2015-06-05 15:42:00

ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መግነዘ እይታ ገዛ እራሳቸን አቀረቡ


በሮማ ሰበካ የቅድስት ሉቺያ ቁምስና አዘጋጅነት እ.ኤ.አ. ዛሬ ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. የተጠናቀቀው 40 ድኾች ቶሪኖ ወደ ሚገኘው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መግነዝ በተኖረበት ቅዱስ ሥፍራ መንፈሳዊ ንግደት ማካሄዳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ በነደታ ካፐሊ ገለጡ።

ድኾች ቶሪኖ ወደ ሚገኘው የጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ቅዱስ መግነዝ በታቀበበት ቅዱስ ሥፍራ መንፈሳዊ ንግደት እንዲያካሂዱ በማለት አስፍፈላጊውን ወጪ ሁሉ የለገሱት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መሆናቸው የቅድስት ሉቺያ ቤተ ክርስቲያን ቆሞስ አባ ፓብሎ ካስቲሊያ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገለጡ።

ድኾችን ቅዱስ መግነዝ ወደ ታቀበበት ቅዱስ ሥፍራ መንገሳዊ ንግደት ያካሂዱ ዘንድ ቅዱስ አባታችን ያሰቡትና ወጪውን ሁሉ በመሸፈን ያሳዩቱ የፍቅር ሥራ ድኾች የወንጌል ማእከል መሆናቸው ደጋግመው የሚያቀርቡት ጥሪ የሚያስተጋባ መሆኑ አባ ካስቲሊያ ገልጠው፣ ይኽ ደግሞ ወደ ጥጋ ጥግ የከተሞቻችንና የህልውና ክልል እንል ዘንድ የሚሰጡት ምዕዳን በተግባር የሚገልጥ ነው። የዚህ ሁሉ ፍጹም አብነት እኛን ለማዳን ሰው ሆኖ ገዛ እራሱ ከሁሉም በታች ዝቅ በማድረግ ድንኳኑን በመካከላችን ያኖረው ወልደ እግዚአብሔር የገለጠው ተልእኮ መሆኑ ቅዱስ አባታችን የሚሰጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን ይኸንን ወንጌላዊነት ማእከል የማያደርግ ክርስትና ባዶ ትርጉም የሌለው እንደሚሆን ያረጋግጥልናል። እያንዳንዳችን የጌታ ማዳን የሚያስፈልገን ድኾች ነን። በቅዱስ መግነዝ ፊት የእኛ ቢጤዎች ባካሂዱት መንፈሳዊ ንግደት ለጌታችን ኢየሱስ እይታ ገዛ እራሳቸውን እንዳቀረቡም ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.