2015-06-29 19:19:00

ቤተክርስትያን የክርስቶስ ናት! ማንኛ ሄሮዱስ የእምነት ብርሃንን ሊያጨልም አይችልም፣


የላቲን ሥርዓተ አምልኮ የምትከተል ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ዛሬ የቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ ዝክረ በዓል በታላቅ መንፈሳውነት አከበረች፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካም ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከአንድ መቶ በላይ በሚሆኑ ካርዲናሎችና ጳጳሳት እንዲሁም እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ካህናት በኁባሬ መሥዋዕተ ቅዳሴ እንዳሳረጉ ሲመለከት በዚሁ ዓመት የሊቀ ጵጵስና መዓርግ ለሰጥዋቸው ከመላው ዓለም ለመጡም አክሚም ፓልዮ ባርከው ሰጥተዋል፣ የአሥመራ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መንግሥተአብ ተስፋማርያምም ከእነዚሁ አዳዲስ ሊቃነ ጳጳሳት አንዱ ነበሩ፣ የዚሁ ታላቅ የብፁዕነታቸው በዓል ተሳታፊ ለመሆን የእምድብር ሃገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ እና የባረንቱ ሃገር ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቶማስ የሚግኝዋቸው ከአሥር በላይ የሆኑ ካህናት አብረው በኁባሬ የቀደሱ ሲሆን ደናግል ውሉደ ክህነትና በሮም የሚገኙ ም እመናን በሥርዓቱ ተሳትፈዋል፣

ቅዱስነታቸው በቅዳሴው መካከል ባሰሙት ስብከት የእነ ቅዱስ ጴጥሮስና ጳውሎስ ሰማዕትነት የቤተ ክርስትያን ስደትን ሲያስታውሰን ዛሬም በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ክርስትያኖች በብርቱ ስደት ላይ እንደሆኑ የሚያሳዝነው ግን ሁሉም ምንም እንዳላዩና ምንም እንዳልሰሙ ዝም ማለታቸው ነው፣ በመሥዋዕተ ቅዳሴ ከተነበቡ ንባቦች የመጀመርያዊ ከሓዋርያት ሥራ 12፡1 የተወሰደው “በዚያም ዘመን ንጉሡ ሄሮድስ መከራ ያጸናባቸው ዘንድ ከቤተ ክርስቲያኑ በአንዳንዶቹ ላይ እጁን ጫነባቸው።

 የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው። አይሁድንም ደስ እንዳሰኛቸው አይቶ ጨምሮ ጴጥሮስን ደግሞ ያዘው። የቂጣ በዓልም ወራት ነበረ።በያዘውም ጊዜ ወደ ወኅኒ አገባው … እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍራ ክፍል አሳልፎ ሰጠው። ጴጥሮስም በወኅኒ ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አጥብቆ ይደረግ ነበር። … በዚያች ሌሊት ጴጥሮስ በሁለት ሰንሰለት ታስሮ ከሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባቂዎችም በደጁ ፊት ሆነው ወኅኒውን ይጠብቁ ነበር። እነሆም፥ የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፤ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና። ፈጥነህ ተነሣ አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ።

