስትያኖች ጓደኛሞችና ወንድማሞች ናቸው፣


 

ይህንን ያሉት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና ዓለም አቀፍ የክርስትያኖችና አይሁድ ምክር ቤት ተወካዮችን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነበር፣ቅዱስነታቸው ዛሬ ዕብራውያንና ክርስትያኖች አንዱ ለአንዱ ባዳ ሳይሆኑ ጓደኛሞችና ወንድማሞች ናቸው ስንል በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የታወጀው የውይይት ፍላጎትና ለሓምሳ ዓመታት በሁሉቱም ባለበጎ ፈቃዶች የተካሄደው ውይይት ፍሬ መሆኑንም አመልክተዋል፣ በዚሁ በሐዋርያዊ አደራሽ በሳላ ክለመንቲና በሚታወቀው ክፍል በተካሄደው ግኑኝነት 250 የሚሆኑ በዕብራውያንና በክርስትያኖች መካከል በመላው ዓለም ለሚካሄደው ውይይት የሚከታተሉና በዚሁ ሳምንታ ለዓለም አቀፉ የክርስትያኖችና አይሁድ ምክርቤት ስብሰበባ የተገኙ እንደሆነ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክተዋል፣

የዛሬ አምሳ ዓመት እ.አ.አ ጥቅምት 28 ቀን 1965 ዓም በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በሰባተኛ ስብሰባ ከታወጁ ሰነዶች አንዱ የሆነው ኖስትራ ኤታተ ያለነው ዘመን በሚል ርእስ ሲሆን ይህም የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ግኑኝነት ክርስትያን ካልሆኑ ሃይማኖቶች ጋር የሚል ሆኖ ከእንዚሁ ክርስትያን ያልሆኑ ሃይምኖቶች አንዱ የአይሁድ እምነት/ጁደይዝም ነበር፣ ለታሪካዊ ማስታወሻ ያህል ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ እ.አ.አ ጥቅምት 11 ቀን 1962 ዓም በር.ሊ.ጳ ቅዱስ ዮሓንስ 23ኛ ተከፍቶ ታሕሣስ 8 ቀን 1965 ዓም በር.ሊ.ጳ ብፁዕ ጳውሎስ 6ኛ ተፈጽመዋል፣ ለ10 ጊዜ እንደተሰበሰቡና 16 ሰንዶች እንዳወጁ የሚታወስ ነው፣

ስለዚህ ዓለም አቀፉ የክርስትያኖችና አይሁዶች ምክር ቤት ጉባኤውን በዚህ ጊዜ ሲያደርግ የዚሁ የውይይት በር ከፋች የነበረው ኖስትራ ኤታተ/ያለነው ዘመን 50 ዓመት በማስተወስም ነው፣

ቅዱስነታቸውም ይህንን በማስታወስ ይህ ሰነድ ያኔ አከራካሪ የነበረውን የክርስትና ሥር መሠረት በእብራውያን ባህልና እምነት እንደሚገኙ ሲያረጋግጥ ጸረ-ሴማው/አንቲሰሚቲክ እንቅስቃሴንም እንዳወገዘ ገልጠው መንፈስ ቅዱስ ጥረቶቻችና ውይይቶቻችን በመሸኘቱና እግዚአብሔር ጸጋው ስለጠን አመርቂ ፍሬ ለማግኘት ስለተቻለ እግዚአብሔር እናመስግን ብለዋል፣ ይህ የከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ያስገኘልንን ጸጋን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣

“ለዚሁ የከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር መንፈስ ምስጋና ይግባውና ሰብአዊ መከፋፈላችን የእምነት ድካማችንና ዕብሪቶቻችን ተሸንፈዋል፤ በዚህም በመካከላችን መተማመንና ወንድማማችነት እያደጉ መጥተዋል፣ አንዱ ለአንዱ ባዳ አይደለንም ጓደኛሞችና ወንድማሞች ነን፣ እኛ ክርስትያኖች ሁላችን የዕብራውያን ባህልና እምነት ሥር መሠረት አለን፣ ለዚህም ይህ ዓለም አቀፍ የክርስትያኖችና አይሁድ ምክር ቤት ከተመሠረተበት ጀምሮ የክርስያኖች ሁሉ ማኅበራትንና አብያተ ክርስትያናትን ካላቸው ልዩነት ተቀብሎ እያስተናገደ ነው፣ ሁላችን ዓለምን በፈጠረና የታሪክ ጌታ የሆነ አንድ እግዚአብሔርን እናመልካለን፣ እርሱም ወደር በሌለው በጎነቱና ጥበቡ ለውይይት የምናደርጋቸውን ጥረቶች ሁሌ ይባርካል፤ ክርስትያኖች ሁላቸው አንድነታቸውን በክርስቶስ ያገኙታል፣ ዕብራውያን ደግሞ በኦሪት ቶራሕ ያገኙታል፣ ክርስትያኖች በዓለማችን ሥጋ በመልበስ ሰው የሆነው የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ያምናሉ፣ ዕብራውያን ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል በቶራሕ በሓሙስቱ ብሔረ ኦሪት እንዳለ ያምናሉ፣ ሁለታቸውም በአንድ እግዚአብሔር ያምናሉ እንዲሁም ይህ እግዚአብሔር የኪዳን አምላክ ሆኖ ለሰዎች በቃሉ ስለሚገለጥም ክርስትያኖች ሥጋ በሆነው የአዲስ ሕይወት ምንጭ በሆነው ክርስቶስ ያገኙታል አይሁድም በቶራሕ ትምህርት ያገኙታል፣ ሲሉ አንድ የሚያደርጉን ብዙ መሠረታውያን ነገሮች እንዳሉ ገልጠዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.