2015-06-05 15:45:00

ካቶሊካውያን የሕግ ሊቃውንትና ዳኞች ማኅበር መግለጫ


የኢጣሊያ መንግሥት አንዳዊ ጾታ ባላቸው ሰዎች መካከል የሚጸናው አብሮ መኖር እንደ ትዳር ይፋዊ እውቅና የሚያሰጥ የሕግ ንድፍ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና እንዲሁም በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ፊት ቀርቦ ውይይት እየተካሄደበት መሆኑ ሲገለጥ፣ አንዳዊ ጾታ ያላቸው ሰዎች የተጋቡ ባለ ትዳሮች ብሎ ሕጋዊ እውቅና መስጠት ልክ በወንድና በሴት መካከል እንደሚጸናው ቃል ኪዳናዊ ጋብቻ በእኩል መመልከት የሚል መሆኑና ቃል ኪዳናዊ ምሥጢር የሚያሰጥ መሆኑ የኢጣሊያ ካቶሊካውያን የሕግ ሊቃውንትና ዳኞች ማኅበር የሚያብራራ ለኢጣሊያ መንግሥት ንድፈ ሕጉን የሚቃወም መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኰ ገለጡ።

የዚህ የኢጣሊያ ካቶሊካውያን የሕግ ሊቃውንትና ዳኞች ማኅበር ሊቀ መንበር ጠበቃ ጃንካርሎ ቸረሊ ጉዳዩ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ውይይት እየተደረገበት ያለው ንድፈ ሕግ አንዳዊ ጾታ ያላቸው ሰዎች የሚያጸኑት አብሮ መኖር እንደ ትዳር እውቅና ለመጠት የሚል ነው። በመሆኑም በወንድና በሴት መካከል ከሚጸናው ትዳር ጋር በእኩል የሚያስቀምጥ ነው። ይኽ ደግሞ በኢጣሊያ ሕገ መንግሥትም ሆነ በፍርድ ቤት ሕግ ጭምር የሌለ አዲስና የኤውሮጳ የሰብአዊ መብትና ክብር አስከባሪው የበላይ ፍርድ ቤት ጫና ያለበት ንድፈ ሕግ ነው። የኢጣሊያ ሕገ መንግሥት ወላጅ አልባ የሆኑትን እንደ አባትና እናት ሆነው ለማሳደግ በሕግ የተጋቡ ባልና ሚስት የሚያቀርቡት ጥያቄ የሚያስተዳድር በትክክል ጥርት ያለ መመሪያ አለ ከዚህ ዓይነቱ ትዳር ውጭ የሚቀርበው የአሳዳጊነት ጥያቄ ብዙ ጥናት የሚጠይቅ ነው፣ ስለዚህ የሕፃኑ መብትና ክብር አለ መጣስ ተቀዳሚው ዓላማ መሆን አለበት ሆኖም የኢጣሊያ ሁለቱ ምክር ቤቶች ውይይት እያካሄዱበት ያለው የሕግ ንድፍ ይኸንን ሁሉ የሚያዛባ መሆኑ የገለጡት ካቶሊካውያን የሕግ ሊቃውንትና ዳኞች ማኅበር መቃወም አልሞ ለመቃወም ሳይሆን፣ የኢጣሊያ ሕገ መንግሥትና እንዲሁም የሥነ ባህል ጥናት መሠረት በማድረግ ያቀረበው የተቃውሞ አስተያየት ነው ብለዋል።

ንድፈ ሕጉ ከጸደቀ ጋብቻና ቃል ኪዳን የሚለው በኢጣሊያ ሕገ መግንሥት ዘንድ የሚሰጠው ትርጉም ሁሉ መቀየር ግድ ይሆናል፣ ጋብቻ በተመለከተ ሕዝብ ያለው አስተያየትና ግንዛቤ ለማስቀየር ያለመ ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለም መሠረት ያደረገ ቤተሰብ የሚያዳክም የቤተሰብ መሠረተ ትርጉሙ የሚያዛባ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.