 መልአኩም። ታጠቅና ጫማህን አግባ አለው፥ እንዲሁም አደረገ። ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ አለው። ወጥቶም ተከተለው፤ ራእይንም የሚያይ ይመስለው ነበር እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም። … ባስተዋለም ጊዜ እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ።ጴጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሉአት አንዲት ገረድ ትሰማ ዘንድ ቀረበች፤የጴጥሮስ ድምፅ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሣ ደጁን አልከፈተችም፥ ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ጴጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች። ... ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ። ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ አለ።” የሚል ክፍል ነበር፣ ቅዱስነታቸውም ይህንን ጠቅሰው ያኔ ይፈጸሙ ስለነበሩ ጨካኝ አያይዝ ስቃይና ኢሰብአዊ ስደቶች ሳንናገር ዛሬ በዓለማችን ስላሉ የክርስትያን ስደቶች የተመለክተን እንደሆነ ከዛኛው በሚብስ ሁኔታ እየተካሄደ ነው፣ የመጀመርያ ማኅበረክርስትያን አባሎች ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ባሳዩት ጅግነንት ሞትንና ስደትን ሳይፈሩ ወንጌልን ለሁሉም ለማዳረስ መቻላቸው የሚደነቅ ሆኖ ዝክራቸውን ስናደርግ ለጸሎትና ለእምነታችን ምስክርነት እንድንሰጥ ጥሪ ያቀርብልናል ብለዋል፣ ቤተክርስትያናችንን እስካሁን ወደፊት ያረማዳት ማኅበራዊ ጸሎቱ አለማቋረጥ ሲካሄድ ነው፣ አንዱ ምሳሌ የጴጥሮስ ሲሆን በሮማ ከተማ ታሪክ ያሉትን ካታኮምበ የሚባሉ ጉድጓዶች የተመለከትን እንደሆነ በስደት ጊዜ ማኅበረክርስትያኖች በኅበረት በተለይ ደግሞ እሁድ እሁድ ጸሎት የሚያሳርጉባቸው ቦታዎች እንደነበሩ እንረዳለን፣

ያ ለጴጥሮስ የተላከ መልአክ ስንጸልይና እግዚአብሔር ለጸሎታችን መልስ ሲሰጥ ለእኛም ይላካል፣ እስቲ እናስተንትን ስንት ጊዜ ነው በችግር ተውጠን ጸሎት ስናሳርግ እግዚአብሔር እንደዚሁ መልአኩ ልኮ ከችግር ያወጣን? ጴጥሮስ ከእንቅልፉ እንደቀሰቀስው ስንት ጊዜ ብቻህን አይደለህም እንደማለት በጉዞአችን ይሸኘናል፣ የኛ ሁኔታ ግን አብዛኛውን ጊዜ በብርቱ ፍራቻ ተውጠን ወይንም ትንሽ ድል ካገኘን በድሉ ሰክረን ሁሉን እንረሰዋለን፣ ወይንም ልክ ለጴጥሮስ እንዳጋጠመው ህልም ሆኖ ይሰማናል፤ ወይንም ያች ጴጥሮስን የተቀበለች በሩን እያንኳኳ ሳትከፍትለት ትታው የሄደች እንሆናለን፣

በታሪክ የተመለከትን እንደሆነ ቤተክርትያንን ለማጥፋት ብዙ ኃይሎች ተነስተዋል ነገር ግን ቤተክርስትያን እስካሁን ጸንታ ትኖራለች፣ የዚህ ዋስትና የማኅበረክርስትያኖች የማያቋርጥ የእምነት ጸሎት ነው፣ ለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ጢሞቴዎች በጻፈው ሁለተኛ መልእክቱ “ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፥ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ። ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል ለሰማያዊውም መንግሥት ይጠብቀኛል፤ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።”(4፤17-18)፣ ይላል፣ እግዚአብሔር ልጆቹን ከዓለም አይለያቸውም እንዲሁም ከክፉ ፈተና ነገር ሁሌ ችግሮችን ለማሸነፈ ጸጋውና ኃይሉ ይሰጣቸዋል፣ በእውነት የሚያምን ሰው ብቻ ነው “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚጐድለኝ ምንም ነገር የለም”(መዝ 23፤1)፣ ከበስተውጭም ይሁን ከበስተውስጥ ቤተክርስትያንን ለማጥፋት ብዙ ጠላቶች ተነሥተዋል ነገር ግን ገዛ ራሳቸው ጠፉ እንጂ ቤተክርስትያን ተርፋለች ሁሌም ሕያውና ፍሬየማ ናት፣ የዚህ ምክንያትም ቅ.ጳውሎስ እንደሚለው “ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን” ለማለት ይችላል፣

