2015-06-05 19:05:00

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ፊታችን ቅዳሜ ስድስት ቀን በቦዝንያ እና ሄርዞጎቪና ሐዋርያዊ ጉብኝት


 ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ፊታችን ቅዳሜ ስድስት ቀን በቦዝንያ እና ሄርዞጎቪና ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማከናወን እቅድ እንዳላቸውው የሚታወስ ሲሆን፡ ለቦዝንያ እና ሄርዞጎቪና ማሕበረ ሰቦች የቪደዮ መልእክት ማስተላላፋቸው የቫቲካን የዜን ምንጭ አስታውቀዋል።

 

ቅድስነታቸው ለማሕበረ ሰቦቹ ባስተላለፉት የቪደዮ መልእክት የሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ይዘታ በማስመልከት የሐዋርያዊ ጉብኝታቸው መሪ ቃል ሰላም ከእናንተ ጋ ይሁን የተሰየመ መሆኑ ጠቅሰው የክርስትያን አንድነት እና የተለያዩ ሃይማኖቶች ውይይት ያካተተ እንደሆነ አስገንዝበዋል ሲል የቫቲካኑ ዘገባ ያመለክታል። 

የቦዝንያ ሄርዞጎቪና ማሕበረ ሰቦች በጋርዮሽ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመሩ ያላቸውን ዓቢይ ተስፋ ገልጠውም ለዚህም አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሆነ በማያያዝ መግለጣቸው የቫቲካን መግለጫ አክሎ አስገንዝበዋል። 

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዚሁ ትናትና ለቦዝኒያ ሄርዞጎቪና ማሕበረ ሰቦች በቪደዮ ያስተላለፉት መልዕክት በመቀጠል በእግዚአብሔር እገዛ በመካከላችሁ ሲገኝ የሚሰማኝ ደስታ የላቀ ነው ብለው የማሕበረ ሰቦቹ ካቶሊካውያን የሚያካሄዱት የክርስትያን አንድነት ውይይት ለማበረታታት እና ለማረጋገጥ እንደሆነ በአከባቢው ሰላም እና መረጋጋት እንዲኖር ባለፈው ቅርብ ግዜ የተካሄደው አሰቃቂ የርስ በርስ ጦርነት የተወው ጠባሳ ለመፈወስ የተሻለ መጻኢ ግዜ ለማነጽ በሚቻልበት ሁኔታ ለመወያየትም እንደሆነ መግለጣቸው ተመልክተዋል።

ሞትን አሸንፎ የተነሳ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሳኤ ምሽት ታቦት እንደታያቸው ሰላም ከናኝተ ጋ ይሁን እንዳላቸው በማስታወስም እሱ ማለት መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ኅይላችን እና ተስፋችን ነው እና ሰላሙ እንዲሰጠን እንለምነው ማለታቸውም መግለጫው ተናግረዋል።

ወደ እናንተ ወደ ሳራየቮ ሲመጣ እንደ ወንድማችሁ እና የሰላም መልእክተኛ በመሆን እና የእግዚአብሔር ምሕረት ለማወጅ ነው እንዲሁም ሐዋርያዊ ጉብኝቱ በጉጉት የሚጠባበቀው እንደሆነ ልግልጽላችሁ እወዳለሁኝ ሲሉም በቪደዮ መልእክቱ በኩል አክለው ማስገንዘባቸው በማያያዝ አመልክተዋል። 

የቦዝንያ እና ሄርዞጎቪና እኅቶቼ እና ወንድሞቼ ከናንት ጋ ያለኝን መንፈሳዊ ቅርበት እና ፍቅር ልገልጥላችሁ እወዳለሁ በቅርቡ እስከ ምንገናኝ ደህና ቆዩኝ ቸር ይግጠመን በማለት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቪደዮ መልእክታቸው  እንዳጠቃለሉ  በቫቲካን   የተሰጠ  መግለጫ አስገንበዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናትና ረፋድ ላይ በዘለዓለማዊት ሮም ከተማ ሀገረ ስብከት ሐዋርያዊ ወኪላቸው ብጹዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቪላኒ በላቲን አመሪካ በቺለ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ እንደራሴ ብጹዕ አቡነ አንቶንዮ ሶጾ እንዲሁም የካሪታስ እንተርናጽዮናሊስ ዋና ጽሐፊ ሚሸል ሮይ በቅደም ተከተል በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው በቫቲካን የተሰጠ መግለጫ አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የፍቅር ስልጣኔ  አገልጋይ ለሆነ ሁሉ በየቅዱስ ወንጌል ብርሃን ይመራል በማለት በትዊተር@Pontifex በኩል አሰራጭተዋል።  20 ሚልዮን ምእመናን  ቅድስነታቸውን በዚሁ ማሕበራዊ መገናኛ በኩል እንደሚከታተሉ ይታወቃል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.