ቤተ ክርስትያን የአር እስተ ሊቃነ ጳጳሳት ወይንም የጳጳሳት ወይንም የም እመናን አይደለችም የጌታ ኢየሱስ ክርስቶ ናት፣ ሁሉ ነገር ስለሚያልፍና ጌታ ግን ለዘለዓለም ስለሆነ ብዙ ነገሥታት ሕዝብ ባህሎች አገሮች ር እዮተ ዓለሞች ሥልጣኖች አልፈዋል ቤተክርስትያን ግን በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ስለተመሠረተች ምንም እንኳ ብዙ ማዕበልና ኃጢአቶቻችን ቢከብድዋት ለዘለማለም በአገልግሎትዋ ታማኝ የእምነት መዝገብ ሆና ትኖራች፣ ይህም በእምነት ኃይልና ልጆችዋ በሚሰጡት ብርታት የተሞላው ምስክርነት ሲሆን ዛሬ የምናስታውሳቸው በደማቸው የመሰከሩ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ እንደሌሎቹ ሓዋርያት የጌታን ጽዋ በመጠጣት በደማቸው ቤተክርስትያንን በዚሁ ምድራዊ ሕይወትዋ እንድትፈራ አደረጉ፣ ለዚሁ ምስክርነት ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ “በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል። መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።”(2ጢሞ 4፤6-8)፣ አንዲት ቤተ ክርስትያን ወይንም አንድ ክርስትያን አለምስክርነት መኻን ነው፣ ልክ በሕይወት እንዳለ የሚመስለው የሞተ ሰው ዓይነት ወይንም ፍሬ የማይሰጥ የደረቀ ተክል ወይንም እንደደረቀ ወኃ የሌለው ኩሬ ነው፣ ሲሉ በአጠቃላይ ስለምስክርነት ክተናገሩ በኋላ ወደ አዳዲሶቹ ሊቃነ ጳጳሳት መለስ በማለት የጸሎት የእምነትና የምስክርነት ሰዎች መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል፣

“የተከበራችሁ ሊቃነ ጳጳሳት ዛሬ የምትቀበሉት አክሚም/ፓልዮ እረኛ በትከሻው የተሸከማት በግ ምሳሌ ሆኖ ይህም መልካሙ እረኛ የሆነው ኢየሱስ ምሳሌ በመከተል ዋነኛው ተልእኮአችሁ ይህ መሆኑን እንዳትዘነጉ አደራ ካሉ በኋላ ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በበዓለ ጴጥሮስ ወጳውሎስ እ.አ.አ 2005 ዓም በመል አከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ ያሉትን ስለ ሊቃነ ጳጳሳት ተል እኮ እንዲህ ብለዋል፣

“ይህ ምልክት በሥርዓተ አምልኮ የውህደትና የአንድነት ምልክት ኮኖ መንበረ ጴጥሮስንና ተከታዮቹ መትሮፖሊታዊ መንበሮች የሚያያዝ በአማካኝነታቸውም በመላው ዓለም ከሚገኙ ጳጳሳት ጋር ያስተሳስራል፣ ዛሬ ይህንን አክሚም/ፓልዮ ስሰጣችሁ ይህንን ለጸሎት ለእምነትና ምስክርነት የሚጠራ ተልእኮን በመተማመን እሰጣችኋለሁ፣ ቤተክርስትያናችን ዛሬ የጸሎት ሰዎች ጸሎት የሚያስተምሩ ያስፍልጋታል፣ የተመዛዘነ ሕይወት ከሌለ ምስክርነት የለም፣ ሄሮዱስን ሳይፈሩ እምነት የሚያስተምሩ ስደትንና ሞትን ሳይፈሩ ለም እመናን ምስክርነት የሚሰጡ እረኞች በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በመስቀሉ የማያፍሩ እጅጉን ያስፍልጋሉ ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.